Sunday, March 2, 2014

ግብረ-ሰዶማውያንና የባህድ ስውር መነፅር፤ ለሃገራችን አይበጃትም!



ሚኒስትር / ዘነቡ ሆኑ የኢአህዴግ ባለስልጣናት እንዲሁም የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቢሆኑም በግብረ-ሰዶማውያን ላይ በአፅኖት ማስገንዘብ አለባቸው። ዳር-ዳር ማለት አያዋጣም!

እውነት ነው ኢትዮጵያ የሴቶች፣ የወጣቶች፣ የሕጻናትና የእናቶችን ነገር በተመለከተ፤ ቡዙ የብዙ፣ ሕጎቿን በማጥበቅ እና እጅግ አድርጋ አርቅቃ መስራት ይጠበቅባታል እንጂ ለአስጸያፊ ድርጊት የአሜሪካንንና የአውሮፓ ሃገራትን የሞት ምኞት ማስተናገድም ይሁን በር መክፈት የለባትም!

እርግጥ ነው፤ በመንግስ መገናኛ-ብዙሃን፦ ስለ ግብረ-ሰዶማውያን አስከፊነት፣ የነውር ድርጊት መሆኑን፣ የሥነ-ልቦና ቀውስ እንደሚያስከትል፣ በዚህ አስጸያፊ ድርጊት የገቡና የኖሩ ሰዎች ለተለያየ በሽታዎች የመያዛቸው ዕድል በጣም ከፍ-ያለ ሰፊ መሆኑን፣ በጭንቀትና በውጥረት መሰቃየታቸው እንደሚጨምር፣ እራስ-በራስ የማጥፋት ደረጃ በነዚህ ሰዎች ላይ ቁጥሩ እንደሚያይል፣ አጠቃላይ ግብረ-ሰዶማውያን አስከፊነትና መራራነት፤ በዜና አውታራቸው አለመዘገባቸው፤ ወዴት እየሄድን ነውም? ያሰኛል!

ወዳጆች ሆይ፦ በውጭ ዓለማት ላላቹ፤ በተለይ ደግሞ በአሜሪካና በአውሮፓ ሃገራትን ያላቹ! ዘመኑ ከባርነት ዘመን ወደ ዲሞክራሲያዊ ባርነት ዘመን (ከሃገራችን የወጣንበት የተለያየ ምክንያት ቢኖረንም) ላይ መድረሳች ይታወቃል። ይህን ስል፥ ማንም ቢሆን ሃገሩ ላይ መኖን የሚጠላ ሠው ያለ̕ አይመስለኝም።

ስለዚህ ውድ፥ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን፣ እንዲሁም ኤርትያዊያንና የኢትዮጵያዊያን ወዳጆች በሙሉ፤ በአሜሪካና በአውሮፓ ሃገራትን ለመኖር የጥገኝነት ጥያቄ ለማግኘ አቋራጩ መንገድ በኢትዮጵያ ውስጥ "ግብረ-ሰዶማዊ" ነበርኩኝ እንዲሉ፤ በሃገራቸውም ላይ የመቆያና የመኖርያ ፍቃድ እንዲያገኙ አሜሪካና አውሮፓ መስመራቸው በመዘርጋት እየሰሩ ይገኛሉ።

ከዚህ አስነዋሪ "ግብረ-ሰዶማዊ" ድርጊት ጊዜያዊና የሚያልፍ፣ የመቆያና የመኖርያ ፍቃድ፤ ከማግኘት ይልቅ የማያልፈውን ዘላለማዊውን ተስፋ እያሰብን የመቆያ ሥፍራ እንዳለን ማወቅ አለብን። /፪ኛ ቆሮ ፭፥፩/
ግብረ-ሰዶማውያን "ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።" ቢሆንም ግን ከዚህ ግብረ-ፆር ተላቀው፣ ወደ ቅድስና ሕይወት የተመለሱትን፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ያደነቃቸውና የመሰከረላቸው ስለ ግብረ-ሰዶማውያን ተንሣሕያን፦ "ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።" ብሏል! /ዘሌ ፲፰፥፳፪፤ ፩ኛ ቆሮ ፮፥፱-፲፩፤ ቲቶ ፫፥፫-/

እና ታዲያ መንግስት ግብረ-ሰዶማውያን ከዚህ የሞት-ምግባራቸው ሳይታደጋቸ፤ ይባስ፥ ለጥፋትና ለሚሞቱበት፤ የአሜሪካንንና የአውሮፓ የሚያገናኝ የግብረ-ሰዶማውያን ድልድይ ለመዘርጋት፤ የኢ ግብረ-ሰዶማውያን የተቃውሞ ሰልፍ መበተንና ድምፅ እንዳያሰሙ ማድረጉ፤ እንደ ማሳያ የመንግስት ድጋፍ መሆኑን ያመላክተን ይሆናል።

በግብረ-ሰዶማውያን ጉዳይ የመንግስት ድጋፍ የሚያደለው ወዴቱ ይሆን? የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዝምታቸውስ እስከ ምን ድረስ ይሆን? እንደ ስዊዲን መንግስት ግብረ-ሰዶማውያን አወንታዊ ምላሽ እንዲያገኙ፣ በፓርላማቸው ሕግ አፅድቀው የማደጎ ልጅ እንዲያገኙ አድርገዋል። በኢትዮጵያስ የዚህ ዕጣ-ፋንታ ተቋዳሽ እንዳትሆን የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይሁኑ የሃይማኖት መሪዎች በዚህ ነገር ላይ ጠንክረው መንግስትን ሃይ! ይሄ የኢትዮጵያ ማንነትን የሚያንጸባርቅ ስላልሆነ እዛው ባለበት ማለት ይጠበቅባቸዋል።

ይህ ሳይሆን ቢቀር እንደ ስዊድን ሃገር፤ የግብረ-ሰዶማውያን (ካህናትና አገልጋይ) ልትፈበርክ ትችል ይሆናል፤ ግን ማንስ ንስሐ ሊገባ ይደፍራል? የቱስ የግብረ-ሰዶማውያን (ካህን) ነው የንስሐ ልጁን እንዴትስ ምክርና ተግሳፅ ሊገስፅ የሚችለው? እንዴትስ ነው ኑዛዜንና የቤ/ክርስቲያንን ሥርዓተ-ምስጢር ለትውልድ የሚያስተላልፈው፣ እንዴትስ ነው የሃገር መሪ የወገን ተቆርቋሪ ልናገኝ የምንችለው?

እንጃ! እኔ በበኩሌ የዘንድሮ መንግስት (ኢአህዴግ) ከሃገር መሪና ከወገን ተቆርቋሪነት ባሻገር የሚያይበት ሌላ፤ ግብረ-ሰዶማውያንና የባህድ ስውር መነፅር ለሃገራችን አይበጃትም! አይጠቅማትምም ባይ ነኝ!!!

No comments:

Post a Comment