"የእግዚአብሔርን ሥራ በቸልታ የሚያደግ ርጉም ይሁን" (ኤር ፵፰፥፲)
"እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፤ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።" (ሉቃ ፲፯፥፲)
አንድን አገልግሎት "መንፈሳዊ አገልግሎት" ነው የሚያሰኙት፤ እነዚህ አራት ነገሮች ሲኖሩት ነው፦
፩፤ አገልግሎቱ፦ ሠማያዊ ዋጋ፥ ታስቦ የሚደረግ ከኾነ ነው። የሚመራውም በመንፈስ፣ የሚሠራውም በመንፈስ ከኾነ ነው "መንፈሳዊ አገልግሎት" የሚባለው። ምድራዊ ዋጋ ታስቦ የሚደረግ ከኾነ "መንፈሳዊ አገልግሎት" አይደለም፤ ይኼ ሥራ ነው።
፪፤ አገልግሎቱ፦ በመንፈስ የሚደረግ ከኾነ ነው። የሚመራውም በሥጋ፣ የሚሠራውም በሥጋ ከኾነ፤ "መንፈሳዊ አገልግሎት" ማለት አይቻልም።
፫፤ አገልግሎቱ፦ በትህትና ከኾነ ነው። ከትዕቢት፣ ከሥልጣን፣ ከክብር፤ እነዚህን ከመሳሰሉት ነገሮች የራቀ ከኾነና በትህትናና ራስን ዝቅ በማድረግ የሚደረግ ከኾነ ነው፤ ይኼ ነው "መንፈሳዊ አገልግሎት" ማለት የሚቻለው። ያ "መንፈሳዊ አገልግሎት" ምድራዊ ክብርን የሚያመጣ፣ ምድራዊ ሥልጣንን የሚያመጣና በምድር ሠዎችን በጣም ከፍ የሚያደርጋቸው ከኾነ "መንፈሳዊ አገልግሎት" መኾን አይችልም። "መንፈሳዊ አገልግሎት" ኾኖ ቢጀመር እንኳን "መንፈሳዊ አገልግሎት" ኾኖ አያልቅም።
፬፤ አገልግሎቱ፦ መሥዋዕትነት ካለበት ነው፤ "መንፈሳዊ አገልግሎት" አገልግሎት የሚባለው። ያ የሚያገለግለው ሠው እራሱ መሥዋዕት እየኾነ የሚያገለግለው ከኾነ ነው። ሌላውን እየሰዋ የሚያገለግለው ከኾነ፣ ወይም ደግሞ ምንም ዐይነት መሥዋዕትነት የማይከፈልበት ከኾነ አገልግሎቱ፦ "መንፈሳዊ አገልግሎት" ነው ማለት አይቻልም። አንድን አገልግሎት፦ "መንፈሳዊ አገልግሎት" ነው የሚያሰኙት እነዚህ አራት ነገሮች ናቸው።
"መንፈሳዊ አገልግሎት" በሚል (በሰባኪ ወንጌል ዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ) በዲ/ን ዳንኤል ክብረት የተሰጠ መንፈሳዊ ትምህርተ ወንጌል ሰምተውና
አዳምጠው፤
ስጋዎትንና
ነፍሶትን ይመግቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ተጋብዘዋል።
እግዚአብሔር አምላክ፦ ለወንድማችን ቃለ ሕይወትን ያሰማልን፤ መንግሥተ ሠማያት ያውርስልን። አሜን!
No comments:
Post a Comment