ከጻድቁ ኢዮብ ትምህርትና ምክር የተነሳ፥ በዙሪያው የነበሩትን የነነዌ መርከበኞችን፣ ነጋዴዎችን፣ መኳንቶችን፣ ከደቂቅ እስከ አዋቂ፣ አጠቃላይ በወቅቱ የነበሩትን ስለሁናቴው ሲገልጽል "ሰዎች፥ እኔን ሰምተው በትዕግሥት ተጠባበቁ፥ ምክሬንም ለማዳመጥ ዝም አሉ።" ብሎ ተናግሯል። ነቢየ ዕንባቆም "እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ ምድርም ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል።" /ዕን 2፥20/ ብሏል። በማቴዎስ ወንጌልም፥ ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ ሰለ አምላካችንና ስለ መድኃኒታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የባህሪው አምላክነቱንና ሲያመለክት፤ "ኢየሱስም፦ ዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሠጸው።" /1፥25/ ይላል፤ እዚህ ጋር እርኩሳንነን አጋንትን በቃሉ የሚያዝ ስለሆነ "ዝም በል ከእርሱም ውጣ" ብሎ ገሠጸው እንጂ "አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ" /ዮሐ 17፥23/ ይህንን አጋንት፥ አሶጣልኝ፣ ላሶጣ፣ ወይንም እናውጣ፤ ብሎ አልጻፈልንም፣ አልሰበከንምም። የሆነው ሆኖ ግን ይህንንም ሥልጣነ ፈውስ (አጋንትን መገሠጽ) ራሱ ባለቤቱ የሰጣቸው ጸጋ ነው።
እንግዲህ የእግዚአብሔር ልጆች በተቀደሰ መቅደሱ ቤተ-ክርስቲያን ያሳደገቻቸው ልጆቿ፥ ሲናገሩ፣ ሲያስተም፣ ሲዘምሩ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ከአንደበታቸው ሰምተው በትዕግሥት ይጠባበቃሉ፣ ምክሩም፥ ግሩምና ድንቅ ከመሆኑ ብዛት የተነሳ ለማዳመጥ ዝም ይላሉ! ምድሪቱንም በቃላቸው ይገስጿታል፥ ከመገሰጿም የተነሳ በፊታቸው ዝም ትላለች። እንዲሁም ከራሱ ከባለቤቱ የተቀበሉት ጸጋ ነውና፥ እነ ቅዱስ ጳውሎስ አጋንትን ሲገሥጹ እንደነበር በዘመነ ሐዲስ ተመዝግቦልናል። በዘመናችንም የተባረኩና የጸጋ ተካፋይ በሆኑት አባቶች ሥልጣነ ፈውስ (አጋንትን እየሠጹ) ዝም ሲያስብሉና ሲያሶጡ እያየን ነው፥ ደግሞም የእግዚአብሔ እጅ መች ይታጠፍና፤ ገና እናያለን።
እነዚህ ሁሉ፥ ከአንዲት፣ ከቤተ-ክርስቲያን የተገኙ ልጆቿ ናቸው፣ አምላካቸውና መድኃኒታቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ብዙ ሞግዚቶችና አእላፍት አሏቸው!
No comments:
Post a Comment