ሃይማኖት ማለት፦ ሠማያዊ ነገርን በመሻት፥ መንግሥተ ሠማያትን ተስፋ በማድረግ፤ የሚኖርበት ማለት ነው። ታዲያ፥
የማንኛውም ሃይማኖተኞች መሪዎች ለሃይማኖት እምነት ተከታዮቻቸው (ለምዕመኖቻቸው) የሚያምኑበትን፥ እምነትና ሃይማኖት በፍቅርና
ስለ ፍቅር ሊሰብኩላቸው፣ የሰበኩላቸውንም በልባቸው ውስጥ እንዲታተም ማስተማር አለባቸው። ተስፋ ስለሚያደርጉት ስለ ሠማያዊት
መንግሥተ ሠማያት በመናፈቅ ከዓለማዊ ምኞት በጸዳ ኹኔታ አስረግጠው ማስተማር መኾን አለበት!። ለምን ቢሊ፥ የሠው ልጅ በእዚች
ምድር እስከሚኖርበት ጊዜ ድረስ፦ ከተወለደበት ቀዬ ወደ ሌላ ቀዬ፣ ከነበረበት ከተማ ወደ ሌላ ከተማ፣ አድጎና ተምሮም የዕውቀር ማዕድ ካወቀባት ሀገር ወደ ሌላ ሀገር ሲሄድ የሚያጋጥሙትና በሕይወቱ የሚከሰቱ ክስተቶች ብዙ ነገሮች አሉʼ። ከክስተቶቹ አንዱ ደግሞ እምነትና
ሃይማኖት ነው፤ በዚህ ጊዜ የ“ሃይማኖት፥ የነፃነት ምርጫ” ወደሚለው ክስተት ራሱን ይፈልጋል።
በሀገሩም ይሁን ከሀገሩም ውጭ፤ ባጋጠመው በዚህ የ“ሃይማኖት፥ የነፃነት ምርጫ” ክስተት ፍለጋ ከእናትና ከአባቱ የወረሰው
ሃይማኖት ይኹን፣ በተለያየ ምክንያት የተቀበለውን እምነትና ሃይማኖት ይዞ ቢጸና እሰየው ያስብላል። ከእዚህ በተረፈ ሃይማኖቱን
በየትኛውም መንገድ ከተማም ውስጥ ይኹን በየትኛውም ሀገር ላይ በሕይወት እስካለ ድረስ እምነቱንና ሃይማኖቱን ሊቀይር ይችላል፤
ወደ ሌላ እምነትና ሃይማኖት ራሱን ቀየረ ማለት የራሱን መንገድ ፈለገ ማለት ነው። የፈለገውን ሃይማኖትና እምነት የመከተል
ከአምላክ የተቸረው ልዩ ሥጦታ ነው። ይኼን ሥጦታ ደግሞ የቀድሞ ቤተ-ሃይማኖቱ ከቻለች በድጋሚ አስተምራ በቀድሞው እምነትና
ሃይማኖት እንዲጸና ማድረግ አለበዚያ ግን ለየአንዳንዱ ሠው ከአምላክ የተቸረውን የእምነትና የሃይማኖት ነፃነትን በጸጋ መቀበል
አለባት።
ቢጣፍጠንም ቢመረንም፦ የሠውን ልጅ የእምነትና የሃይማኖት የነፃነት ምርጫውን ማክበር አለብን! ሊከበርለትም ይገባል!። በእስልምና
“ሼሪዓ”ግን
የዚህ የተለየ ነው። የቀድሞውን
ሃይማኖቱን ብቻ በመቀየሩ ምክንያት፦ እንደ ማፊያ ቡድኖችና እንደ ወንጀለኛ ድርጅቶች፤ ከዚህ ሃይማኖታዊ ድርጅት ከወጣህና ወደ
ሌላ ሃይማኖት ከሄድህ ውርድ-ከራስህ፤ ዐይነት ነገር ይባላል። እንደ ማፊያዎቹ አባባል፦ “ምስጢር ታወጣለህ፣ አልያም ሀገርን
ለጠላት አሳልፎ እንደሸጠ” ተቆጥሮ፤ የሞት ፍርድ ይበየንበታል። [፩] ዶ/ር ዛኪር እንዳሉት።
የ“ሃይማኖት፥ የነፃነት ምርጫ” ከዶ/ር ዛኪር በፊት የነበሩት የሙስሊሞች መምህራን እንኳን የሠዎችን የእምነት ነፃነትን
