በዲ/ን ዳንኤል ክብረት ስለ አባታችን ጻድቅ "አቡነ ተክለሃይማኖት ሐዋርያ" በሚል የተሰጠ መንፈሳዊ ትምህርተ ወንጌል፥ አይተው፣ ሰምተውና አዳምጠው፤ ስጋዎትንና ነፍሶትን ይመግቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ተጋብዘዋል።
በዚህ ትምህርት ውስጥ፦
*
በዮዲት ጉዲት፥ የጥፋት ጊዜ፣ ለኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን የሚመጡ የነበሩ የግብፅ ጳጳሳት እንደቀሩና ክርስቲያን አማኞች የጠፉበት ጊዜ፤ እንደነበረ ይገልፅልናል።
*
ዮዲት ጉዲት፥ አርባ ዓመታት ያህል፣ ታላቅ መከራና ከባድ ጥፋት ካደረሰች በኋላ፤ ባደረሰችው የቤተ-ክርስቲያን ብዝበዛ፣ ካህናትና ምዕመናን በጠፉበት ጊዜ፤ ከአንድ ትውልድ ጥፋት በኋላ፤ ፀሐየ ጽድቅ አቡነ ተክለሃይማኖት የተወለዱበትና የተነሱበት ጊዜ፤ ለኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን በጣም አስፈላጊ እንደሆነ፤ ወንድማችን ዳንኤል ክብረት፥ አልምቶና አብራርቶ ያስተምራል።
*
በዚያን ግዜ፥ በመረጃ ያለመኖርና መለዋወጥ በማይቻልበት ወቅት፣ የግብፅ እስላሞች "ጳጳስ ነን" ብለው የመጡበት ጊዜ እንደነበረም ያትታል።
*
በወቅቱ የነበረውን የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ከዛም በኋላ የነበረውን የሃገሪቱን ታሪክና ሁናቴን፣ የቤተ-ክርስቲያን ታሪክ ይተርክልናል።
*
አጠቃላይ፥ ስለ ፀሐየ ጽድቅ አቡነ ተክለሃይማኖት ተጋድሎና ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን በስፋት ያስቃኘናል።
ለወንድማችን
ለዲ/ን ዳንኤል ክብረት፥ እግዚአብሔር አምላክ የአገልግሎቱን ጊዜውን ይባርክለት፤ አሜን!
No comments:
Post a Comment