የእግዚአብሔር ቃል ክብር ለሚገባው ክብር መስጠት እዳለብን ያስተምረና፤ /ሮሜ ፲፫፥፯/ ቢኾንም ግን አንዳንድ
የፕሮቴስታንቶች ፓስተሮች (የተቃዋሚ አገልጋዮች) ይኼንን አምላካዊ ቃል ወደ ጎን በመተው የራሳቸውን ሥጋዊ ምኞቶቻቸው
እንዳዛዘቸው እየፈጸሙና እያስፈጸሙ ነው። አባታችሁ ዲያብሎስ ስለኾነ፣
ከመንፈሳዊነት ይልቅ ሥጋዊ ምኞት ስላሳወራቸው፤
የሥጋዊ ምኞታቸውን እየተከተሉ የሚፈልጉትንና የሚመኙትን ነገሮች ሁሉ በቤተ-ክርስቲያኒቷ ላይ እጃቸውን በኃይል በመጫን ያሻቸውን ማድረ ጀምረዋል።
ቢኾንም ግን ከመጀመርያው ጀምሮ ፕሮቴስታንቶች፥ ከካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሲያፈነግጡ፤ የነበራቸው እምነትና ሃይማኖት
ከካቶሊካውያን የወረሱትን መሠረታዊ የካቶሊካውያንን ሥርዓት በመያዝ ነበር። ሉተር፥ ከካቶሊካውያን ያፈነገጠበት ዋናው ምክንያት፦
ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን በወቅቱ ለአንዳንድ ነገሮች የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስለፈለገች ስለነበር ያዘጋጀችውን ትኬት “የመንግሥተ ሠማያት የመግቢያ ትኬት” ነው፤ ትኬቱን
ግዙ እያለችና እያስባለች በነበረበት ወቅት በሉተር አማካኝነት ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ተቃውሞ ገጠማት። ይኼም ተቃውሞ እየበረታና እያየለ ኼዶ፤ ካቶሊካዊት
ቤተ-ክርስቲያን የራሷን ልጆች የነበሩትን እነ ሉተርን በማግለልና እነ ሉተርም የራሳቸውን ተቃውሞ በሀገሩ ላይ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ የቀድሞ የካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን በሮች ላይ
የተቃውሞውን ሐሳቦቹን ጽፎ ለጥፎ ነበር።
ይኹን እንጂ፥ የፕሮቴስታንቶች እምነትና ሃይማኖት እንደዚህ ከመቀየሩ በፊት፦ ለመድኃኒታችንና ለአምላካችን ለኢየሱስ
ክርስቶስ ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳንና ለሰማህታት ባዘዛቸው መንገድ፥ ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያም፣
ለቅዱሳኑ፣ በአጠቃላይ ከካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን የወረሱትን ሃይማኖታና ባህላዊ፣ ትውፊትና ቅዱሳት መጽሐፍቶቻቸውን
እስከተወሰነ ጊዜያት ድረስ ይጠቀሙበት ነበር።
ከዛ በኋላ የተነሱ ልዩ ልዩ የፕሮቴስታንቶች መሪዎችና ፓስተሮች የተዛባ አስተሳሰባቸውን በመርጨት፦ ለድንግል ማርያምና
ለቅዱሳን፣ ለሰማህታትና ለፃድቃን፣ ለደናግልና ለአባቶች፤ እንዲሁም ደግሞ ለቅዱሳት መጽሐፍትና ለቅዱሳት ሥዕላት፤ ማንቋሸሽ፣
ማብጠልጠል፤ ጥቅም አልባ ማድረግ፤ ከምዕመናኑ፥ ልቦናና ኅሊና ፍቆ ማውጣት፤ የነደፉት ንድፈ-ሐሳባቸውን በመጫን ያላቸውን ጥላቻ
ቀስ በቀስ ቀጠሉበት።