(የደብረ መዊዕ ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ስብከተ ወንጌል ሐላፊ)
“በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።” (፩ኛ ጴጥ ፫፥፲፭)
የዚህ “ምስጢራዊ ቡድን” የተሰኘው ትምህርታዊ ምላሽ ዓላማ፦ ከውጭ ኾነው፥ ቤተ ክርስቲያናችንን መዋጋት የተሳናቸው፣ እኛን አኽለውና እኛን መስለው ወደ ውስጣችን በመግባት፣ በዲቁናና በቅስና ከተቻለም እስከ ጵጵስና መሐረግ በመድረስ፣ ቀን ጠብቀውና ጊዜ አመቻችተው፣ ጸረ-ክርስትናን የኾነን እምነት እንደ አዲስ እንደተቀበሉ በማወጅ፣ የእምነቱ ተከታይዎች ላይ ጥርጣሬ በመዝራትና ከተቻለም አስክዶ በመውሰድ፤ ጸረ-ክርስትናን እንቅስቃሴ የሚያደርጉትን ወገኖች ማጋለጥ ሲሆን፤ በሌላ መልኩ፥ እነዚህ ጸረ-ቤተ ክርስቲያ ኃይሎች የዘሩትን የኑፋቄ ትምህርት ሰምተው፣ ግራ የተጋቡ አማንያንን ለማረጋጋትና የያዙት እምነት እውነተኛ የሕይወት መንገድ መሆኑን፣ ቤተ ክርስቲያንም፥ ለሚጠይቋት ሁሉ በቂና ከበቂ በላይ የኾነ መልስ እንዳላት ለማስገንዘብ ነው።
ከዚህ በፊት (በምስጢራዊ ቡድን በክፍል ፩ ሀ እና ለ በማፈናጠር ይመልከቱ) እንደገለጽነው አንድ ሠው የፈለገውን እምነት እንዲያምንና ያመነበትን እምነት እንዲከተል ሕገ-መንግሥታዊም ሆነ ሕገ-እግዚአብሔራዊ ነፃነት እንዳለው ቢታወቅም፤ የራስን እምነት፥ በነፃነት ማራመድ፣ ያወቁትን ለራስ እምነት ተከታዮች ማሳወቅ እየተቻለ፤ የሌላውን እምነት፥ ማንቋሸሽና ማጥላላት፣ መለኮታዊ የሆኑትን ቅዱሳት መፃሕፍትን መንቀፍ፣ አማንያኑን መዝለፍ፤ ተገቢ ነው ብለን አናምንም!።
መቼም ዛፍ እራሱን ለመከላከል ካልሆነ በቀር መኪና ገጭቶ አያውቅም እንደተባለ፤ ሳንደርስባቸው ለደረሱብን፣ ሳንነካቸው ለነኩን፤ ዶግማችንና ቀኖናችን እንዲሁም ሥርዓታችንን አልፎም ትውፊታችንን ለመናድ ለሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች እንደየ አመጣጣቸው ተገቢውን መልስ መስጠት ግድ ይለናል።
፩ ሁኔታዎች አሳሳቢ እየሆኑ ነው፤ የተነገሩት ትንቢቶች በአፋጣኝ እየተፈጸሙ ነው። ወደድንም ጠላንም፥ አሁን የመጨረሻው መጨረሻ ላይ ነን።
፪ ስለዚህ በአፋጣኝ ይህንን ቪሲዲ ይመልከቱና ላላዩት በማሳየት ክርስቲናዊ ግዴታዎን ይወጡ።
የኻሊድ ካሳሁንና የዳኢ ኻሊድ ክብሮም የተዛባ አስተምህሮታቸውንና እነርሱ ስተው፣ ሌላውን ለማሳት የተደረገውን ሴራ የሚያጋልጥ፣ ጥልቅና ድንቅ፣ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፍቃድ አጋዥነት ምጡቅ ምላሽ በወንድማችንና በመምህራችን በመምህ ምሕረትተአብ አሰፋ የተዘጋጀ ምስለ-ወድምፅ (ቪሲዲ) ይመልከቱና ላላዩት በማሳየት ክርስቲናዊ ግዴታዎን ይወጡ!።