Sunday, December 1, 2013

ከጽጌ ስጦታው እና ከመሰሎቹ ተጠበቁ!!!


[ቅ/ሲኖዶስ በተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅነት ካወገዛቸው፤] ከግለሰቦቹ ከአስራ ስድስቱ አንዱ ጽጌ ስጦታው ነው።

 "ሰውን ማስታመም የሚቻለው በምግባር ድክመቱ እንጂ በሃይማኖት ክሕደት አይደለምና!” /ብፁዕ አቡነ አብርሃም የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ለሀ/ስብከታቸው ሰባክያነ ወንጌል እና ምእመናን ይፋ ሲያደርጉ ከተናገሩት/ (ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 9/2004 .ም፤ ጁን 16/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF) የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያንና ለሃይማኖት ጉዳይ በተለይም ለምእመናን አንድነት ቅድሚያ በመስጠት፣ በጉዳዩ ላይ በስፋት በመነጋገር፣ ግንቦት 15 ቀን 2004 .ም፣ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅቶች፣ ግለሰቦች እና መጽሐፎቻቸው ላይ በአንድ ድምፅ ያስተላለፈውን የውግዘት ውሳኔ የያዘው ቃለ ጉባኤ ለመላው አህጉረ ስብከት ተሰራጨ፡፡ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት /ቤት ሰኔ 7 ቀን 2004 .ምሰ ጀምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙ 48 አህጉረ ስብከት ባሰራጨው ቃለ ውግዘት የተካተቱት መናፍቃን ድርጅቶች ሰባት ሲኾኑ የግለሰቦቹ ብዛት ደግሞ 16 ነው፡፡ ከግለሰቦቹ ከአስራ ስድስቱ አንዱ ጽጌ ስጦታው ነው።
 
"ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን። ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።" /1 ዮሐ 218-19/

እነ ጽጌ ስጦታው እና መሰሎቹ፤ የጥበበኞችን ጥበብንከንቱ የሚያድርግ ጌታ፤ ለነብዩ ሲራክ የገለጠለት፦ "ገንዘብህን በከንቱ አትበትን፤ በቃኝም አትበል" /ሲራክ 51/ የሚለውን በመምዘዝና ላልተገባ ትርጎሜ ጠቀሙበት መጽሐፍ ቅዱስን ልብ አለማለታቸ አያስደንቀንም፤ ምክንያቱም ቀድሞኑን "ሐሰተኛ ወንድሞች" ስለሆ ነውና።

                                                                                                  ለ ገንዘብ

መቼም የገንዘብ ነገር ሰሙ፣ ያነቡ፣ መለከቱ፤ አይጣል ነው። ለዚህ እኮ ነው ላልተገባና ለተዘበራረቀ ትርጉም ያዋ!!! "ድምፃዊ ንዋይ ደበበ "ወይ ገንዘብ፥ አወይ ገንዘብ" እየለ ያቀነቀነልን ትዝ ኝ፤ ቢቻል ብጋብዛቸያዳምጡት ይመቻችዋል! ምክንቱም፦ ለ ገንዘ


ወደ ተነሳሁበት ነገሬ ላምራ፤ ገንዘብ፦ ዕቃ መግዢያ፣ መነገጃ፣ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ ነገሮች መለዋወጫ እና ይህን ለመሳሰሉት ለመልካም ምግራት ይውላል። የዛን ያህሉም ደግሞ ገንዘብ የነውርና የኃጢያት ስራዎችን የሚያሰራው ነው። በዚህ ትውልድ አሁን እያየነውም ያለነው ነገሮች ሁሉ ገንዘብ ከፍተኛ ቦታ ይዞ ይገኛል። ነገ ግን እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አረዳድ ከሄድን ግን "ገንዘብ" ኃይለ ቃል፤ ለሌላ ዓላማ ሲውልና ሲገለጽ እናያለን።

እስቲ እንት፦ አምላካችን መድኃኒታችን፣ መድኀነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በምሳሌ ባስተማረበት ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ "አንድ መኰንን ለራሱ መንግሥትን ይዞ ሊመለሰ ወደ ሩቅ አገር ሄደ። አሥር ባሪያዎችንም ጠርቶ አሥር ምናን ሰጣቸውና። እስክመጣ ድረስ ነግዱ አላቸው። የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ነበርና። ይህ በላያችን ሊነግሥ አንወድም ብለው በኋላው መልክተኞችን ላኩ። መንግሥትንም ይዞ በተመለሰ ጊዜ፥ ገንዘብ የሰጣቸውን እነዚህን ባሪያዎች ነግደው ምን ያህል እንዳተረፉ ያውቅ ዘንድ እንዲጠሩለት አዘዘ። የፊተኛውም ደርሶ። ጌታ ሆይ፥ ምናንህ አሥር ምናን አተረፈ አለው። እርሱም፦ መልካም፥ አንተ በጎ ባሪያ፥ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በአሥር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ይሁንልህ አለው። ሁለተኛውም መጥቶ። ጌታ ሆይ፥ ምናንህ አምስት ምናን አተረፈ አለው። ይህንም ደግሞ። አንተም በአምስት ከተማዎች ላይ ሁን አለው። ሌላውም መጥቶ። ጌታ ሆይ፥ በጨርቅ ጠቅልዬ የጠበቅኋት ምናንህ እነሆ፤ ፈርቼሃለሁና፥ ጨካኝ ሰው ስለ ሆንህ፤ ያላኖርኸውን ትወስዳለህ ያልዘራኸውንም ታጭዳለህ አለው። እርሱም፦ አንተ ክፉ ባሪያ፥ አፍህ በተናገረው እፈርድብሃለሁ። እኔ ያላኖርሁትን የምወስድና ያልዘራሁትን የማጭድ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ አወቅህ፤ ምን ነው ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ያልሰጠኸው? እኔም መጥቼ ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር አለው። በዚያም ቆመው የነበሩትን። ምናኑን ውሰዱበት አሥሩ ምናን ላለውም ስጡት አላቸው። እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ አሥር ምናን አለው አሉት። እላችኋለሁ፥ ላለው ሁሉ ይሰጠዋል፥ ከሌለው ግን ያው ያለው ስንኳ ይወሰድበታል። ነገር ግን እነዚያን በላያቸው ልነግሥ ያልወደዱትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው በፊቴም እረዱአቸው።" ሉቃ 1911-26/ ይላል።

