"ግብረ ሶዶማዊነት በኢትዮጵያ" በሚል፦ መምህር ደረጄ ዘወይንዬ፤ በግብረ ሶዶማዊያኖች፥ ላይ ባደረገው ጥናታዊ ዳሰሳ፣ ከድምጸ ተዋህዶ የሬድዮ ፕሮግራም አዘጋጆች ጋር ባደረገው የቃለ መጠይቅ ቆይታ፥ እንዴት ወደ ግብረ ሶዶማዊነት ሕይወት እንደገቡ፣ በግብረ ሶዶማዊነት ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል፣ ሥራዎቻቸውና እንቅስቃሴዎችቸውን፤ በተመለከተ ሰፋ ያለ፥ በተበራራና ግልፅ በሆኑ ቃላቶች፣ ከግብረ ሶዶማዊያን ሕይወትና ተመክሮ በመነሳት፣ ስለ ግብረ ሰዶማውሪያን እንቅስቃሴ የሚያመለክትና ግንዛቤ የሚያስጨብጥ፣ ወደዚህ ሕይወት ለገቡት የመውጪያውና የማምለጫው በር፣ ወደዚህ ሕይወት ለመግባት ዳር ዳር ላሉ ደግሞ የደውል ምልክት ነውና። ታዲያ በግብረ ሶዶማዊያን ዙርያ የቀረበው በተጨባጭ ሁናቴ በመረጃና በማሰረጃ ስለሆነ ግንዛቤ እንዳስጨበጠን የታመነ ሃቅ ነው!
“ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሶዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሰራር” የሚለውን በደረጀ ነጋሸ ዘወይንዬ አዘጋጅና አቅራቢነት በቪዲዮ ወምስል ካቀረበልን ከግብረ ሶዶማዊያን መካክል አንዱና ዋነኛ የሆነው አብይ (ኤሊያና) ስለራሱና ስለ ጓደኞቹ ስል ግብረ ሶዶማዊያን ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል፣ በእውነተኛ ታሪካቸው በተፃፈው መፅሐፍ አማካይነት ስለ ግብረ ሶዶማዊነት ሲናገር እንዲህ ነው የሚለው፦
* “ግብረ ሰዶማዊነት፥ እንደ ማግኔት ነው! አንድ ጊዜ ስቦ ካጣበቀ በኋላ
የማይለቅ” ነው ብሎ ይገልፀዋል። (መፅሐፍ፦ የሰዶም ነፍሳት፥ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ)
* በዚህ ቪሲዲም ሆነ
መፅሐፍ ላይ አብይ (ኤሊያና) እራሱን ትውልድ ይዳን
ግብረ ሶዶማዊነት በኛ ይበቃ በማለት እራሱን አሳልፎ የገለጠ ታላቅ ሠው ነው።
* አብይ (ኤሊያና) ይሁን ሌሎችም በግብረ ሶዶማዊነት ያገኙት አንዳች ጥቅም እንደሌለ
ነው የሚስረዱት።
* በግብረ ሶዶማዊነት ያገኘውና ያተረፍ ትርፍ ቢኖር፥ የሥነ-ልቦና ቀውስ፣ የህሊና ወቀሳ፣ በራስ የመተማመን ስሜት ማጣት፣
የፊንጢጣ፣ የኤች ይ ቪ ፖዘቲቭ፣ ለተለያዩ በሽታ መጋለጥ፣ ወደ ተቃራኒ ፆታ መቅረብ አለመቻል፤ እነዚህን ሌሎችንም የመሳሰሉትን
ቀውሶችን ለራሳቸው ገንዘብ እንዳደረጉ እንደሆነ ነው የሚገልፁት።
* ስለ ግብረ ሰዶማዊነት ምስክርነት
ዋነኛ ምስክር እኔ ነኝ፥፥ ከኔ ሌላ ምስከር ሊመጣላችሁ አይችልም
* ትውልድ እስከዳነ ድረስ ሞትም ቢሆን ለእኔ ጥቅሜ ነው!!! (ለሠዎች እራሱን በመግለጡን
ምክንያት ለሚመጣበት ማንኛውንም መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ሲያጠይቅ)
አንድ አፍታ ቆይታ ከአብይ
(ኤሊያና)መልዕክት ጋር
.... (መፅሐፍ፦ የሰዶም ነፍሳት)
“ኡፍፍፍፍፍ!”
ለብዙ አመታት የታመቀ
.. ግን ልተነፍሰው የምፈልገው ስሜት እነሆ ተዘረገፈ።
“እፎይ!” ብል ደስ ባለኝ፥ የምችል ግን አጥመስለኝም። መፅሐፉ ከወጣም
በኋላ በሕይወት ወስጥ ያሉትን ግብረ ሰዶማዊ ጓደኞቼን እፈራቸዋለሁ ... “ማባባስ ነው” ብለው የሚያስቡትን እፈራቸዋለሁ ...
ስለ እኔ ሕይወት ገና አሁን በዚህ መፅሐፉ አማካይነት የሚያውቁ ... ቤተሰቦቼን፣ ዘመድ አዛማዶቼን እፈራቸዋለሁ።
ግን
ስንት ጊዜ እሞታለሁ?
ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሉት
አንዱን ግባ በለው አለ እንደተባለው ዘጠና ዘጠኝ ፈራቻዎች ቢኖሩኝም ትውልድን ከማዳን የበለጠ ስላልሆነ ደፈርኩ። አይነኬ የሆነውንን
ለመስማት እንኳን የሚቀፈውን ታሪኬንና ታሪካችንን ወደ አደባባይ ላወጣው ወሰንኩኳ።
አንድ ሰባኪ አንድ ጊዜ
“ኢትዮጵያውያን እንወድቃለን ብላችሁ አትፍሩ” ሲሉ የሰበኩት ትዝ ይለኛል። “ኢትዮጵያዊያን አይዟችሁ ... እንወድቃለን ብላችሁ
አትፍሩ - ወድቃችኋልና” ካሉ በኋላ “ይልቅ ለመነሳት ሞክሩ” ሲሉ ደመደሙ። እና እኔም አሁን እሞታለሁ ብዬ አልፈራም! ግብረ ሰዶማዊ
ሳለሁ ሙት ነበርኩና። ይልቅ ሕይወት ለማግኘት ነው ይሄ መፅሐፉ እንዲታተም መፈለጌ - በእኔ ታሪክ የሚድኑ ሁሉ ሕይወት ይለግሱኛልና።
ግብረ ሰዶማዊነት፥ ልክ
እንደ ማግኔት ነው! አንድ ጊዜ ስቦ ካጣበቀ በኋላ የማይለቅ። በሕይወቴ ከተዘፈቅኩበት የልጅነት ጊዜዬ አንስቶ (ከግብረ ሰዶማዊነት)
ከሕይወቴ ለመውጣት ምን ያህል እንደቃተትኩ፣ ምን ያህል እንደተሰቃየሁ፣ ምን ያህል እንዳነባሁ፤ እኔና እግዚአብሔር እናውቃለን።
ከልብ መታወክ እስክ አእምሮ መነካት ደርሻለሁ። ማግኔት ከሆነው ሕይወት ለመውጣት እየሞከርኩ ራሴን ተመልሼ የማገኘው እዛው ውስጥ
ስንቧችር ነበር። ልክ እንደ እኔ ከሕይወቱ (ከግብረ ሰዶማዊነት) ለመውጣት የሚፈልጉ በዙዎች እንዳሉ አውቃለሁ።
ምናልባት ይህ መፅሐፍ
የረዳቸው ይሆናል። ከገቡበት ይልቅ ገና ሊገቡበት የፈለጉትን ምናልባት ይህ መፅሐፍ ያስቆማቸው ይሆናል። ዘመናዊነት፣ አራድነት፤
አሪፍነትና ስልጣኔ ለሚመስላቸው ሁሉ የሕይወቱን አስቀያሚ ገፅታ ማየት እንዲችሉ ይረዳቸዋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
በተለይ የቤተሰብ አስተዳደግ
የሚፈጥረው ተፅዕኖ በማሳየት ረገድ፣ እንዲሁም ወላጅ፥ ሴት ልጁን ብቻ ሳይሆን ወንድ ልጁን ከጥቃት እንዲጠብቅ ያስችላል ብዬ አምናለሁ።
የተፃፈበትን ዓላማ ለማይረዱ ደግሞ ምናልትም ያነሳሳ ይሆናል ብዬ እፈራለሁ። ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርምና ፍርሃቴን ውጬ፥
መውጣቱን ወሰንኩ። ምክንያቴ ደግሞ፦ በሳውድ አረቢያ የሆነው ክስተት ነው።
ሲሰርቅ የተገኘ እጁን
ይቆረጥ የሚለው ህግ፥ ሌቦችን ያጠፋል የሚል እምነት ስላለ ህጉ ተፈፃሚ ይሆን ነበር። እናም ሲሰርቁ የተገኙ ሌቦች በአደባባይ እጃቸው
እየተቆረጠ ሳለ ይህን ተእይንት ተሰብስበው ይመለከቱ ከነበሩ በርካታ ሰዎች መካክል የአንዳንዶች ዋሌት ተሰረቆ ነበር።
ዓላማዬን የማይረዱትን
በሕይወት ውስጥ ያሉትን ሰዎች የምፈራቸውም ለዚሁ ነው፣ ባህል ተነካ የሚሉ ወግ አጥባቂዎችን የምፈራቸውም ለዚሁ ነው፤ ማባባስ ነው
ብለው የሚስቡትን የምፈራቸውም ለዚሁ ነው።
ግን
ስንት ጊዜ እሞታለሁ?
ትውልድ እስከዳነ ድረስ ሞትም ቢሆን ለእኔ ጥቅሜ ነው!!!
(ከላይ ከዕርሱ፥ እንዳነበባችሁት፣ እንዳያችሁትና እንዳዳመጣችሁ፤ እርስዎ
በሃገራች ይህ መኖሩን ያውቁ ነበር? አሁንስ ምን ይላሉ? ስለ ሰዶመ ነፍሳት ምን ተሰማዎት? ምንስ ይላሉ? ከልጆዎ ጋር ስለዚህ አስከፊነት እንዴትስ ሊነጋገሩ አስቧልን? ከወዳጅ፣
ከዘመድ-አዝማድስ ጋር ሊያወሩበት ተዘጋጅተዋልን? ከባልዎ ወይንም ከሚስትዎ፣ አልያም ከፍቅር ጓደኛዎስ ጋር በግልፅ
ልትነጋገሩበት ወስናችዋልን? ተወያዩበትና ወስኑ!!!)
26/10/2013
No comments:
Post a Comment