ከፍሪሳዊ ወገን፥ የአይሁድ አልቃ የሆነው፤
ከሕገ ልቦና እስከ ሕገ ኦሪት የተማረው።
ኒቆዲሞስ የሌሊቱ ተማሪ፤
ሕጉን ሥርዓቱን አክባሪ፤
በሙኩራብ ቃሉን መስካሪ፤
ቅዱሳት መፅሐፍትን መርማሪ።
የሌሊቱ ተማሪ፥ ምጡቅ ዕውቅት ቢኖረው፤
ያላወቀውና ያለተረዳው፥ ጉድለት ነበረው፤
ስለዚህ፥ የሃይማኖቱን ጉድለቱን ሊሞላው፤
ለሕሊናው እረፍት መላ ፈለጎ አገኘው።
እያሰላሰለ፥ በሌሊቱ ጨልማ፤
ለነፍሱ
ጥማት ቃሉን ሊስማ፤
ይኼድ
ነበር ወደ ቃሉ አውድማ፤
ቀረበ፥ ኢየሱስም
ድምፁን አሰማ።
ሠው፥ ዳግምኛ
ከውኃና ከመንፈስ፤
ይወለድ አለ የእኛ አምላክ ኢየሱስ።
የሠውን ሠውነት፥ የተዋሕደው፤
ለዓለም ኹሉ መድኃኒት የኾነው፤
ለኒቆዲሞስ ምስጢረ ጥምቀት የነገረው፤
የድንግል ዘር፥ ኢየሱስ ክርስቶስ
ነው!።
ሠው ዳግምኛ እንዲወለድ፥ ከውኃና ከመንፈስ፤
ነገረው በአማናዊ ቃሉ ለሌሊቱ ተማሪ ለኒቆዲሞስ።
(ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወድንግል ማርያም ክብር!)
No comments:
Post a Comment