እናም ታዲያአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ ከማስተማፊ፤ በነብዩ በሲራክ አንበት የተገለጸውና የተፃፈው አጣቅሶ ማተማ በነና በሐርንፃች የተባለ ፀምንድ ችን አስተማረው።

         ነብዩ ሲራክም፦ "ገንዘብህን በከንቱ አትበትን፤ በቃኝም አትበል" ማለት፦ ከጌታህ የተቀበልከውን የአገልግሎትህ ገንዘብህን (ምናንህን)በከንቱ አትበትነው። በእግዚአብሔር የአገልግሎት ጥሪ ተጠርተህ፥ የመንፈስ ቅዱስ የጸጋው ተካፋይ ከሆንክ በላ፣ የተቀበልከውን ገንዘብህን (ምናንህን) በቃኝ ብለህም፣ በጨርቅ አትጠቅልለው፣ ወደ መሬትም ቆፍረህ አትቅበረው፤ ይልቅስ፥ ጠብቃት፣ ተንከባከባት፣ አትርፍባት፤ ሲል በቃኝም አትበል አለ። /ሲራክ 51/

እስቲ ተመልከቱ ወዳጆቼ፦ የተቀበለቡ ሳይበትነው፥ ተጠቅሞበት፣ ነግዶና አትርፎ፤ ባለቤቱ ሲመጣ፥ ከነ ትርፉ ሲያስረክብ ይከብራል፣ ይመሰገናል፣ ይሞገሳል፤ ይሾማል። እንዲማ ካላደረገማ፥ የእግዚአብሔር ገንዘብ (ምናን)በከንቱ ከበተነ በቃ ሎ ጌታ በጨርቅ ጠቅልሎ የጠበኋት ምናንህ እነሆ፤ ፈርቼሃለሁና፥ ጨካኝ ሰው ስለ ሆንህ፤ ያላኖርኸውን ትወስዳህ ያልዘራኸውንም ስለምታጭድ ብሎ ቢመልስለት፤ ከጌታው ዘንድ መልሱ ምን እንደሚያገኝ በሉቃስ ወንጌል ተመዝግቦ  እናገኝዋለን

እንግዲንድቼ፦ ች በሉቃስ ወንጌል ላይ “ነገር ግን እነዚያን በላያቸው ልነግሥ ያልወደዱትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው በፊቴም እረዱአቸው።" ሉቃ 1926/ የሚለውን ሐረፍተ ነገር በመውድ ላልተገባ ትርጓሜ የሚያውሉም አሉ።

“ወደዚህ አምጡአቸው በፊቴም እረዱአቸው" ውን በመምዘዝና ላልሆነ ትርጓሜ ልናውለው እንወዳለ እንዴ? ምክንያቱ፦ “እረዱአቸው ኃይለ ቃል ለጌች አይስማማውም። ለምን ቢባል፦  መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፥ የሚያሳድዱአችሁን፣ የሚገድላችሁ፣ መርቁ፥ እንጂ አትርገሙ፤ ይላልና። እነ ጽጌ ስጦታው እና መሰሎቹ፣ አረዳድና አካሄ የሚሄዱ አህዛብም፤ ይህንን ኃይለ ቃል ላልሆነ ትርጓሜ ሲጠቀሙበት ሰምቻለሁ።

ሌላው ደግሞ፥ እነ ጽጌ ስጦታው እና መሰሎቹ ለ ገንዘብ ነብዩ ሲራክን መልዕክቱን፣ ሐሳቡን፣ ዓላማውን፤ በደምብ ካለመረዳታቸ የተነሳ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ ያለ ነገር አናገኝ ማለታቸው የመንፈሳዊ ዕውቀታቸው ምን ያህል አናሳ መሆኑ ያሳየናል።

ታዲያ አጠቃላይ ሙሉ ራቸውን፥መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ብንመዝነው እንኳን፤ የሚሰሩት ስራ፥ ላልተገባ ትርጎሜ እንጠቀሙበት፣ ሆኖ እናገኝዋለን! “አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ” /1ኛ ጢሞ 6፥11/ እንደተባለ መሸሽ ያስፈልጋል።

                                                           /ይቆየን/
                                ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወድንግል ማርያም!

No comments:

Post a Comment