ፍቅሬ ሆይ፥ ቀኑን ሙሉ ሳስብሽ እውላለሁ፤
እንቅልፍ እየነሳኝ ... ሌሊት ሌሊት እባንናለሁ።
ፊቴን ... ሽቅብ ወደ ላይ አንጋጥቼ፤
ዓይኖቼን ... ወደ ሠማዩ አንስቼ፤
ጨረቃዋን ... አትኩሬ ተመልክቼ።
የኮከቦች ድምቀት ... በድቅድቅ ጨለማ፤
ከአድማስ አድማስ ... መድረሷማ፤
ብልጭ ድርግም ... ማለቷማ፤
ልዩ ናት አቀማመጧ ... ጨረቃ ውበቷማ።
ጎህ ሲቀድ ... ጨረቃዋ ስትርቅ፤
የሌሊቱን ቅዝቃዜ ... ለማራቅ፤
ቀረበች ፀሐይ ... ምድርን ለማሸብረቅ፤
ዓለምን ... በብርሃኗ ለማሞቅ።
በጨረቃዋ ፍንጣቂ ... ፍቅሬን እንዳያዋት፤
ከሌሊቱ ይልቅ ... ወዳጄን እጅግ ፈለኳት፤
በፀሐይ ጮራ ውስጥ ... በጧት ፍካት፤
ፊቴ በብርሃን ተሞላ ... ፍቅሬን ስላየዋት።
ጨረቃ፥ ለፀሐይ ቦታዋን ... እንደለቀቀች፤
ፍቅሬን በማየቴ ... ልቤ ሐሴት ተሞላች።
ፍቅሬ ሆይ፥ ... ቀኑን ሙሉ ሳስብሽ እውላለሁኝ፤
እንቅልፍ እየነሳኝ ... ሌሊት ሌሊት እባንናለሁኝ።
የኔ ፍቅር፥ ... እወድሻለሁ፣ አፈቅርሻለሁኝ፤
ይህቺን ሌሊት .. ልደግማት እናፍቃለሁኝ።
ከሥንታየሁ
ጌታቸው (ታኅሣስ ፲፩/ ፪፻፮ ዓ/ም)
እግዚአብሂር ከፍ ከፍ ያድርጋችሁ ይህን ትምህርት የምትሰጡ ሰወች ያበርታችሁ!!!
ReplyDelete