በመንፈግ እምነቱን ለሚቀይር ከፊቱ ላይ የመቃብር ቁፋሮ እንዳለ ያመላክታሉ። እንደተናገሩትም፥ እንደዚህ እያሉና እያስባሉ፦
“አንገትህን በሠይፍ እንቀላለን፣ በሕይወት የመኖርህ ህልውና ነገር ያከትማል፣ አትኖራትም፣ ንብረትና ልጆችህ ለሃይማኖታዊ
ድርጅቱ” በማለት ጊዜ ያለፈበትና ሃይማኖቱን ለዘላቂያዊ በፖለቲካ ለማካሄድ የነደፉት፦ ሃይማኖታዊ የሚመስሉ፥ ኢ-ሃይማኖታዊ፤
ጽንሰ-ሐሳብቦችን ማርቀቅ ለምን? እንደፈለጉ አማኙ ሙስሊሙ ሕብረተሰብ
እንዴት እስከዛሬ አይረዳውም!!!።
ኢ-ሃይማኖታዊ ሕጎችን ማርቀቅ፦
ቁርዐን መለኮታዊ ቃል ነው ብዬ አላምንም፤ (ይኼን ስል፦ ቁርዐንን ስለማላምንበትም ነው፥ ሌላ የመለኮታዊ ቃል የተቀበልኩት፤ እንዲህም ስል ደግሞ ቁርዐንን
የተቀበሉት ሙስሊሞች የሌላው ቤተ-እምነት የመለኮት ቃል ነው ብለው እንደማይቀበሉት ማለት ዐይነት ነው።) “ቁርዐን
መለኮታዊ ቃል አይደለም” ብለው የሚያምኑ ግለሰቦችም ይኹኑም ቡድኖች ተነስተው ደግሞ “እኛ የማናምንበትና ያተቀበልነውን እንዴት
ሌላው ይቀበላል” ብለው በኢ-አምልኮታዊ (ኢ-ሃይማኖታዊ) ስም በኾነ መንገድ በመደራጀት፤ ቁርዐንን የሚቀበሉትን ኹሉ
ኢ-አምልኮታዊ ናቸውና በማለት ሙስሊሞችን ለመጉዳት የታለመ የ“ሼሪዓ” ዐይነት
ሕግ ቢያቋቁሙ እኔ በበኩሌ አልስማማም!።
(እንደማይኾንም እርግጠኛ ነኝ! ምክንያቱም፥ የእምነትና የሃይማኖት ነፃነት መንፈግና መከልከል ከቅዱሳት ብሉያት መጽሐፍት እያጣቀሱ
መጠቀም በተቻለ ነበር፣ ለእንደዚህ ዐይነት ሕጎችን ለማርቀቅ ይመች ነበር፤ ነገር ግን የሰዎችን ደም ለማፍሰስ፣ ለማሰቃየትና ለመግደል፤ ከብሉያት ወደ ክርስትናው ዓለም አልተቀደም። ወደ ክርስትናው ቢቀዱ ኖሮ
ከ“ሼሪዓ”ው ዐይነት በላይ ሕግ በረቀቀ ነበር።
ግን፥ በክርስትና ውስጥ፥ አልነበረም፣ አልኾነም፤ አይኾንምም!።)
በተቃራኒው ግን የእስልምናው “ሼሪዓ”ው ግን የሃይማኖት
ሕግና ቅጣት በማሰኘት፣ ከእስልምና ውጭ ያሉትን (በእስልማናም ውስጥ “ሼሪዓ”ው ሕግ
የማይቀበሉትንና በእስልምነታቸው ያሉʼ ግን ስማቸው የተለያዩትንም ያካትታል) ኢ-ሃይማኖታዊ ናቸውና ተብሎ ለመቅጣት እንዲያመች፤
ኢ-ሃይማኖታዊ፣ ኢ-ፍትሃዊ፣ ኢ-ሰብዓዊ፣ ኢ-ሞራላዊ፣ ኢ-ስብህናዊ፣ ኢ-ህልውናዊ፤ የሚነኩ ሕጎችን በማርቀቅ “ሼሪዓ”ው አርቅቆ በስራ ላይ አውሎታል። እንደዚህ ዐይነት ሕጎችን ለማርቀቅ ደግሞ በጣም
የቀላሎች ኹሉ ቀላል ነገር ነው!። ለ“ሼሪዓ”ው የሚከብደው ግን፦ ፍቅር የኾኑ፣
