ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፥ የዓለም መድኃኒት፣
ተወልዶ፥ ከድንግል ማርያም ቅድስት፣
ፍቅሩን ሲገልፅላት፥ እነሆ፦ እናቴ አላት፣
እኛም እንበላት፥ በክርስቶስ ፍቅር እናታችን ናት።
ክርስትና፥ ኦርቶዶክ ዘ ተዋሕዶ ነች፣
የቅዱሳኑን ስማቸው፥ ታከብራለች፣
ከክርስቶስ ስርዓት፥ ያልበረዘች፣
ሁሉን ነገሯን፥ ስለ እርሱ ያደረገች።
መጥምቁ ዮሐንስ፥ ክርስቶስን ሲሰብከው፣
የዓለም በግ፥ መድኅነ ኢየሱስ ነው ሲለው፣
አይሁድ ፈሪሳዊያን፥ ለካስ ሞኞች ናቸው፣
አፍጥነው ለመስቀል፥ እቅድ አዘጋጅተው።
በተንኮልና በሐሰት ተመካክረው ዋሉ፣
ሁከት እንዳይነሣ
በበዓል አይሁን አሉ።
ዕረቡ፥ የከንቱ ከንቱ ምክር ተፀነሰ፣
ቀኑ ጸጥ ብላ ዋለች ዕለት ሐሙስ፣
በዚች ሌሊት ተያዘ የዓለም ንጉስ፣
ዓለሙን በደሙ ሊያነፃ ክርስቶስ።
ጴጥሮስም ሰይፍ ቢመዝው፣
የመፅሐፍት ቃል እንዲፈፅመው፣
ሰይፍፉን እንዲመልስ
አመላከተው።
ወደ ይሁዳ የፍቅር ዓይኖቹን፣
ለካህናት አለቆች ውብ እጆቹን።
ራሱን አሳልፎ ሰጠ
ስለ ፍቅሩ፣
እንዲፈፀም የቃሉ ምስጢሩ።
እንስቀለው አሉ፥ ወንበዴውን ሊያስፈቱ፣
ጮኦትና እሪታ እያሰሙ፥ እስከ ለሊቱ፣
ከንጉሳቸው ዘንድ ቀረቡና ከዙፋኑ
ፊቱ፣
ይለቀቅ፥ ይለቅቅ! እያሉ በርባን ከእስራቱ።
ተሳካና፥ አሉ የታለ ያ
የዓለም በግነቱ፣
ምግብ የሚሆነው፥ ብለው ሲዘባበቱ፣
አላስተዋሉምና ሥጋውን ሊበሉ፥ ተዘባበቱ፣
ጌታን ለመስቀል፥ እርስ በርሳቸው እየዶለቱ።
በይሁዳ ልቦና፥
ተንኮል ተፀነሰሰና፣
በምክረ ሠይጣን፥ ልቦናው ሸፈተና፣
ክርስቶስ ሞተ፥ ለዓለም ተሰቀለና፣
ሞትን
ድል ነሳው፥ ሕያው ጌታ ነውና።
ክርስትና፥ በብዙ መስቀለና እንግልት እያለፈች፣
በመከራ አፋፍ ብትሆን እንኳን፥ እየጸናች፣
ኑ ከበጉ ማዕድ፥ ተመገቡ ጠጡ እያለች፣
የክርስቶስን፥ ሥጋ ወደሙ ትመግባለች።
ክርስትና፥ ኦርቶዶክ ዘ ተዋሕዶ ነች፣
የቅዱሳኑን፥ ስማቸው ታከብራለች፣
ለጴጥሮስ ቃል የገባለትን፥ ታስታውሳለች፣
በስማቸውም፥ ቤተ-ክርሰቲያን ትመሰርታለች።
የዓለም በግ፥ መድኅነ ኢየሱስ፣
እንድንጠመቅ
ከውኃና ከመንፈስ፣ ʼ
ልጁ እንድንሆን በመንፈስ ቅዱስ፣
ታትመናል፥ በደሙ
በክርስቶስ!።
------------------------------------------------------------------
(ማሳሰቢያ፦ ሥነ-ግጥሙን፥ ገንዘብ ለማግኛ እንዳይጠቀሙበት በእግዚአበሔር ስም አደራ እላለሁ፣ ይህን
ሥነ-ግጥሙን ከወደዳችሁት በማንኛውም መንገድ ለሕዝበ ክርስቲያንን ሊጠቅም በሚችል መንገድ ማንሸራሸር፤ ትችላላቹ። እግዚአበሔር
ይስጥልኝ አመሰግናለሁ! በከንቱ የተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ። /ማቴ 10፥ 8/ ይላልና ወንጌሉ!)
-----------------------------------------------------------------
No comments:
Post a Comment