* ያልሰገደ
ትውልድ ራዕይ የለውም! ለሚሰግዱ ሠዎች፥ እግዚአብሔር መንገድ አለው።
የጸሎት ሥነ-ሥርዓት፦
፩ኛ፤ በመንፈቀ
ሌሊት
፪ኛ፤ በነግህ
ጊዜ ፲፩ ሠዓት (5:00 AM በፈረንጆች) ዌዳሴ ማርያም፣ ሰይፈ መለኮት፣ ሠይፈ ሥላሴ ወይም ከቅዱሳን አንዱ፤
፫ኛ፤ በ፫ ሠዓት (9:00 AM በፈረንጆች) አርጋኖን፣ መልክአ ገብርኤል፤
፬ኛ፤ በ፮ ሠዓት (12:00 PM በፈረንጆች) መልክአ ስላሴ፣ መልክአ ሚካኤል፤
፭ኛ፤ በ፱ ሠዓት (3:00 PM በፈረንጆች) መልክአ መድኃኒዓለም፣ መልከአ ኡራኤል፤
፫ኛ፤ በ፫ ሠዓት (9:00 AM በፈረንጆች) አርጋኖን፣ መልክአ ገብርኤል፤
፬ኛ፤ በ፮ ሠዓት (12:00 PM በፈረንጆች) መልክአ ስላሴ፣ መልክአ ሚካኤል፤
፭ኛ፤ በ፱ ሠዓት (3:00 PM በፈረንጆች) መልክአ መድኃኒዓለም፣ መልከአ ኡራኤል፤
፮ኛ፤ በ፲፩
ሠዓት
፯ኛ፤ ማታ ከመኝታ በፊት በ፫ ሠዓት (9:00 PM በፈረንጆች) መልክአ ሩፋኤል፣ አርጋኖን፤
፯ኛ፤ ማታ ከመኝታ በፊት በ፫ ሠዓት (9:00 PM በፈረንጆች) መልክአ ሩፋኤል፣ አርጋኖን፤
በተጨማሪ፦ በነዚህም በሰባቱ የጸሎት ጊዜያት፥ እግዚኦታ ፲፪ ጊዜ፣ በእንተ ማርያም ፲፪ ጊዜ፣ ኦ አምላክ ፲፪ ጊዜ፣ ኦ
ክርስቶስ ፲፪ ጊዜ፣ ያድኅነነ እመዓቱ ፲፪ ጊዜ፣ ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከን ፲፪ ጊዜ፤ ማድረስና ከቀዳሚትና ከእሑድ
እንዲሁም ከታላላቅ በዓላቶችና ሥጋ ወደሙ ከተቀበሉበት ዕለት በስተቀር ሰባት ሰባት ጊዜ መስገድ ይገባል።
ልዩ ማሳሰቢያ፦
ሥራና ጸሎት ጐን ለጐን የሚጓዙ (በሥራ መስክም እያሉ ጸሎትን አብሮ ማዋሕድ ስለሚችሉ) ስለሆነ፤ የሥራን ሠዓት ሳይሻሙ እግዚአብሔርን
በአጭር ጸሎት አነጋግሮ (ጸልዮ) ወደ ሥራ መሰማራት ይቻላል።
በ፮ ሠዓት
ጸሎት (12:00 PM በፈረንጆች) መልከአ ሚካኤል ማንበብ፦* ቅዱስ ሚካኤል ሆይ እርዳኝ፣ የአጋንንትን ኃይል ገስፅልኝ፣ ርኩሳን መናፍስትን አስወግድልኝ፣ ታላቅ የኾነውን ቅዱስ የኾነው ሰይፍህን በክፉ መናፍስት ላይ ጣለው፣ ቆራርጠው፣ የበረከትህን ተስፋና ኃይል ለእኔም ስጠኝ፣ ከጎኔ ተሰለፍ፣ ኃይሌን አጠናክር፣ ውስጣዊ ሕይወቴን በመንፈስህና በፀጋህ አስበኝ፣ በምስጋና ስፍራ ኹሉ፤ በጸሎትህ እርዳኝ። አባታችን ሆይ ........
