ሳውዲ ከሪስ አብደላ ሚባል አካባቢ ዝናብ ጥሎ በአሁን ሰዓት መብራት ጠፍቶ ከተማው ጎረፍ ላይ ነው። በአረባ አመት ውስጥ ታይቶ ማይታወቅ ። ሳውዲ ሆይ፦ የማይነኩትን የቅድስት አገር ኢትዮጵያ ልጆች ነክተሻልና ፍርድሽን ከላይ ተቀበይ! (ፍሪደም ፎር ኢትዮጵያ)
የመጨረሻው መጀመርያ፦
የመጨረሻው
መጀመርያ፥ ማለቴ፦ ለእነርሱ የመጨረሻ፣ ለፈጣሪያችን ደግሞ ሥራውን የሚጀምርበት መጀመርያ፤ ማለቴ ነው!!!
እግዚአብሔር፥ በነቢዩ ኢሳያስ አንደበት አድሮ፤ ሕዝብን ለሚጨፈልቁ፣ ክቡር የሆነውን የሰውን ደም እንደ ውሃ ጅረት በእጃቸው ላጨማለቁ፣ እንደዚህ ይላል፦
"በዚያም ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር
ወደ ልቅሶና ወደ ዋይታ ራስን ወደ መንጨትና ማቅንም ወደ መልበስ ጠራ።"
እውነት ነው! በየትኛውም ዘመን ይሁን - በየትኛው ጊዜ፤ አምላክ ብድራታቸውን
ጠርቶ ይመልስባቸዋል።
በመቀጥል፥ ለተበደሉ፣ ላዘኑ፣ ለተጨነቁ፤ ሕዝብ ደግሞ፦ "እኔም በኢየሩሳሌም
ሐሤት አደርጋለሁ በሕዝቤም ደስ ይለኛል ከዚያም ወዲያ የልቅሶ ድምፅና የዋይታ ድምፅ አይሰማባትም።" /ኢሳ 22፥12 እና 65፥19/ ብሎ ተናግሯል!
ኧረ ለመሆኑ፥ ደስታና ሐሤት የሚያደርግባቸው፣ ሕዝቦች የተባሉት እነማን ይሆኑ? ሕዝብን እየጨፈልቁ፣ ክቡር የሆነውን የሰውን ደም እንደ ውሃ ጅረት በእጃቸው እያጨማለቁ፣
እያረዱና እየገደሉ፤ "ይቅርታ" ጠይቁኝ በሚሉት ይሆን ሐሤት የሚያደርገው? እንደ መለኮታዊ ቃሉ ግን፥ በኢየሩሳሌም
አምሳል የተጥራችው ሃገረ ኢትዮጵያና ፈሪሐ እግዚአብሔር ባደረባቸው ሕዝቦች ደስታና ሐሤት ያደርግባቸዋል።
ለምን ቢሉ እንደ ሰማእቱ እስጢፋኖስ፥ እያዘኑ፣ እየተጨነቁ፣ እየተበደሉ፣
እየታረዱና እየተገደሉ፤ ሰይፍና ጎመድ ይዘው አልዝመቱምና። እንደውም አብዝተ እንደ መዝሙረኛው ንጉሡ ዳዊት "ጠላቶቼ ሁልጊዜ ይሰድቡኛል፥ የሚያሳድዱኝም ተማማሉብኝ። አመድን እንደ እህል ቅሜአለሁና፥ መጠጤንም
ከእንባዬ ጋር ቀላቅያለሁና" /መዝ 102፥8-9/ በማለት የዘመረውን ዝማሬ አብዝተው ዘመሩ እንጂ!!!
ታዲያ ንጉሣችንና አምላካችን ይታደገናል! ስለዚህ፥ ደስታና ሐሤት የሚያደርግባቸው ሕዝቦች ስለሆንን ክብር ይመስግንልን ለምላካችን!!!
ዋቢ፦
1 (ፎቶ) ኢትዮጵያን በአረብ ሃገራት
2 አረብ ኒውስ