Friday, April 25, 2014

"እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው!" ማለት ምን ማለት ነው? /ዘጸ 15፥3/



በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራዕይ በጥሬ-ቃል “እግዚአብሔር” የሚለው ቃል ወይንም ሐረግ 7361 (ሰባት ሺ ሦስት መቶ ስልሳ አንድ) ጊዜያት ተጠቅሶና ተጽፎ እናገኛለን። እንደዚህ ቢሆን መፅሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሥም በአንድም በሌላም መንገድ እናገኘዋለን፤ ለምሳሌ እኔ የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የያዕቆ አምላክ እንዲል።

"እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው!" በሚለው በዚህ ጥቅስ ውስጥ ሁለት ዓበይት ነገሮችን እናገኛለን። ይኸውም

1ኛ . "እግዚአብሔር"
2ኛ . "ተዋጊ" የሚሉትን ቃል ወይንም ሐረግ ናቸው።

"እግዚአብሔር" ማለት «ያለና የሚኖርመጀመርያውና መጨረው፣ አልፋና ዖሜጋፊተኛውና ኋለኛው» ማለት ነው፥ ይህ የዘላለሙ ስሙ ነው/ዘጸ 314እ 1፥17፣ 2፥8፣ 21፥6፣ 22፥13፤/

"ተዋጊ" ማለት ደግሞ በአንድም በሌላ መንገድ እግዚአብሔር ስለ መጠጊያስለ ጋሻስለ ኛ መከታ፣ ስለ ተዋጊ (ይዋጋል) ዝም እንላለ! እርሱም፥ ማዳኑን፣ ፍቅሩን፣ቱንምህቱንዚህንገች ይገልጥልናል ማለት ነው።  /ዘጸ 1414 ዘዳ 130፣ 3፥22 ነህ 4፣202 2231512 287901፣ 91፥1-10፤ ምሳ 305፤ ኢሳ 38፥14፤ ዘካ 14፥3፤ ሮሜ 1312፤ ኤፌ 616ዮሐ 19፥11/

እግዚአብሔር ማለት «ያለና የሚኖር መጀመርያውና ጨረው፣ አልፋና ዖሜጋ ፊተኛውና ኋለኛው» ነው ካልን ታዲያ ተዋጊ ደግሞ መጠጊያ ጋሻ መከታና ተዋጊ እንደሆነ መልክተናል። ስለዚህ ሁለቱን ስናቀናጀው፥ እግዚአብሔር ተዋ ው፣ እግዚአብሔር ጋሻ ው፣ እግዚአብሔር መከታ ው፣ እግዚአብሔር ጠጊ ው፤ የሚሉ ቃል ወይንም ሐረግ ናገ።እንግዲህ የእነዚህን የሁለቱን ትርጉሞችን ከተረዳን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው!" የሚለው ጥቅስ እንዴት እንየው ከመጽሐፍ ቅዱስ ዕይታ?

*
የእግዚአብሔርጋሻከታና ውጊ፤ ወደ ፈርዖን ቤት፦

እስኤል ዘ ሥጋ በጽኑ ሐን፣ በከባጉልት ሥ፣ በመረረ ለቅሶና በታላቅ በሆነ ጩኽት በግብፅ ምድር ሳሉ ነበር እግዚአብሔር ለቀ ነሙሴ ተገልጦት ወደ ፈርዖን ቤት ሄዶ ህዝቤን እንዲያገለግለኝ ልቀቅ በል ብሎት በሰደደው ጊዜ ነበር ሊቀ ነት ሙሴ አንድ ጥያቄ ጠየቀ።

የሊቀ ነት ሙሴ ጥያቄም፦ "ሙሴም እግዚአብሔርን ወደ ፈርዖን የምሄድ የእስራኤልንም ልጆች ከግብፅ የማወጣ እኔ ማን ነኝ? ሎ በየቀው ጊዜ፤ እርሱም (እግዚአብሔር)፦ በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ነው ሕዝቡን ከግብፅ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ ለእግዚአብሔር ትገዛላችሁ አለ። ሙሴም እግዚአብሔርን፦ እነሆ፥ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜየአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ ባልሁም ጊዜ ስሙስ ማን ነው? ባሉኝ ጊዜ፥ ምን እላቸዋለሁ? ሲል፤ እግዚአብሔርም ሙሴን፦ «ያለና የሚኖር» እኔ ነኝ ሎታ እንዲህ ለእስራኤል ልጆች «ያለና የሚኖር» ወደ እናንተ ላከኝ ትላለህ። እግዚአብሔርም ደግሞ ሙሴን አለው ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ። የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ላከኝ ይህ ለዘላለሙ ስሜ ነው፥ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።" ላለ ሎታል። /ዘጸ 311-15/

