እርሱ የእግዚአብሔር በግ ነው፤ እርሱም መሥዋዕት ነው።
እርሱ ስለብዙዎች ኃጢአት የተሠዋው ፍሪዳ ነው፤ እርሱ መሥዋዕቱን የሚያቀርብ ሊቀ ካህናት ነው፤መሥዋት
ተቀባዩም እርሱ ነው።
ስለእኛ መከራን የተቀበለው እርሱ ነው፤ ስለእኛም የራራልን እርሱ ነው።
እርሱ ሙሽራ ነው፤ እርሱ ራሱ ሙሽሪትም ነው። (ከእናታችን የነሣው ሥጋ ለጌታችን እንደሙሽሪት
ነው። ይህ ሥጋ ግን አምላክ በመሆኑ ሙሽራ ሆነ፤ በሐዋርያትም
እኛ ለእርሱ ታጨን። ስለዚህም እርሱ ሙሽራ ነው፤ እርሱ ራሱ ሙሽሪት ነው አልን)።
እርሱ የሰርጉ ቤት ነው፤ እርሱ ራሱ የሰርግ ቤቱ አሳላፊ ነው።