Showing posts with label ነገረ ቅዱሳ. Show all posts
Showing posts with label ነገረ ቅዱሳ. Show all posts

Wednesday, April 22, 2015

“የሰማዕታት ደም የቤተ ክርስቲያን [ምርጥ] ዘር ነው” (ጠርጠሉስ)



ጠርጠሉስ የተባለውና 2ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (160 AD - 220 AD) የነበረው ታላቅ ፀሐፊና የክርስትና ጠበቃ ስለ ሰማዕታት ደም በተናገረበት ሥፍራ ያስቀመጠው ነው። ተርቱሊያን/ Tertullian ወይም በእኛ አጠራር ጠርጠሉስ የሚባለው ሊቅ ከመጀመሪያዎቹ የክርስትና አባቶች ጋር የሚቆጠር እንዲያውም የላቲኖች (በላቲን የምትናገረው፣ የምትጽፈው) ቤተ ክርስቲያን ወይም የምዕራብ ቤተ ክርስቲያን አባት ተብሎ መጠራት እንዳለበት ብዙዎች የሚስማሙበት ሊቅ ነበር። በእኛ በኦርቶዶክሳውያንም ሆነ በካቶሊኮቹ ዘንድ ብዙም ስሙ ሲጠቀስ የማይሰማው ከጻፋቸው ጽሑፎች መካከል ከቤተ ክርስቲያን ትምህርት የወጡ ስላሉበት ነው። ይሁን እንጂ ይህንን ሊቅ በዚህ ሥፍራ መጥቀስ የፈለግኹት አገሩና ምንጩ የሰሜን አፍሪካ (የዛሬዋ ቱኒዚያ) አካል በሆነችው በካርቴጅ የተገኘ በመሆኑ ጭምር ነው። []

እንዴት ዓይነት መከራ ይቀበሉ እንደነበረ፣ እንዴት ዓይነት ሰማዕታት ይቀበሉ እንደነበረ፣ በነገሥታቱ ፊት፥ ቀርበው ሲመሰክሩ እንዲህ አሉ፦ አውግዙን፣ አሰቃዩን፣ ስቀሉን፥፣ ግደሉን፣ አጥፉን፤ የእናንተ ክፋት ለእኛ እውነተኝነት ምስክርነት ነው! የእናንተ እንዲህ ክፉ መኾን፣ የእናንተ እንዲህ አረመኔ መኾን፣ የእናንተ እንዲህ ደካማ መኾን፤ የእኛ እውነተኝነት ይመሰክራል። []

አሰቃዩን፥ ስቀሉን፣ ግደሉን፣ አጥፉን፤ የእናንተ ይኼ ክፋታችሁ፥ የእኛ እውነተኝነት ይመሰክራል። በእናንተ በተሰቃየን ቁጥር፥ እየበዛን እንኼዳለን፤ የሰማዕታት ደም የቤተ ክርስቲያን ዘር ነው። ባሰቃያችሁን ቁጥር እየበዛን እንኼዳለን። የሰማዕታት ደም የክርስትና ዘር ነው። እኛ ሁላችን በሰማዕታት ደም የተዘራን ነን! []

Friday, May 9, 2014

ዝክረ ቅዱሳን፦ ማርያምን!!!



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን!

ወዳጄ ሆይ፦ አንተ አመልከዋለሁ የምትለው አምላክ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ከኾነ፦ ትንቢት የተነበየለት፣ "የዘመኑ ፍፃሜ" ከሴት ብሎ ከእናቱን ከቅድስት ድንግል ማርያምን በሥጋው እንደተወለደ፣ በጌታ ዘንድ ጻድቅና ትጉህም የነበሩ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ከእናቱ ጋር አብረው እንደባረኳት፤ እናነባለን እንጂ ክርስቶስን ብቻ እንባርክ አላሉም! /ሉቃ ፪፥፳፭፤ ገላ ፬፥፬/ ማርያምን!!!

በጌታ ዘንድ ጻድቅና ትጉህም የነበሩ ከባረኳት፣ ለጌታችን፣ ለመድኃኒታች፣ ለኢየሱስ ክርስቶስ ለሥም አጠራሩ ክብርና ልዕልና፣ ውዳሴና ምስጋና፤ ይገባውና አንድ ጊዜ የመረጣቸውን ሐዋርያት እንዲኾኑ ወስኗል። ለዚኽ ነው፥ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፤ በሮሜ መልዕክቱ፦ "ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው። እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?" /ሮሜ ፰፥፳፱-፴፩/ ሲል አንድ ጊዜ የመረጣቸውን እስከመጨረሻው እንዳከበራቸው ይገልጽልናል። ማርያምን!!!

እራሱ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ።" ያለበት ያለ ምክንያት አይደለም! ክርስትና መምሰልና መኾኑ እንዳለብን ሲያስገነዝበን ይህን ተናገረ። /፩ኛ ቆሮ ፲፩፥፩/ አንድ ክርስቲያን፥ ክርስቶስን አምላኬ ነው ካልን፤ መምሰል ደግሞ ግድ ይላል! ያውም፥ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ መምሰልና ኾኖ መገኘት! ማርያምን!!!

እንደዚህ ዓይነቱ መምሰል ደግሞ  የቅዱሳንና የፃድቃንን መትጋትና ተጋድሎ አይቃወምም! ቅዱሳንን ማክበር ከዚኽ ይጀምራል። ዓይነ-ሥውራኖች (ዓይነ-ለሞች) እኮ መዳን ቢፈልጉ "የዳዊት ልጅ ማረን" እንዳሉ ልብ ማለት ይገባል! /ማቴ ፱፥፳፯፤ ፲፭፥፳፪/ "የዳዊት ልጅ" የሚለው የመጠሪያ ሥም በመንፈሳዊ ዕይታ እንዴት እንደቀደመ ማገናዘብ ይጠይቃል። ለዚኽም ነበር ቅዱስ ማቴዎስ የቅዱሳንን ተጋድሎ ከመናገሩና ከመፃፉ በፊት፤ የወገናቸውንና የአባታቸውን ሥም በማስቀደም በመጥራት ይጀምራል። ለዚኽም አንድ ማሳያ እንዲኾነን፦ "ከአሴር ወገንም የምትሆን የፋኑኤል ልጅ ሐና የምትባል አንዲት ነቢይት ነበረች፤ እርስዋም ከድንግልናዋ ጀምራ ከባልዋ ጋር ሰባት ዓመት ኖረች" ይላል። /ሉቃ ፪፥፴፮/ ማርያምን!!!

እንዲኹ ደግሞ፦ በቅዱሳን መንፈስና ክርስቶስን በመምሰል፤ የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እናትና አባቷ የነበራቸው መንፈሳዊ ተጋድሎና ሕይወት፣ ስለ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፥ ፅንሰትና ውልደት፣ ሕይወቷና አጠቃላይ መንፈሳዊ ተጋድሎዋ ቢሰበክና ቢፃፍ፤ የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፦ እግዚአብሔር፥ የጠራቸውን፣ ያጸደቃቸውን፣ ቅዱሳንን ማክበርና ተገቢ መኾኑን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አስረግጦ ገልፆ አስተምሮናል። (በነገራችን ላይ፥ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያናችን ለሌሎችም ቅዱሳን በዓላቸውን ታከብራለች) ስለዚኽ፦ እግዚአብሔር፥ የጠራቸውን፣ ያጸደቃቸውን፣ ቅዱሳንን አለመቃወማች አስረግጠን እንገልጽለን እንጂ! አንቃወምም! ማርያምን!!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወድንግል ማርያም ክብር፤ አሜን! (//፳፻፮ /)