የዘወትር የአምልኮ ስግደት፦ (መቅረት የሌለበት)
* ለአብ እሰግዳለሁ፣ ለወልድ እሰግዳለሁ፣ ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ፣ ምስጋና ይሁን ለአብ፣ ምስጋና ይሁን ለወልድ፣ ምስጋና ይሁን ለመንፈስ ቅዱስ፣ በረከቱን ለሰጠን፣ ኃይሉን ላበዛልን፣ በዚህ ሠዓት ላቆመን፣ በቸርነቱ መንገድ ለመራን፣ በዚህ ሠዓት በፀጋ ለጠበቀን፣ በብርሃኑ ኃይል ለመራኸን፣ ላንተ፥ ክብር ምስጋና ይግባኽ፤ ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ፤ ቅዱስ እግዚአብሔር፣ ቅዱስ ኃያል፣ ቅዱስ ሕያው፣ ቅዱስ ኤልሻዳይ፣ ቅዱስ አዶናይ፣ ቅዱስ ያህዌ፣ ቅዱስ ጸባኦት፣ ቅዱስ ኢየሱስ፣ ቅዱስ ክርስቶስ፣ ቅዱስ አማኑኤል፣ የድንግል ማርያም ልጅ፤ ክብር ምስጋና ይግባው!።
የንስሐ ስግደት፦

* ኪርያ ላይሶን ኢየሱስ፣ ኪርያ ላይሶን ክርስቶስ፣
ኪርያ ላይሶን አማኑኤል፣ አቤቱ ክርስቶስ ሆይ ማረን፣ አቤቱ አምላክ ሆይ ማረን፣ አቤቱ መድኃኒዓለም ሆይ ማረን፣ አቤቱ የድንግል ማርያም ልጅ ሆይ ማረን!።
ክብረ በዓል ከሆነ፦
* ስብሐት ለአብ፣ ስብሐት ለወልድ፣ ስብአት ለመንፈስ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር፣ ቅዱስ ኃያል፣ ቅዱስ ሕያው፤
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ።
የክብር ስግደት፦
ክብረ በዓል ከሆነ፦
* ስብሐት ለአብ፣ ስብሐት ለወልድ፣ ስብአት ለመንፈስ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር፣ ቅዱስ ኃያል፣ ቅዱስ ሕያው፤
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ።
የክብር ስግደት፦
* ለቅዱስ ሚካኤል እሰግዳለሁ፣
በቅዱስ ሚካኤል እሰግዳለሁ።
የፀጋ ስግደት፦
* ለድንግል ማርያምም እሰግዳለሁ፣ ክብር ምስጋና ይገባሻል።
የፀጋ ስግደት፦
* ለድንግል ማርያምም እሰግዳለሁ፣ ክብር ምስጋና ይገባሻል።
ምልክት ሲሰጥ፥ በተባረከ መቁጠርያ እየቀጠቀጡ የሚባለው፦
እግዚኦ ማርና ክርስቶስ፣ በእንተ ማርያም ማህርነ ክርስቶስ፣ ኪርያ ላይሶን ኢየሱስ፣ ኪርያ ላይሶን ክርስቶስ፣ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም፣ የዲያቢሎስን ሰራዊት በሰበረው በኃያሉ በቅዱስ ሚካኤል ስም፣ ለቅድስት ድንግል ማርያም ብሥራትን ባበሰረው በቅዱስ ገብርኤል ስም፣ ውስጤ የተደበቀኸው ጠላቴ፥ ነርቭ የኾንኸው፣ በሽታ የሆንኸው፣ ቅዠት የሆንኸው፣ ተሥፋ መቁረጥ የሆንኸው መንፈስ እገስፅሃለው፣ በገንዘቤ ላይ፣ በባሕሪዬ ላይ አዛዥ አትኾንም፣ ይኽ መንገድህ፥ ተሽሯል፣ ተሰርዟል፤
በድንግል ማርያም ስም ወደ ግባር ውጣና ታሰር።
የጸሎት ቦታ ማዘጋጀት፦ በምስራቅ
አቅጣጫው፥ በፀሐይ መውጫ ይኹን።
የፀሎት ቦታው በቁመት፦ የመድኃኒዓለም እና የቅድስት ሥላሴ ስዕል (ተባርኮና ቅባ ቅዱስ ተቀብቶ) በንብርክክ፦ የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል፣ የእመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም፣ የቅዱስ ሚካኤል ቅዱሳት ስዕላት (ተባርኮና ቅባ ቅዱስ ተቀብቶ) መፀለይና መስገድ እፎይታን ያጎናፅፋል። ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ ንስሐ መግባት፣ ቅዱስ ቁርባን መውሠድ፣ አስራት በኩራት መስጠት፣ የበረከት ሥራ መሥራት፤ የዘወትር ክርስቲያናዊ ተግባራችን ይኹን!።
ማታ፥ ሰግዶ፣
ፀልዮ፣ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና አድርሶ የሚተኛ ከኾነ፤ ኢንዱስትሪ፣ ሃብት፣ ገንዘብ፣ ዶላር የማይሰጠውን ሠላም፤ አግኝቶ በሠላም
ይተኛል። ይኼንን መሞከር ነው! ብዙ የሞከሩ ክርስቲያኖ እፎይ ብለዋል!።
No comments:
Post a Comment