የ“ሼሪዓ”ው እስልምና ለክርስትና እና ለሌላው ቤተ-ሃይማኖት ያለው አመለካከት በጣም የተዛባና ፍጹፍ የኾነ ጥላቻ ነው።
“ሼሪዓ”ው፥ ያስከተላቸው፣ እያስከተለ ያለውና የሚያስከትላቸው መዘዞች ብዙ ናቸው፤ ይኼንንም የምለው እንዲሁ ከመሬት ተነስቼ
አይደለም። በ“ሼሪዓ”ው እስልምና የሃይማኖት ሊቃውንቶቻቸው ዘንድ ስለ ክርስትና፦ የሚጽፉት፣ የሚናገሩት፣ እንዲሁም አጠቃላይ በሌላ
ቤቴ-ሃይማኖቶች ላይ ያላቸው አስተምህሮ መንፈሳዊነት አይታይባቸውም። ለዚህም ማስረጃ ይኾነኝ ዘንድ፦ የ“ሼሪዓ”ው አፍቅሪያን ግለሰቦችና ቡድኖች፥ የሌላ ቤተ-ሃይማኖት ማየት ያስጠላቸዋል፣ ይቀፋቸውማል።[፭] በዕንባና በለቅሶ፥
በታላቅም ጩኧት እየጮኡ የሳውዲው ዋሀቢ ሰባኪ፥ ክርስቲያኖችንና አይሁዶችን የሚረግም ከሱራት ቁራን እየጠቀሱ በስሜት ተውጦ ሲያለቅሱ
እንደነበር [፮] እና የ“ሼሪዓ”ው እስልምና አፍቃርያን ቡድኖች፤ በክርስቲያኖች ቤተ-ሃይማኖቶች ላይ የቃጠሎ፣ በክርስቲያን አማኞች ላይ ደግሞ፥
የትንኮሳ፣ የማሰቃየት፣ የመደብደብ፣ የመግደልና ከቀዬ የማባረር ተልኳቸውን ሲፈጽሙ እንዳየን፤ የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ነው። [፯]
የፖለቲካ ሠዎች የተባሉት፦ እነ አቶ ጀዋር መሐመድ እና የፖለቲካ አጋሮቻቸው፤ የፖለቲካ ሰዎች መስለው ለመታየት ሞክረው ነበር። ሃይማኖታዊያን ከሚመስሉ፥ ከኢ-ሃይማኖታዊ
ከኾኑ ግለሰቦችና ቡድኖች ጋራ በማበር፣ የፖለቲካ ጽንሰ-ሐሳቦቻቸውን
በማርቀቅና የፖለቲካ ጥላቻ አመልካከታቸውን በእስልምና ሃይማኖት ላይ በመጫን፤ በክርስቲያኖች ላይ የቃላት ጦርነት ሲሰነዝሩና ሲዶልቱ ዐየናቸው፤
ሰማናቸው።
የእነ አቶ
ጀዋር መሐመድ፥ የፖለቲካ ጽንሰ-ሐሳቦቻቸውንና የጥላቻ አመልካከታቸውን በሙስሊሙን ሕብረተሰብ በመጫን፣ በእስልምናና በክርስትና በቤተ-ሃይማኖቶች ላይ ግጭት እንዲፈጠር፣ ሕዝቡ እርስ-በርስ እንዲበላላ፣ ደም መፋሰስ እንዲኖር፣
እልቂት እንዲነግስ፤ ለማድረግ የነደፉትን የጥላቻ ንድፍ-ሐሳብቸውን
ሲዶልቱና ሲያስዶልቱ እጅጉን ታዘብናቸው።[፰] ይልቅስ፥ የእነ አቶ ጀዋር መሐመድ፥ የፖለቲካ ጽንሰ-ሐሳቦቻቸውንና የጥላቻ አመልካከታቸውን፤ ሠላም ወዳጆች ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻችንና
ኅህቶቻችን ሙስሊሞችም ሳይቀሩ ነው የተቃወሟቸው። (መኾንም ያለበት
ተቃውሞ!)
