Friday, December 28, 2012

በተሰደብክ ጊዜ


      ስለዚህ ወዳጄ፦ እንደ ቃየን ላለመሆን እንደ እንደ ንጉሱ ዳዊት ለመሆን በተሰደብክ ጊዜ፣ በውይይቶች መሐል፣ በባልና በሚስት፣ በቤተሰብ፣ በመስሪያ ቤት፣ በት/ቤት፤ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ይህን በመሳሰለው ባለመግባባት ችግር ጊዜ ይሄን አስታውስ!። እግዚአብሔር፦ ስደበው ብሎ አዝዞታልና ይርገመኝ ለምንስ እንዲህ ታደርጋለህ? የሚለው ማን ነው? እግዚአብሔር አዝዞታልና ተዉት፥ ይርገመኝ በል። በዚህ ጊዜ ሞኝነትን ሳይሆን ገንዘብ ያደረከው ትዕግስትንና ታጋሽነት ነው!  

Tuesday, December 25, 2012

"ስምዖንም ባረካቸው እናቱን ማርያምንም።" /ሉቃ 2፥ 34/




         *ቅድስት ድንግል ማርያምን መባረክ እነሆም፥ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል ሰው ነበረ፥ ይህም ሰው የእስራኤልን መጽናናት ይጠባበቅ ነበር፤ ጻድቅና ትጉህም ነበረ፥ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበረ። በጌታም የተቀባውን ሳያይ ሞትን እንዳያይ በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ ነበር። /ሉቃ 225-26/