ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በተለያየ መልክቶቹ "ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።" /ገላ 6፥14/ ቢል "ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።" /ገላ 1፥8/ ቢለን እንኳን በአንድም በሌላም መንገድ ስለቅዱሳን ይሁንም ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሳይነግረን፣ ሳያስተምረን፣ ሳይሰብከን፤ ግን አላለፈም።
ለዚህ ደግሞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ክርስቲያኖች ባስረዳቸው እውነተኛ አስተምህሮ ድንግል ማርያም ንጽሕት፣ ድንግል መሆኗን፤ መስክሯል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ለክርስቶስ አገልግሎት በተጠራበት ግዜ "እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን
ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና" /2ኛ ቆሮ 11፥ 2/ ይላል። ታዲያ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በትንቢተ ሕዝቅኤል /44፥ 2/ የተነገረውን የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ ሲናገር እመቤታችን ድንግል ማርያም ንጽሕት፣ ድንግል፣ ለክርስቶስ
በክርስቶስ እንደሆነች አስረግጦ አስረድቶናል።