ከሩቅ ይሰማኛል፤
የቤተ- ክርስቲያን ደውል፤
ነፍስን የሚያማልል፤
ልብን የሚያባብል።
እንደ አዲስ የሆነ፤
እንደ አዋጅ የሆነ፤
ከቀኑ ሁሉ ጠዋት እሁድ የገነነ፤
ከእለት ሁሉ ግህዝ እሁድ የገነነ።
ማለዳ ሰንጥቆ የሚያስገመግም፤
ሠመመን መሳይ ድምፅ፥ ከሩቅ ሚሰማ፤
ቀላቀሎ የያዘ፥ የካህናት
ወረብ፣ የካህናት ዜማ።
ንፋስ የሚያመጣው፥ አልፎ-አልፎ ሽው፣ የሚል፤
ተነስ ቀድሰ የሚል፥ አዳም የት
ነህ የሚል።