Wednesday, December 11, 2013

አንደበተ ርቱዕ፥ አባ ፍስሐ



       ከደብረ ሊባኖስ ወደ አብተ ማርያም ገዳም ለመድረስ በእግር ጉዞ መሄድ ግድ ይላል። የመድረሻ ሰዓት፥ እንደ እግር ተገዦች (እንደሰዎች) ፍጥነት ይለያያል። እኛ ግን ወደ አንድ ሰዓት ከአርባ ደቂቃ አካባቢ ፈጅቶብን ደረስን።

በዛም፥ በአብተ ማርያም ገዳም አካባቢ ከሚኖሩ አበው ዘንድ ጎራ በማለት አባ ፍስሐ አገኘናቸው። እርሳቸው በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የበቁ አባት ናቸው። አባ ፍስሐ፥ ምክራቸው፣ ተግሳፃቸው፣ ትምህርታቸው፤ እጅግ እጹብ ድንቅ ነው።

ከአንደበታቸው በሚወጣው ፍጹም መንፈሳዊ ምግብ፦ ነፍስህ ሐሴት ስታደርግ ታስተውላለህ፣ ሕይወት ትማረካለች፤ ተመስጧቸው፥ ህሊናን ወደ መንፈሳዊ ተመስጦ ውስጥ ይመራዋል፣ በመንፈሳዊ ተጋድሎዋቸው የሕይወታቸው ምርኮኛ እንድትሆን አንዳች የመንፈስ ቅዱስ ምሪት ያነሳሳሃል። እድሜያቸውን በሙሉ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የገበሩ አባት ናቸው።



አባታች አባ ፍስሐም፥ እንዲህ አሉን፦ ልጆቼ ሆይ፥ የምነግራቹ ብዙ ነገር ቢኖረኝም፣ ጀንበሩ ሳይዘቀዝቅ (ሳይጨልም) ወደመጣቹበት ትመለሱ ዘንድ ጥቂት ነገር ብቻ ላጫውታቹ አሉን። እኛም ከአባታች፥ የሚወጣውን መንፈሳዊ የገበታ ምግብ* ለመብላትና ለመጠጣት፤ እንዲሁም ለማዳመጥ፥ ህሊናችንና ልቦናችንን፣ ጆሮዎቻችንና መላ አእምሮዎቻችንን ለእርሳቸው ዝግጁ በማድረግ፤ በሰሌን ላይ ቁጭ፣ ቁጭ አልን።

አንደበተ ርቱዕ፥ አባ ፍስሐም አንደበታቸውን በመክፈት፣ ፈጣሪንና የፈጣሪ አገልጋዮችን፣ ለማመስገን ተሰናዱ፤ ስለ ቅድት ማርያም፣ ስለ ቅዱሳን መልአክት፣ ሠዎችን ስለ ማማት፤ እንዲህም እያሉን አወጉን።
 

   ስለ ቅድት ማርያም
ሾላ ሾላዬ ... ሾላ ሾላዬ፤
ፍሬውን በልቼው ... ዛፉ ከለላዬ፤
እመቤቴ ማርያም ... ስምሽ ያምር፤ 
በፍየል ብራና ... በቄስ ከናፍር።

ከሁሉም ከሁሉም ... ማርያምን ውደዱ
እርሷ ያለችበት ... ቅርብ ነው መንገዱ።

ሳሊለነ ቅድስት ... ይሉሻል ደብተራ፤ (2) 
ሰውሪን ብሎ ... ከክፉ መከራ፤ 

ኧረ፥ ንኢ ንኢ ... ንኢ በሰሌዳ
ግሸን ላይ ያለሽው ... ምስከ ፍቅር-ወልዳ።

     እልልል,,,, እልልል,,,, እልልል,,,,


          ስለ ቅዱሳን መልአክት 
   ሚካኤል በክንፉ ... ገብርኤል በአክናፉ፤(2)
    ይውላሉ፥ ያድራሉ ... እኛን ሲደግፉ።

          ደህና ውሎ (2) .. ደህና ካነጋው፤ 
          ተመስገን ብቻ ነው ... የአንድዬ ዋጋው፤ 
          የእግዚአብሔ ... ዋጋው።


   ሠዎችን ስለ ማማት
 ይህ ጊዜ ... ይህ ወራት፤(2)
ነገርን ከሆድ ... አለማውጣት

ሠውን ተናግሮ ... ከመጨነቅ፤(2)
ከኮረጀ ... አፏን እንቅ።

ከአንደበተ ርቱዕ፥ ከአባ ፍስሐም አንደበት። (መስከረም /፳፻፭ /)

* (መንፈሳዊ የእግዚአብሔር ቃል

No comments:

Post a Comment