እነ አቶ ጀዋር መሐመድ እና የፖለቲካ አጋሮቻቸው፤ ውድ ቅኖችና
ገርዎችን የሀገራችን ሕዝበ-ሙስሊሙ ሕብረተሰብ፥ በክርስቲያኖች ላይ በጥላቻ እንዲነሱ፣ ክርስቲያኖችንን ለማጥፋት፦ "በሜንጫ፥ አንገት አንገታችንን እንዲጨፈጭፉ" የጥላቻ ስብከታቸውን ሰበኩ፣
እኛን ክርስቲያኖች፥ በታላቋ ኢትዮጵያ ሀገራችን፣
በውቧ ክልላችን በኦሮምያ ላይ እንዳንኖር ህልውናችንን ለመሻር ሲዳክሩ፣ በሕይወት እንዳንኖር፥ ድራሻችንን
ከነ አካቴው እንድንጠፋ የጥላቻ
ስብከታቸውን አስተጋቡ። ሀጅ ነጂብ በተራቸው፦ ''የኢትዮጵያ
ሕዝብ ህብረተ-ሰእብ በትንሹ
ሃምሳ ሚሊዮን ይኾናል፣ ከዚህ ሃምሳ
ሚሊዮን ውስጥ ሰማንያ
ፐርሰንት (80%) ኦሮሞ ነው,,,,''
ሲሉ ተደምጠዋል። በማስከተልም፦ “የቀረው ሃያ
ፐርሰንት (20%) የትም ሊደርስ አይችልም” ሲሉ እንደተናገሩት ልብ እንበል!። እንግዲህ እንደነ አቶ ጆዋር መሐመድ እና የፖለቲካ አጋሮቻቸው ዐይነቶች፤ ኢትዮጵያን ሊያስተዳድሩ ሥልጣን ቢኖራቸውና ቢችሉ ኖሮ የሃይማኖት ነፃነት ምን እንደሚመስል ቡዙ መተንተን አልያም ነብይ መኾን አያስፈልግም።[፱]
እኛስ ግን እንዲህ እንላቸዋለን፥ እነ አቶ ጆዋር መሐመድና የፖለቲካ አጋሮች ሆይ፦ አንድነትና ሕብረትን፣ ሠላምንና ፍቅርን ስበኩ!!! እባካችሁ እነ ጆዋር ይኼንን የጥላቻ አመለካከታችሁን ከኅሊናዎቻችሁ፣ ከአዕምሮዎቻችሁ፣ አስወጡና በፍቅርና ስለ ፍቅር ለውጡት እንጂ!።
አንዳንድ የ“ሼሪዓ”ው እስልምና አፍቃርያን ቡድኖች፤ በፓልቶክ የሚያሰሙትን ንግግራቸውም እንዲሁ ጥላቻ የተሞላበት
ነው። በእስልምናና በክርስትና በቤተ-ሃይማኖቶች ላይ ግጭት እንዲፈጠር፣ ሕዝቡ እርስ-በርስ እንዲበላላ፣ ደም መፋሰስ እንዲኖር፣
እልቂት እንዲነግስ፤ ለማድረግ የነደፉትን የጥላቻ ንድፍ-ሐሳብቸውን
እና በሕይወት የቀረውን ክርስቲያኖችንን ከያሉበት
ከዐረብ ሀገራት ተለቃቅመው ወደ ሀገራቸው
በማስመለስ፤ ተጠርዘው የመጡትን ሕዝበ-ክርስቲያኑን በወረደ ድርጊቶቻቸው በግዴታ ወደ እስልምና ለማስለም የዶለቱትንና
ያለሙትን
ዕቅድና አላማቸውን በይፋ አሰምተው ገልጹት።[፲]
የሃይማኖት፥
ነፃነትና ምርጫ፤ በ“ሼሪዓ” ሕግ መከልከል ለምን?
