በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራዕይ በጥሬ-ቃል “እግዚአብሔር” የሚለው ቃል ወይንም ሐረግ 7361 (ሰባት ሺ ሦስት መቶ ስልሳ አንድ) ጊዜያት ተጠቅሶና ተጽፎ እናገኛለን። እንደዚህ ቢሆን መፅሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሥም በአንድም በሌላም መንገድ እናገኘዋለን፤ ለምሳሌ እኔ የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የያዕቆ አምላክ እንዲል።
"እግዚአብሔር
ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው!" በሚለው በዚህ ጥቅስ
ውስጥ ሁለት ዓበይት ነገሮችን እናገኛለን። ይኸውም፦
2ኛ . "ተዋጊ" የሚሉትን ቃል ወይንም ሐረግ ናቸው።
"እግዚአብሔር"
ማለት «ያለና የሚኖር፣ መጀመርያውና መጨረሻው፣ አልፋና ዖሜጋ፣ ፊተኛውና ኋለኛው፤» ማለት ነው፥ ይህም የዘላለሙ ስሙ ነው። /ዘጸ 3፥14፤ ራእ 1፥17፣ 2፥8፣ 21፥6፣ 22፥13፤/
"ተዋጊ" ማለት ደግሞ በአንድም በሌላ መንገድ እግዚአብሔር
ስለ እኛ መጠጊያ፣ ስለ እኛ ጋሻ፣ ስለ እኛ መከታ፣ ስለ እኛ ተዋጊ
(ይዋጋል)፥ እኛም ዝም እንላለን! እርሱም፥ ማዳኑን፣ ፍቅሩን፣ ቸርነቱንና ምህረቱን በእነዚህ መንገዶች ይገልጥልናል ማለት ነው። /ዘጸ 14፥14፤ ዘዳ
1፥30፣ 3፥22፤ ነህ 4፣20፤ 2ኛ ሳሙ 22፥31፤ መዝ 5፥12፣ 28፥7፣ 90፥1፣ 91፥1-10፤ ምሳ 30፥5፤ ኢሳ 38፥14፤ ዘካ 14፥3፤ ሮሜ 13፣12፤ ኤፌ 6፥16፤ ዮሐ 19፥11፤/
እግዚአብሔር ማለት «ያለና የሚኖር፣ መጀመርያውና መጨረሻው፣ አልፋና ዖሜጋ፣ ፊተኛውና ኋለኛው፤» ነው ካልን፤ ታዲያ ተዋጊ ደግሞ፥ መጠጊያ፣ ጋሻ፣ መከታና ተዋጊ እንደሆነ ተመልክተናል። ስለዚህ ሁለቱን ስናቀናጀው፥ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፣ እግዚአብሔር ጋሻ ነው፣ እግዚአብሔር መከታ ነው፣ እግዚአብሔር መጠጊያ ነው፤ የሚሉ ሐይለ ቃል ወይንም ሐረግ እናገኛለን።እንግዲህ የእነዚህን የሁለቱን ትርጉሞችን ከተረዳን እንደ እግዚአብሔር
ፈቃድ "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው!"
የሚለው ጥቅስ እንዴት እንየው ከመጽሐፍ ቅዱስ ዕይታ?
* የእግዚአብሔር፥ ጋሻ፣ መከታና ውጊያ፤ ወደ ፈርዖን ቤት፦
እስራኤል ዘ ሥጋ በጽኑ ሐዘን፣ በከባድ የጉልበት ሥራ፣ በመረረ ለቅሶና
በታላቅ በሆነ ጩኽት በግብፅ ምድር ሳሉ ነበር እግዚአብሔር ለሊቀ ነቢያት ለሙሴ ተገልጦለት ወደ ፈርዖን
ቤት ሄዶ ህዝቤን እንዲያገለግለኝ ልቀቅ በል ብሎት በሰደደው ጊዜ ነበር ሊቀ ነቢያት ሙሴ አንድ
ጥያቄ ጠየቀ።
የሊቀ ነቢያት ሙሴ ጥያቄም፦ "ሙሴም፥ እግዚአብሔርን ወደ ፈርዖን የምሄድ የእስራኤልንም ልጆች ከግብፅ የማወጣ እኔ ማን ነኝ? ብሎ በጠየቀው ጊዜ፤ እርሱም
(እግዚአብሔር)፦ በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ነው፤ ሕዝቡን ከግብፅ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ ለእግዚአብሔር
ትገዛላችሁ አለ። ሙሴም እግዚአብሔርን፦ እነሆ፥ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜ፣ የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ ባልሁም ጊዜ፣ ስሙስ ማን ነው? ባሉኝ ጊዜ፥ ምን እላቸዋለሁ?
