በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ስለ ጌታችን፣ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ትምህርቱ የሚዳስሳቸዉ ነጥቦች፦
•
ቀዳማዊ ወድኅራዊ ሕያዉ ዘላለማዊ አምላክ ስለመሆኑ፤
•
ቅድመ ዓለም ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት፣ ድኅረ ዓለም ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያለ አባት ስለመወለዱ (ስለ ሁለቱ ልደታት፤
• ስለ ድንቅ ልደቱና የልጅነት ህይወቱ፣ ስለ ጥምቀቱ፣ ስለ ትምህርቱና ስለ ተዓምራቱ፣ ስለ ህማሙ፣ ስቅለቱ፣ ሞቱ፣ ትንሣኤዉና ዕርገቱ፣ ዳግመኛም ለፍርድ ስለ መምጣቱ፤ ወዘተ… ይሆናል።
በቅድሚያ አንድን
አካል "አምላክ" ነው ለማለት የአምላክነት ባህርያት ምን እንደሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል። የሁሉ ነገር የማንነቱ መገለጫ ወሠን ባህርዩ ነውና። ሰለዚህ የአምላክነት ባህርያት የሚባሉትና የየትኛዉንም ሃይማኖት ተከታይ ወይም ፍልስፍና አራማጅ የሚያስማሙት፡-