ፕሮቴስታንቶች (ተሐድሶ)
በሐዲስ ኪዳን ውስጥ በማስረጃነት ደረጃ የተጠቀሰ ጥቅስ የለም ይላሉ። ይህ አባባላቸው የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን በደንብ ካለማንበባቸው
የተነሣ እንጂ በብዙ ቦታዎች እንደተጠቀሱ ማስረጃዎችን ከብሉይ ኪዳንም ከሐዲስ ኪዳንም እንደሚከተለው መጥቀስ ይቻላል!
ፕሮቴስታንቶች (ተሐድሶ)፦
ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚፈልጓቸውን ብቻ በመውሰድ ሌሎችን ትተዋቸዋል። በመሆኑም እነርሱ በሚቀበሏቸው እና ቤተ-ክርስቲያናችን
በምትቀበላቸው መጻሕፍት ቁጥር መካክል ልዩነት አለ።
1.
የፕሮቴስታንቲዝም መስራች ማርቲን ሉተር
ለእርሱ ትምህርት የማይመቹ የመሰሉትን መጻሕፍት እያወጣ ይጥል ነበር። ለምሳሌ፦ የያዕቆብ መልእክት ስለ ምግባር አስፈላጊነት
ሰለሚያስተምርና ይህም ማርቲን ሉተር ስለ ጸጋ እና እምነት በቻ ይሰብከው ከነበረው ትምህርቱ ጋር አልሄድ ስላለው መልእክቱን
ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አውጥቶት ነበር። እንዲያውም “Epistle of straw ገለባ መልእክት” ብሎ እስከ መጥራት ደርሶ
ነበር።
2. አንዳንድ ወገኖች ከ66ቱ መጻሕፍት ውጭ ያሉትን መጻሕፍት “አፖክሪፓ” ብለው ይጠሯቸዋል። ይህ ግን የተሳሳተ ስያሜ
ነው። “አፖክሪፓ” በጥንት ዘመን ምሥጢራዊ ለሆኑት የጥንቆላ መጻሕፍት የሚሰጥ ስም ነውና። እኛ ግን፥ የብሉይ ኪዳን
መጻሕፍቱን፦ “ሁለተኛ የቀኖና መጻሕፍት - ዲዮካትሮኒካል” እንላቸዋለን።
3. የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁለት ዓይነት የቀኖና ክፍሎች አሏቸው። እነርሱም፦ የመጀመርያ-ፕሮቶካኖኒካል፣ እና ሁለተኛ-
ዲዮካትሮኒካል ይባላሉ።