ሲል፤ እግዚአብሔርም ሙሴን፦ «ያለና የሚኖር» እኔ ነኝ ብሎታል። እንዲህ ለእስራኤል ልጆች «ያለና የሚኖር» ወደ እናንተ ላከኝ ትላለህ። እግዚአብሔርም
ደግሞ ሙሴን አለው፥ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ። የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅም አምላክ፣ የያዕቆብም አምላክ፤ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ላከኝ ይህ ለዘላለሙ ስሜ ነው፥ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።" ትላለህ ብሎታል። /ዘጸ 3፥11-15/
እዚህ ጋር ታዲያ በእግዚአብሔር ፍቃድ አዛዥነት፣ በሊቀ ነቢያት ሙሴ ታዛዢነት፤ እስራኤል ዘ ሥጋ በብዙ መከራና ችግር፣ ከውጣ-ውረድና እንግልት፤ ከባርነት ወደ ነፃነት ከመውጣታቸው በፊት እግዚአብሔር ትእዛዝ አዟቸው ነበር። ትእዛዙም፦ የበጉ የደም ምልክት በቤቶቻቸው እንዲሆንላቸው
ነው። ከወጡ በኋላ
ደግሞ ትእዛዙን እንዲጠብቁት እርሱ የበጉ
የደሙ ምልክት የእግዚአብሔር ፋሲካ
ነውና በዓል አድርጉ ብሎ ትእዛዝ አዟቸዋል።
“የበጉ የደሙ ምልክት የእግዚአብሔር ፋሲካ ነውና በዓል
አድርጉ” የበጉ የደም ምልክትና ፋሲካ የሚለውን! ልብ ይበሉ!
* እስራኤል ዘ ሥጋ፦
እስራኤል ዘ ሥጋ በወጡበት ወቅት፥ ሠላም፣ ሐሴት፣ ፍስሐ፤ በሆነበት፥ በዚያም ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህንን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፥ እንዲህም ብለው
ተናገሩ።
በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤
ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።
ጕልበቴ ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፥ መድኃኒቴም ሆነልኝ፤
ይህ አምላኬ ነው አመሰግነውማለሁም፥ የአባቴ አምላክ ነው ከፍ ከፍም አደርገዋለ።
እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው፤
የፈርዖንን ሰረገሎች ሠራዊቱንም በባሕር ጣላቸው፤
የተመረጡት ሦተኞች በኤርትራ ባሕር ሰጠሙ።
ቀላያትም ከደኑአቸው፤
ወደ ባሕር ጥልቀት እንደ ድንጋይ ሰጠሙ።
አቤቱ፥ ቀኝህ በኃይል ከበረ፤
አቤቱ፥ ቀኝህ ጠላቱን አደቀቀ።
በክብርህም ብዛት የተነሡብህን አጠፋህ፤
ቁጣህን ሰደድህ፥ እንደ ገለባም በላቸው።
በአፍንጫህ እስትንፋስ ውኆች ተከመሩ፥
ፈሳሾችም እንደ ክምር ቆሙ፤
ሞገዱም በባሕር ውስጥ ረጋ።
ጠላትም፦ አሳድጄ እይዛቸዋለሁ፥
ምርኮንም እካፈላለሁ፥
ነፍሴም ትጠግባቸዋለች፤
ሰይፌንም እመዛለሁ፥ እጄም ታጠፋቸዋለች
አለ።
ነፋስህን አነፈስህ፥ ባሕርም ከደናቸው፤
በኃይለኞች ውኆችም እንደ አረር ሰጠሙ።
አቤቱ፥ በአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
በምስጋናህ የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥
በቅድስና የከበረ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
ቀኝህን ዘረጋህ፥ ምድርም ዋጠቻቸው።
በቸርነትህ የተቤዠሃቸውን
ሕዝብህን መራህ፤