እዚህያ በእግዚአብሔር ድ አዥነት፣ ቀ ነት ሙሴ ታዛዢነት፤ እስኤል ዘ ሥጋ በብዙ መከራና ችግር፣ ውጣ-ውእንግልት፤ ከባት ከመውጣታቸው በፊት እግዚአብሔር ትእዝ አዟቸው ነበር። ትእዛዙም፦ የበጉ የደም ምልክት በቤቶቻቸው እንዲሆንላቸው ነው። ከወጡ በኋላ ደግሞ ትእዛዙን እንዲጠብቁት እርሱ የበጉ የደሙ ምልክት የእግዚአብሔር ፋሲካ ነውና በዓል አድርጉ ብትእዛዝ አዟቸዋል።

“የበጉ የደሙ ምልክት የእግዚአብሔር ፋሲካ ነውና በዓል አድርጉ” የበጉ የደም ምልክትና ፋሲካ የሚለውን! ልብ ይበሉ!

* እስኤል ዘ ሥ

እስኤል ዘ ሥበወጡበት ወቅት፥ ሠም፣ ሐሴት፣ ፍስሐ፤ በሆነበበዚያም ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህንን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩ።

በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤
ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።

ጕልበቴ ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፥ መድኃኒቴም ሆነልኝ፤
ይህ አምላኬ ነው አመሰግነውማለሁም፥ የአባቴ አምላክ ነው ከፍ ከፍም አደርገዋለ።

እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው፤
የፈርዖንን ሰረገሎች ሠራዊቱንም በባሕር ጣላቸው፤
የተመረጡት ሦተኞች በኤርትራ ባሕር ሰጠሙ።

ቀላያትም ከደኑአቸው፤
ወደ ባሕር ጥልቀት እንደ ድንጋይ ሰጠሙ።

አቤቱ፥ ቀኝህ በኃይል ከበረ፤
አቤቱ፥ ቀኝህ ጠላቱን አደቀቀ።

በክብርህም ብዛት የተነሡብህን አጠፋህ፤
ቁጣህን ሰደድህ፥ እንደ ገለባም በላቸው።

በአፍንጫህ እስትንፋስ ውኆች ተከመሩ፥
ፈሳሾችም እንደ ክምር ቆሙ፤
ሞገዱም በባሕር ውስጥ ረጋ።

ጠላትም፦ አሳድጄ እይዛቸዋለሁ፥
ምርኮንም እካፈላለሁ፥ ነፍሴም ትጠግባቸዋለች፤
ሰይፌንም እመዛለሁ፥ እጄም ታጠፋቸዋለች አለ።

ነፋስህን አነፈስህ፥ ባሕርም ከደናቸው፤
በኃይለኞች ውኆችም እንደ አረር ሰጠሙ።

አቤቱ፥ በአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
በምስጋናህ የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥
በቅድስና የከበረ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
ቀኝህን ዘረጋህ፥ ምድርም ዋጠቻቸው።

በቸርነትህ የተቤዠሃቸውን ሕዝብህን መራህ፤
በኃይልህ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ አገባሃቸው።

አሕዛብ ሰሙ፥ ተንቀጠቀጡም፤
በፍልስጥኤም የሚኖሩት ምጥ ያዛቻው። /ዘ 15 1-14/


ቀ ነት ሙሴ ኅህትም፣ ዘማንና ዘማሪያት ተሰብስበው በሆሆታና በእልልታእግዚአብሔርን፥ ተዋት፣ ኃልነት፣ መድኃኒትነት፣ ጠጊያነት፣ ጋሻነት፤ ከመዝሙሩንፈዊ ሥግጥም መረዳት እንችለን።