ፍትህ የሰፈነበት፣ አድሎአዊት የማይታይበት፣ ለሰዎች ስብህና የቆመ ሕግ ማርቀቅ ከባድ ለምን ይኾንበታል?።
እስልምናና ፖለቲካ፦
የእስልምናን
ሃይማኖት ከፖለቲካ ጋር አዳቅሎ መሄድ የተለመደ ነገር ነው። ከመሀመድ ጀምሮ እስካለንበት ዘመን፣ ሠዓትና
ደቂቃ እንኳ አብረው በማቀናጀት በመስራት
ላይ ናቸው። በእስልምና ውስጥ የፖለቲካውን ዕርዮተ-ዓለምን
በመጨመር
የ“ሼሪዓ”ው ሕግ በማለት ታውጇል። ይኼ አዋጅ የእስልምናን ተከታዮቻቸውን በአንድ ሰንሰለት-ዕዝ
በማቀፍ ለማስተዳደር የታሰበ ነው። ቢኾንም ግን በ“ሼሪዓ” ሕግ ላለመመራት የሚፈልጉትን፣ አልያም በእስልምና በ“ሼሪዓ”ው አስተምህሮት
ወጣ ያሉትን ለመቅጣትም የታለመ ሕግ ነው።
ዑስታዝ አቡ ረሺድ በፓልቶክ ያሰሙትን ንግግራቸው፦ እስልምና ከፖለቲካው እዳልተለያየ ከሰለሀዲን ዘመን ወይንም ከሰለሀዲን ዘመን በኋላ ያለው የተቆራኘ ታሪክ በማውሳት "የእስልምናን ሃይማኖት ከፖለቲካ አይለይም፤ ፖለቲካውም፥ ከእስልምና ሃይማኖት ጋር አይገነጠልም!፤ ፖለቲካውን ከእስልምና ሃይማኖት የመገንጠሉ ጉዳይ፦ ይኼ ናራቢዊያን (ምዕራብያዊያን) የፈጸሙብን ጉዳይ ነው። እስካሁን ድረስ የቆላ ቁስል ኾኖ የኖረብ በዚህ የተነሳ ነው። የማይድን ቁስል! ሃይማኖቱን፥ ከፖለቲካው የለየን ዕለታ፤ የዚያን ዕለታ፥ የሙስሊሙ ዓለም እንዳለ ይወድቃል፤
የበታች ይኾናል።"
[፪] ሲሉ ይተነትናሉ። ታዲያ እንደ ርሳቸው አባባል፦ የእስልምናን ሃይማኖት ከፖለቲካ፤ ፖለቲካን፥ ከእስልምና ሃይማኖት ጋር እንደማይለያይና ይልቁንስ የእስልምናን ሃይማኖት ከፖለቲካ የተለያየ ዕለት ታላቅ ቁስል ይኾንበታል ሲሉ ያስገነዘቡት፤ ከመጀመርያው
ጀምሮ እስልምና
እንዴት ከፖለቲካው ጋር ያለው መስተጋብሮሽ እውነታና ሃቁ ዑስታዝ አቡ ረሺድ እንዳሉት ይኼን ይመስላል።
በእስልምና
ውስጥ ብዙ ዐይነት እስልምናን እናገኛለን፤ ከፓኪስታን እስከ ህንድ፣ በአንዳንድ ሙስሊም ሀገራትም በአስተምሮት የተለያዩ ሙስሊሞቹን እናያለን። ታዲያ እነዚህ በአስተምህሮት የተለዩ ሙስሊሞች አንዱ ከአንዱ ጋር በአስተምህሮት
አለመስማማት
ብቻ ሳይኾን እስከ ኃይል
መጠቀምና እስከ
ከባባድ ነገሮች ውስጥ ሲገቡ እናያለን። ለምሳሌ፦ በእስልምና ስም ያሉ ቢያንስ ስድስቱን ከታች እንመልከት፦ (ምናልባት በስም ያልተጠቀሱ ሌሎችም
ይኖሩ ይኾናል።)
፩፤ ሱፊ (ሱፊያ)
፪፤ ሰለፊ
፫፤ ሺሃ
፬፤ አህባሽ
፭፤ ወሃብያ (ወሀቢ)
፮፤ ሱኒ፤ ናቸው።
እንግዲህ ከላይ በስም በስም ያየናቸው ትንሹን ነው፤ እነዚህ እስልምና
ይከተሉ እንጂ አንዱ