በኃይልህ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ አገባሃቸው።
አሕዛብ ሰሙ፥ ተንቀጠቀጡም፤
በፍልስጥኤም የሚኖሩት ምጥ ያዛቻው። /ዘጸ 15፥ 1-14/
የሊቀ ነቢያት ሙሴ ኅህት ማርያም፣ ዘማርያንና ዘማሪያት ተሰብስበው በሆሆታና በእልልታ የእግዚአብሔርን፥ ተዋጊነት፣ ኃያልነት፣ መድኃኒትነት፣ መጠጊያነት፣ ጋሻነት፤ ከመዝሙሩ መንፈሳዊ ሥነ ግጥም መረዳት እንችላለን።
* ፋሲካና
እስራኤል ዘ ሥጋ፡-
ከዚህ በኋላ እስራኤል ዘ ሥጋ እግዚአብሔር
እንዳዘዛቸው የበጉ
የደም ምልክት እያስታወሱ ለብዙ ዘመናት ፋሲካ እያከበሩ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ በግልፅ ይነግረናል። /ዘጸ 12፥11፤ ዘሌዋ 23፥3፤ ዘኍል 9፥12፣14፣
28፥16፤ ዘዳ 16፥1-2፤ ኢያ 5፥10፤ 2ኛ ነገ 23፥21-23፤ 2ኛ ዜና 30፥1፣5፣ 35፥1፣18-19፤ ማቴ 26፥2፤
ሉቃ 22፥15፤ ዮሐ 6፥4፤ 11፥55/።
ይህ “የበጉ የደሙ ምልክት የእግዚአብሔር ፋሲካ ነውና በዓል
አድርጉ” የሚለው ቃል በወቅቱ ለእስራኤል ዘ ሥጋ ነበር።
ያ የበጉ የደም ምልክትና ፋሲካው ለአማናዊው፥ ለመድኃኒታችን፣ ለዓለም ቤዛ ለኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌው ነው።
* ፋሲካና
እስራኤል ዘ ነፍስ፡-
በዕብራይስጥ ፋሲካ ‹‹ፓሳሕ›› ይባላል በዘጸ 12 እንደምናነበው
የእስራኤል ልጆች ፋሲካን ያዘጋጁት አስረኛ መቅሠፍት ሁኖ በታዘዘው ሞተ-በኩር በግብፃውያ ላይ ሲያልፍ እነሱንም የሞት መልአክ እንዳይቀጣቸው
ሞት እንዲያልፋቸው የፋሲካውን በግ አርደው ያከበሩት የእግዚአብሔር
በዓል ነው። ፋሲካን ያከበሩት ከነጻነት በፊት ሲሆን ለሁለት ዓላማ ነበር ያከበሩት፡-
1. ከእግዚአብሔ
ርፍርድ ለመዳን፣
2. ሊያጠፋ ከመጣው አጥፊ መልአከ ሞት ለመዳን ነበር።
1. በዓሉንም ከነጻነት በኋላ በየዓመቱ በአሥራ አራተኛው ቀን ያከብሩት ነበር። /ዘጸ16፥6፤ ዘጸ 12፥1-3/ ከዚያም እስከ አንድ ሳምንት ድረስ የቦካውን ነገር ለመብላት ስላልተፈቀደላቸው
አንድ ሳምንትም የቂጣ በዓል ያከብራሉ። ያልቦካ መብላት የእስራኤልን
በችኮላ ከባርነት መላቀቅ ያመላክት ነበር።
2. ከኃጢአት ኑሮ የመላቀቅ፣ ከባርነት ኑሮ የመለየት ምሳሌ ነበር። /ዘጸ 12፥18-34፤ ዘዳግ16፥1-3/ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ሳምንት የፋሲካ ሳምንት ነበር። /ሉቃ 22፥14-16፤ ዮሐ 18፥38-40/ ክርስቶስ ንጹሕ የእግዚአብሔር በግ ኹኖ ደሙን ስላፈሰሰልን
“ፋሲካችን ክርስቶስ” ተባለ። /1ቆሮ 5፥7፤ 1ጴጥ 1፥18-19/ ስለዚህ የክርስቶስ ትንሣኤ በዓለ ፋሲካ ተብሎ ይጠራል። በአጠቃላይ ፋሲካ ማለት መሻገር ማለት ነው። ይህ ዘመን ከሞት ወደ ሕይወት የተሸገርንበት፣
ከሐሳር ወደ ክብር ያለፍንበት፣ ከድካም ወደ ኃይል ያለፍንበት ዘመን ነው።
በትንሣኤ ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን የምንወርስበትን፥ ሞተ ፈርዖን የተሻረበረት፥
የዲያብሎስ ግብፃውያን የበኩር ልጆቹ በሞት፣ በኀዘን፣ በልቅሶ፣ በትካዜ፣ በድካም፤ በመቃብር የተቀጡበት ዘመን ነው። እስራኤል ዘ ነፍስ፥ ምእመናን ወደ ከነዓን መንግሥተ ሰማያት ያለፉበት፣ ቀይ ባሕር ኃጢአት በክርስቶስ የተከፈለበት፣ ከመና ይልቅ የከነዓን ፍሬ ተመገቡ