Sunday, April 20, 2014

ክርስቶስ፥ በከርሰ መቃብር፤ ሦስት መአልት ሦስት ሌሊት እንዴት ሊሞላው ቻለ? በቀሲስ ብርሃኑ ጎበና

        ክርስቶስ ሦስት መአልት ሦስት ሌሊት፣ በከርሰ መቃብር አደረ፤ የሚባለው፥ እንዴት ሆኖ ነው? (ለሚለው ጥያቄ፥ ምላሹ በሁለት ዓይነት አረዳድ እንገነዘባለን)

        
፩፤ ለዚህ ምላሽ የዕብራውያንን አቆጣጠር ማወቅ ያስፈልጋል:: የመጽሐፍ ቅዱስን ምስጢር ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት የዕብራውያንን ሥርዓት ወግና ጂኦግራፊያዊ (መልክአ ምድራዊ) አቀማመጥ ያስፈልጋል።

        
ምክያቱም፥ ጸሐፊዎቹ ባህላቸውንና ሥርዓታቸውን ጠብቀው የጻፉት ስለሆነ ነው። ጌታ ዓርብ ተሰቅሎ ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ከተነሳሣ እንዴት ብሎ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ይሞላል ሊያሰኝ ይችላል።

        
ዕብራውያንን አቆጣጠር ሌሊት የሚቆጠርው በዋዜማው ካለው አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው። ከአሥራ አንዱ ሰዓት በፊት ያሉት ሰዓቶች ግን አንድ ሰዓትም ቢሆን እንደ አንድ መዓልትና ሌሊት ይቆጠራል። ጌታ የተቀበረው ዓርብ ከአሥራ አንድ ሰዓት በፊት ስለሆነ የተቀበረበት ሰዓት የዓርብን መዓልትና ሌሊት ያጠቃልላል።

        
አርብ ከሠርክ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ ቅዳሜ አሥራ አንድ ሰዓት ከሰዓት በዋላ ድረስ ያለው የቅዳሜ መዓልትና ሌሊት ነው። ቅዳሜ ከአሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ያለው እሑድ ነው። አንዱም ሰዓት ቢሆን ከላይ እንደ ተገለጠው የዕለቱን ሰዓቶችን ያሟላል። ጌታም የተነሣው እሑድ በመንፈቀ ሌሊት ስለሆነ ሦስት መዓልት ሶስት ሌሊት ይሆናል።

        
፪፤ ሁለተኛው ደግሞ የተሰቀልው በዕለተ አርብ ሰለሆነና የሞተውም በዕለት አርብ በመሆኑ አቆጣጠሩ ከአርብ ጠዋት ይጀምራል። አርብ ጠዋት ከ፲፪ ሰዓት እስከ ሰዓት ድረስ በምድር ላይ ብርሃን ነበር፤ አንድ ቀን።

        
ከ፮ እስከ ሰዓት በምድር ላይ ጨለማ ሆነ ይላል መጽሐፍ ቅዱስ፤ ያም፥ ጨለማ እውነተኛ ጨለማ እንጂ በምትሐት የሆነ ስላልሆነ እንደ ሌሊት ይቆጠራል። አንድ ቀን አንድ ሌሊት ይኖረናል። አርብ ከ፱ ሰዓት እስከ ምሽቱ ፲፪ ሰዓት እንደገና ቀን ሆኖአል፤ አርብ ሌሊት ለቅዳሜ አጥቢያ ያለውን ጨለማ ወይም ሌሊት ስንቆጥር ሁለት ቀን ሁለት ሌሊት ይሆናል።

        
ቅዳሜ ሙሉ ቀንና ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ ጌታ እሁድ ሌሊት ተነስቷል፤ አንድ ላይ ሲደመር ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ይሆናል። እንግዲህ በሁለቱም ዓይነት የሚቆጥሩ ስላሉ ሁለቱም ዓይነቶች ቀርበዋል እኛም የገባንና የተረዳንን አቆጣጠር መርጠን ማስረዳትም መረዳትም እንችላለን።

                     
<<<<<<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! >>>>>>>>

ምንጭ፦ ዓምደ ሃይማኖት /ገፅ ፹፱/ ሲስ ብርሃኑ በና