ከአንዱ አስተምህሮታቸውም
የተለያየ ነው። አንዱ ከአንዱ መናፍቅ (ከሀጂ) እየተባባሉ በከባድ ነገር ሲጎዳዱ እንሰማለን፣ እናነባለን፣
እንመለከታለን፤
የዚህ ኹሉ ጣጣው የ“ሼሪዓ”ው ሕግ “የሃይማኖት፥ ነፃነትና ምርጫ” መከልከሉና የቅጣቱ ጣርያው ወሰን ያለፈ መኾኑ ነው።
በእስልምና
ሀገራት ከላይ በስም ያየናቸው አንዱ ጎልቶ መውጣት ስለሚፈልግ በሌሎቹ የእስልምና ሃይማኖቶች ላይ “የሃይማኖት፥ ነፃነትና ምርጫ” እጦት በማድረግና በመንፈግ፤ ከብዕር እስከ ጦር ዘመቻውን ይከፍትባቸዋል።
በ“ሼሪዓ”ው ሕግ፥ ኢ-ሃይማኖታዊ ሕጎችን፦ የሠዎችን የሃይማኖት ነፃነት የሚጋፋ፣ የሠላም ሃይማኖት
ድርጅት መስሎ የሠዎችን የመኖር ህልውና በድርጅታቸው (በሃይማኖታቸው) እጅ እንዳለ በመንገርና በማስነገር፤ ሠዎች “የሃይማኖት፥
ነፃነትና ምርጫ” እንዳያገኙ፣ እየተሳቀቁ እንዲኖር፣ ይኼንን ሃይማኖት ጥሎ መሄድ በሕይወት የመኖርና የመቆየት ጊዜያት የሦስት
ቀን እድል ናቸው፤ በማሰኘት በ“አደጋና በሞት አፋፍ” ላይ መኾናቸውን ይሰብካሉ።
ሃይማኖታዊ መስለው፥ ኢ-ሃይማኖታዊ መኾኑ በጣም ቀላል መኾኑን ከተረዳን፤ እነዚህ ቡድኖች፥ በቡድን በመደራጀት፣ ሃይማኖታዊ
የመሰለው፥ ኢ-ሃይማኖታዊ ድርጅታቸውን ብቻ ለማጎልበትና ለማጠንከር፣ በዓለም ላይ ለመብዛትና ለመንገሥ፣ ዓለምን ለመቆጣጠር ሲሉ
ድርጅታቸውን የሚደግፉ፣ ያሚያግዙ፣ የሚያጸኑ፣ የሚያካብቱ፣ ከድርጅታቸው አባል ውጭ የኾኑትን ለመጉዳትና ደብዛቸውን ለማጥፋት፤
በድርጅቱ ውስጥም ያሉትን ደግሞ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ እንዲኖሩ በማድረግ፣ ከረር ያለ ሕጎችን በማርቀቅ “ሼሪዓ”ና ብቸኛው የ“ሼሪዓ”
ሕግ በሚል ዐይነት መጠሪያ ሥም በመሰየም፤ የሃይማኖት ነፃነት እንዳይጎናጸፉ፣ የሃይማኖት ምርጫው ከቶ እንዳይታሰብና የማይታሰብ እንዲኾን፣ የሃይማኖት ነፃነት፥ የሚባል ነገር ይቅርና እንኳን ሊመርጡ ሊያስቡት የማይገባ ታላቅ ክህደት ነው በማለት በ“ሼሪዓ”
ይከለክላል። ይኼ ክልከላ ደግሞ፥ የሃይማኖት ነፃነት መምረጥ የክህደትና የሞት ብይን የሚያሰጥ ስለኾነ፦ የመራጩ የሠውዬውን፥ እምነቱን፣
ኅሊናው፣ አዕምሮው፣ ስብህናው፣ አጠቃላይ ማንነቱ የሚፈታተኑ ጥያቄዎች እያነጎዱበት፣ ለሦስት ቀን ወደ እምነቱ (እስልምና)
እንዲመለስ እድል እንዲያገኝ ይመቻችለታል፤ አለበለዚያ ግን ሠውዬው የእስልምናን እምነት አልፈልግም ብሎ ከጸና የሚወሰንበት ውሳኔ
አንገቱን እንዲቀላና እንዲሞት ይወሰንበታል።[፫]ግን ለምን?