ብሎ እንደተፃፈው ከፍየሎችና ከበግ
ደም ይልቅ፥ ከአማናዊት ከድንግል ዘር የተዋሕደ፤ በሕያው ቃሉ፦ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ ,,,
እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው” ብሎ ሥጋ ወደሙን እንድንበላ አዘዘን። /ኢያ 5፥12፤ ማቴ
26፥26፤ ዮሐ 6፥35፣48፤ ዕብ 9፥12/
ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፦
“በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ
እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።” /1ኛ ዮሐ 4፥9/ ፍቅር የሆነው ወልደ ክርስቶስ ከሰማይ ለምእመናን የወረደበት፣ ጥል የወደቀበት፣ ዓምደ ብርሃን ክርስቶስ በሕዝቡ መካከል እያበራ፣ የሕዝብ ብርሃን ኹኖ የሚገለጥበት፤ አንድ መንጋ በአንድ እረኛ የሚመራበት ዘመን ነው። /ዮሐ 10፥16/ በዚህ የፋሲካ ወቅት የምናከብረው፥ ከሞት ወደ ሕይወት የተሸገረንበትን፣ ፋሲካችንን ክርስቶን ነው!። ከሞት ወደ ሕይወት አልፈንበታልና። ሞትን ተሸግረንበታል፣
ፍርድን አሸንፈንበታልና “እውነት እውነት እላችኋለሁ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ ከሞትወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም” /ዮሐ5፥24/ ብሎ እንዳስተማረን፤ ክርስቶስ ፋሲካችንም ማእዶታችንም ነው።
ማጠቃለያ፦ ዛሬ ውጊያችን ከሥጋና ከደም ጋር አይደለም፤ ይልቅ ከእርኩሳት መናፍስ ኃይሎች እንጂ! ሥጋንም
የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ። እንደ
እግዚአብሔር ቃል መሠረት ክርስቲያኖች ሊኖሩበት የተገባ ሕያው የሕይወት መንገድ መከተልነው።
ይኸ፥ ሕያው የሕይወት መንገድ ደግሞ ስንኖር፦ አህዛብና የዓለም ሥጋውያን መሪዎች፥ በክርስቲያኖች
ላይ ያደረሱትና እያደረሱ ያሉትን፣ ለወደፊቱም ለሚወስዱት የተዛባ ፍርድ፣ የሐሰት ክስ፣ ማሸማቀቅና መድልዎ፣ እንግልትና ስቃይ፣
ማሳደድና ከቀዬ ማባረር፣ ወደ እስር ቤት (ወኅኒ ቤት) ማጋዝና ማሰር፣ መደብደብና መግደል፤ በዚኸ ብቻ አያበቃም ቅዱሳት
መፅሐፍትን ማስተማር ወንጀል እስከሚሆን፣ በሕጋቸው የወንጀለኛ መውጫ ሕግ በማበጀት፣ ያሻቸውን ሊያደርጉ ይችላሉ። ለዚህም ማሳያ
ግብረ-ሰዶዊነትን)
ይኸም አህዛብና የዓለም ሥጋውያን መሪዎች፥ የሐሳባቸውን እንዳሳኩ መፅሐፍ ቅዱስ
ይመሰክራል፦ “ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ
ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ።” /ማቴ 23፥35/ ብሎ ደም ያፈሰሱ እንደነበሩና በድጋሚም ደም እንደሚያፈሱ ሲያመላክታቸው በዚህ
ሐይለ ቃል እንረዳለን ማለት ነው!። “ሥጋንም የሚገድሉትን
ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።” /ማቴ 12፥28፤
ሉቃ 12፥4/
ሠዎችን ማረድና መግደል አምላክ ማገልገል እስኪመስላቸው ድረስ፦ “ከምኵራባቸው
ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። ይህንም
