ህንደኬ፥ የተባለች፣ የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ፣ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ፣ ኢትዮጵያዊ ሰው፤ በነብየ ኢሳያስ የተተነበየውን የመድኃኒታችንና የአምላካችን፣ የኢየሱስ ክርስቶስን፤ የትንቢት ቃሉ ሲያነብ፥ በቅዱስ ፊልጶስም አማካኝነት፣ የቃሉን የትንቢት ምስጢር ከነ-ትርጓሜው የተተረጎመለት፤ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ (አገልጋይ)።
በሙሉ ልቡ፥ ያመነና የተቀበለ፣ የተጠመቀና በእግዚአብሔር ጃንደረቦች (አገልጋዮች) በነብያትና በሐዋርያት ቃል የታነጸ፤ በተመስጦ ባነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ልቡ ደስ ያለው፤ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ (አገልጋይ)። /ኢሳ 53፥4-9፤ ሐዋ 8፥26-40/
No comments:
Post a Comment