በእነዚህ በሦስት ቀናት ውስጥ፦ የሃይማኖት ነፃነትና ምርጫ ሳይኾን የሚያደርጉለት፤ ሃይማኖቱን ለምን እንደማይፈልገው ለምን
እንደቀየረ ይጠየቃል። በመቀጠል ደግሞ፥ የገንዘብ እጦት፣ የኑሮ አለመመቻቸት፣ ሥጋዊ ምቾቶች ከጎደሉበትም አለንልህ ይባላል። መራጩ
ሠውዬውን ግን የሃይማኖት ነፃነትና ምርጫ የናፈቀው እንደኾነ ካሳወቃቸው፤
ውዱ የነበረው ባልደረባቸውና አባላቸው፤ በሥጋዊ ምቾቶች፥ በገንዘብና በኑሮ አለመመቻቸት እንዳልኾነ፣ “የሃይማኖት ነፃነትና
ምርጫ” እንደሚፈልግ ካበሰራቸው፤ የርሱ ነገር አበቃለት። ውዱ የነበረው ባልደረባቸውና አባላቸው ግብዐተ-መሬቱ ይማስለታል፤ በሕይወተ
ሥጋ የመኖሩ ነገር እንዳከተመ ይነገረዋል። ግን ለምን? “የሃይማኖት ነፃነትና ምርጫ” ስለ ሻተ ብቻ!።
ሌላው ደግሞ በሙስሊሞች ዘንድ፦ “ማንም ሠው ሲወለድ ሙስሊም ነው" [፬]
የሚሉ ሲኾኑ፤ ይኼ አባባላቸው ደግሞ በ“ሼሪዓ”ዎች ሙስሊሞች ዘንድ ጎልቶ የሚነገር
ነው። በሌላ አነጋገር በእዚች ዓለም ላይ የሚገኙ የሠው ልጅ ላይ እስላምነታቸውን እንዳወጁ ልብ እንበል!። አንድ ህፃን
ከተወለደበት ሰከንድና ደቂቃ ጀምሮ እስላምቱን አስረግጠው ሲናገሩ በዛው መልዕክታቸው ውስጥ የሚያስተላልፉት መልዕክት ቢኖር፦
እስላም ባልኾኑና እስልምናን ባልተቀበሉ ሕዝቦች ላይ ያላቸው “ሼሪዓ”ዊ ጽንሰ-ሐሳባቸውን ለመረዳት በጣም ቀላል ነገርነው።
ይኼውም፥ አንድምታቸው የሚያንጸባርቀው ወደ ግብዐተ-መሬት እየቆፈሩልን እንደኾነ እየነገሩን ነው። ምክንያቱም፥ እንደ “ሼሪዓ”
አመለካከት “ማንም ሠው ሲወለድ ሙስሊም” ስለኾነ፣ ሙስሊም ባልኾኑ ሠዎች ላይ ጥላቻቸው የሚበረታው ለዚሁ ነው። “ማንም ሠው
ሲወለድ ሙስሊም ነው” እያሉና እያስባሉ፤
ሙስሊም ባልኾኑ ሠዎች ላይ የሞት ፍርድ እየፈረዱብን ነው።
ምክንያቱም፥ በእስልምና “ሼሪዓ” ሕግ እናትና አባት እስላም ከኾኑ አልያም ከእናትም ይኾን ከአባትም ከኹለት አንዳቸው
እስላም ከኾኑ በተወለደው ህፃኑ ልጅ ላይ ሙስሊምነቱ ይጸናበታል። (በሴቷ በኩል ጭርሽ ወደ ሌላ፥ በሃይማኖት ከማይመስላት ሠው
ጋር ሄዳ ልትወልድ ይቅርና ፍቅረኛ እንኳን ይዛ ብትገኝ “ሼሪዓ”ው አይጣል ነው!፤ ለሴቷ የሚጥልባት ሕግ ከባድ ነው!።) የኾነው
ኾኖ ግን ከወለዱ በኋላ፥ የሚወለደው ልጅ እስላምነቱ በ“ሼሪዓ”ው ተቀባይነት ይኖረዋል። አድጎም ቢኾን ወደ ሌላ ሃይማኖት መኼድ ግን በፍጹም አይችልም። እናትም ይኾኑ አባታም
ወደ ሌላ ሃይማኖት መኼድ በ“ሼሪዓ”ው የሞት ፍርድ ስለኾነ፤ በፍጹም አይታሰብም።
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ይቀጥላል ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ዋቢ፦
[፩] ዶ/ዛኪር
[፪] ዑስታዝ አቡ ረሺድ
[፫] ሼህ ሳዲቅ ሙሀመድ
[፬] ኻሊድ ካሳሁን
No comments:
Post a Comment