የሚያደርጉባችሁ አብንና እኔን ስላላወቁ ነው።” /ዮሐ 16፥2-3/ ሲል ልዑለ ባህሪ ወልደ እግዚአብሔር ወልደ ማርያም ኢየሱስ
ክርስቶስ በአማናዊ ቃሉ ነግሮናል።እንዴት ቢሉ፥ ሲነገራቸው የነበረውን ቃል አላገናዘቡም ነበርና ክርስቶስን ደሙን እስከ
ማፍሰስና እስከ መስቀል ድረስም የደረሱትም ለዚህ ነበር። ከክርስቶስም ሞትና ትንሣኤ እንዲሁም ዕርገት በኋላም እንኳን
በክርስቶስ ሐዋርያት ተብለው የተጠሩት በኋላም ሐዋርያት ተሰባስበ እራሳቸውን በአንፆኪያ ክርስቲያን ብለው ከመጥራታቸው በፊትም
ይኹን ከጠሩም ማግስት ጀምሮ እንግልቱና ስቃይ ከባድ ነበር። ከመክበድም በላይ የከባድም ከባድ የሆነው አሳሳቢ ነገር “በስሙ
ምንም ዓይነት” ቃል ትንፍሽ እንዳይሉና እንዳይናገሩ ይደረጉ ነበር። ዛሬስ፥ ስሙ ይነገራል ግን ግብረ-ሰዶማዊነትን በክርስትና
ላይ ለመጫን ይጥራሉ! አልያም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጥስ ያሉትን ግብረ-ሰዶማዊነትን የሚያወግዙ ይቆነፃፅላሉ፣ ለራሳቸውም
ቤተ-እግዚአብሔር እስከ ሟቋቋምም ይጥራሉ (ይኼንን በሌሎች ሠለጠኑ ያልናቸው ሃገራት ሲያራምዱ አይተናል)።
በዚህም አላበቃም፥ ክርስቲያኖችን ማሳደድና ድራሻቸውን ማጥፋት የዘመኑ የንጉሡ ትህዛዝና
የረበናት ካህናት ፍላጎትና ምኞት ቢሆንም ግን ክርስትናን ሊያስቆሙትና ድራሹን ሊያጠፉት ይቅርና እንደውም ምስማር በደምብ
ሲመታና ሲደበደብ እንደሚጠብቀው ሁሉ፤ ክርስቲያኖችም፥ እንግልቱና ከቀዬያቸው መባረራቸው፣ መታሰራቸውና መደብደባቸው፤ ይብለጥ
ክርስትናን በፈተናቸው ባለው ጥንካሬያቸው ዓለምን በጦርና በሰይፍ ሳይኾን በቃላቸው ባለው በክርስቶስ ፍቅር ሊማርኩና ለክርስቶስ
ፍቅር እራሳቸውን እንዲያንፁ ተግተው ከማስተማርና ቃሉን በመመስከር ብቻ ይኼው አሁን ላለንበት ዘመን ክርስትናችን ጉልህ ሚናና
ለሕይወታችን ሕይወታቸውን የገበሩና ደማቸውን ያፈሰሱ ሰማዕታት ብዙዎች አሉ!።
ከእነዚህ መከከል አሳዳጅና አንገላች፣ ለዘመኑ ለነበረው ንጉስና ለረበናት ካህናት ቀናኢ
የሆነ ሳዖል የሚሉትን በመፅሐፍ ቅዱስ እናገኛለን። ይኽ ሳዖል የሚሉት፥ ሐዋርያትን ከያሉበት እየጠቆ መና እያስያዘ፣ ወደ
ግዞትና ለግርፋት እንዲሁሙ ለሞት የሚያበቃ የሐሰት ክሦችን በመዶለት የሚተጋ ነበር። ቢሆንም ግን “የመውጊያውን ብረት”ን መቃወሙን
አላወቀም ነበር። በዚህም የተነሳ ሐዋርያትና ህዝበ ክርስቲያኑን በማሳደዱ ብቻ “አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤
የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል” /ሐዋ 9፥15/
ብሎታል።
መድኃኒታችን፣ መድኅነ ዓለም ቤዛ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፦ የሳውል ዓይነ ሥጋውን ገፍፎ፣ ዓይነ
ሕሊናውንና ሕዝነ ልቦናውን ከከፈተለት ወዲያ፤ ስለክርስቶስ ፍቅርና በክርስቶስ ኃይል፦ ከአሳዳጅነት ወደ ተሳዳጅነት፣ ቃሉን
ከናጣመምና ከመግፋት ይልቅ ስለቃሉ እውነቱን በመመስከር፣ ከገዳይነት ወደ ተገዳይነት፣ ሕይወቱን በሙሉ ስለ ክርስትና ተጋድሎና
ሕይወት በመመስከር፤ ከመውጊያውን ብረት እንዳልተቃወመና ይልቅስ "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው!"
