የክብሩ ሞገሥ፦ በሠማያት፣ በምድር፣ በጥልቁም ሥፍራ ያለ፤ እግዚአብሔር ለፈጠረን ፍጥረቱ (በተለይ ለእኛ በአምሳሉ ለፈጠረን ሠዎች) ስለሚወደንና ስለሚያፈቅረን ይገሥጸና! በነጐድጓድና በመባርቅት፣ በከባድም ደመና ድምፅ፣ በብርቱ የንፋሳት
ውሽንፍር ድምፅ፤ እግዚአብሔር፥
ህዝቡን ይገስጻል!።
ከነዚህ፥ ከተፈጥሮ ተግሣጽ ይልቅ ግን ተግሣጽን
በአንደበተ-ቃል (ከሠዎች በሚወጣ ቃል) ሲገሥጽ በብሉይም በሐዲስም እናያለን። ለምሳሌ ያህል፥ በብሉይ፦ እግዚአብሔር፥ በሚወዳቸውና እንደ ሐሳቡና እንደ ትህዛዛቱ የሚሄዱትን
አገልጋዮቹን በመላክ፣ በነቢዩ ኤርምያስ አንደበት አድሮ፦ ተግሣጽን አትቀበሉምን? /ኤር 35፥13/ እያለ ያናግር ነበር እናነባለን።
ይህ ተግሣጽ፥ በብሉይ ብቻ ሳይሆን በሐዲስ ኪዳንም ቢሆን የምናገኘው እውነታ ነው!። ይህ የተግሣጽ እውነታ ደግሞ እራሱ ባለቤቱ፦ የፍቅር አምላክ፣ የተግሣጽ ጌታ፣ መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስም በመዓክለ ምድር ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በስጋ ተወለዶ፣ (ከበረት ውስጥ መወለድ ጀምሮ እስከ በዓለ ዕርገት፤ የተተረከውን ብናነብና ብናስተውል፣ በመንፈሳዊ ዕይታ ብናያቸው፣ ፍቅርን ብቻ ሳይሆን ተግሣጽ እናገኛለን! ) ሲያስተምርና ይህንን ዓለም በፍቅሩ አቅርቦ፣ በተግሣጹ ገሥጾ፤ ሕይወትን እንድናገኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያት እንዲህ ሲል ጥያቄ አቀረበላቸው፦ "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?" ብሎ ሲጠይቅ፥ ሐዋርያትም በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን፣ እንዲሁም በአይሁድ ረበናት ካህናት የሚባለውንና የሚናገሩት ቀድመው ስለሰሙ፦ "አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው፤ ይላሉ
አሉት።"