መኾኑን በማመንና በመገንዘቡ ምክንያት ለክርስትና ተጋድሎ በቃ!።
እውነት ነው፥ "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው!"
የሚዋጉንን ተገዳዳሪዎቻችንን፦ በጦርና በመሣሪያ፣ በፈረስና በብርቱ በጠንካራ ሠራዊት፤ አይዋጋቸውም፣ በፍቅሩ ይጠራችዋል እንጂ! እናስብ፣ እናስታውሳቸው፦ እነ ቅዱስ ሳውል (ቅዱስ ጳውሎስ) በክርስቶስ ፍቅሩ
ተማረከ እንጂ በጦርና በመሣሪያ እንዳልኾነ፣
ቅዱስ እስጢፋኖስም ሲዎግሩትና ሲደበድቡት በአርምሞና በመንፈሳዊ ፅናቱ የሰማውና ያየውን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ነበር እስከ ሚሞት
ድረስ ፍቅራዊ በኾነ ቃል እንጂ ሰይፍና ጎመዱን እንዳልመዘዘ ልብ እንበል!።
በጉ ታረደና ቅዱስ ሥጋው ተቀበረ፣
ኃይል ስናገኝ ዲያቢሎስ እጅግ አፈረ።
በመውጊያው በትር በክርስቶስ፣
ስሙ ተቀየረ ኾነ ቅዱስ ጳውሎስ፣
መንፈሳዊ ፅናት እንድንላበስ፣
እንማር ከቅዱስ እስጢፋኖስ።
ከቅዱስ ያሬድ ጥቅስ፤ ከጡዕም ዝማሬው፦
በግእዝ፡- ‹‹ፋሲካ ዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲ (አዝ) ዛቲ ዕለት ንትፈሣሕ በቲ (አዝ) ዛቲ ዕለት ናሕይ ወዕረፍት (አዝ) ሰማይ ወምድር ይትፌሥሑ ባቲ (አዝ) ፋሲካ..... ተዝካረ ትንሣኤሁ ለመድኃኒነ››።
አማርኛ፡- ይህች የፋሲካ ዕለት ቅድስት ናት (አዝ) በዚህ ዕለት እደሰትባት (አዝ) ሐሤት እናድርግባት (አዝ) ይህች ዕለት ዕረፍት ጸጥታ ናት (አዝ) ሰማይና ምድር በሷ ደስ ይላቸዋል (አዝ) ፋሲካ ፋሲካ ፋሲካ የሙድኃኒታችን ትንሣኤ መታሰቢያ።
በግእዝ፡-ንጉሠ ዓለም መንሥኤ ሙታን ተንሥአ በሣልስት ዕለት ሰንበተ ክርስቲን ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን።
አማርኛ፡- የዓለም ንጉሥ የሙታን ትንሣኤ ክርስቶ በሦስተኛው ዕለት ተነሣ፥ በሰንበተ ክርስቲያን ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ (አርባዕት)
በግእዝ፡- ንግበር በዓለ በትፍሥሕት ቅድስተ ፋሲካ በሐሤት እስመ ለስሐ ሕምዙ ለሞት ወተቀጥቀጠ አርዑተ ኃጢአት።
አማርኛ፡- በደስታና በሐሤት የቅድስት ፋሲካን በዓል እናክብር የሞት መርዝ ተሸሮአልና የኃጢአት ቀንበር ተቀጥቅጧልና።
በግዕዝ፡- ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት ወሰበረ ኆኃተ ብርት እግዚኦ ለሰንበት ሲኦለ ወሪዶ በነደ እሳት ተቤዘወሙ ለቀደምት።
አማርኛ፡- ትንሣኤውን በሰንበት አደረገ፤ የሰንበት ጌታ የብረት በሮችን ሰበረ፥ ሲኦል ወርዶ በነደ እሳት የነበሩትን የቀደሙትን አባቶች ተቤዣቸው።
ስብሐት ለእግዚአብሔር ወድንግል ማርያም ክብር! የቅዱስን ረድኤት በረከት ይደርብን፤ አሜን!
<<ይቆየን>>
No comments:
Post a Comment