በሙስሊም “ሼሪዓ” ሕግ “የየሃይማኖት፥ ነፃነትና ምርጫ” የለም! የ“ሃይማኖት፥ ነፃነትና ምርጫ” አንድ አማኝ ሙስሊም ከፈለገ በነኚህ ቡድኖች፦ ለሞራላዊ ዝቅጠትን፣ ለስብህናዊ ጥሰትን፣ ለአካላዊ ጉዳትን፣ ለአዕምሮአዊ ሁከትን፣
ለማህበራዊ ግንኙነት ቀውስን፤ እንዲኹም ደግሞ፥
ከቀዬ ማባረርን፣ ለከባድ ግርፋት፣ ለእስር፣ አንገትን
በገመድ አንጠልጥሎ መግደል፣ አንገትን በሠይፍ መቅላት፣ በአሰቃቂ ግድያዎች ተፈፃሚነት እንዲያገኝ፤ በሕጋቸው ውስጥ በማካተት
“የሃይማኖት ነፃነትና ምርጫ” ለማፈን የተጠነሰሰ፣ ሕግ ነው። በዚህ ሕግ የሚጠቀሙበት የሠው ደም የሚናፍቃቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ያቀናጁት ሤራና
ዶሴ መኾኑን እንዴት አይገባንም? “የሃይማኖት ነፃነትና ምርጫ” በሌለባት እምነትና ሃይማኖት መሳይ የኾነች፤ ኢ-ሃይማኖታዊ ነው! ከማለት ውጪ
“ትክክለኛና የሠላም እምነትና ሃይማኖት” እንዴት ልንለው እንችላለን? እንዴትስ በዓለም ላይ በእንደዚህ ዐይነት ኹናቴ ሠላም
ይመጣል? እንዴትስ ርኅራኄ ይገኛል ብላችሁ ታስባላችሁ?። እሳትና ጭድ አልያም እሳትና ቤንዚል ቢኾን ኖሮ የዓለማችን ገጽታ ምስቅልቅል ባለች ነበር።
አንድ ሙስሊም “የሃይማኖት፥ ነፃነትና ምርጫ” ቢሻ “ሼሪዓ”ው ሕግ ቅጣቱንና ውሳኔውን ስለሚያውቀው የ“ሼሪዓ”ዎች
እስልምና የሚደርጉትን እያየና እየሰማ፣ ነፍሱ እየተጨነቀ፣ ኅሊናው እየታወከ፣ በሚያደርሱት ስቃይና በደል፣ በመራራ ነገሮች ልቡ
እየተቅበዘበዘ እስከ-ዕለተ ሞቱ ድረስ “የሃይማኖት ነፃነትና ምርጫ” ሳያገኝ፣ የሃይማኖቱን አመጸኝነትና እውነትነቱን ትንፍሽ
ሳይልና ሳይናገር፣ በመጀመርያ ነፍሱ ወደ ነበረበት፣ በዚህች ምድራዊ መቃብር ሥጋው ተቀብሮ ነፍሱ አምላክ ፊት እስከምትቆም
ድረስ ምድርን ይሰናበታታል። ግን ለምን “የሃይማኖት ነፃነትና ምርጫ” ሳያገኝ ይሰናበታታል?።
“የሃይማኖት፥ ነፃነትና ምርጫ” ካለው፤ የፈለገውን ሃይማኖት ለመከተል ለምንድን ነው የሚከለከለው? በፈጣሪ
ዘንድ አዳምና ሔዋን (አደምና ሐዋን) ባለመታዘዛቸውን ምክንያት
አንገታቸውን በሰይፍ እንዳልተቀሉ እንዴት ልብ ልንል አንችልም ወይ! ይልቅስ እስከ ሕይወታቸው ፍፃሜ ድረስ ጠበቃቸው እንጂ!
ፈጣሪ ነው ከተባለ፦ “በአላህ፥ ስም በጣም ሩኅሩህ፣ በጣም አዛኝ በኾነው” [፲፩] (አል ፋቲሃ
1፥1) ከተነገረ፤ እስከ ምኑ ድረስ ነው፥ በጣም
ሩኅሩህ፣ በጣም አዛኝ የሚባለው? በምንስ ይታወቃ አዛኝነቱንና ርኅራኄቱ? እንዴትስ ይታወቃል ፍቅር መስጠቱ? ሲያመሰግኑትና
ርሱን /አላህን/ ሲያመልኩት ብቻ ነው ወይ? ትህዛዛቱን ያልጠበቁት አዳምና ሔዋን (አደምና ሐዋን) ስለምን አልቀጣቸውም ይኾን?
ይኼማ እንኳን ፈጣሪ የተባለ ግብዞችስ ይህን ያደርጉ አይደለምን? ሠው፥ በሕይወት እስካለ ድረስ “የሃይማኖት፥ ነፃነትና ምርጫ”
ከተከለከለ፤ “አላህ”ም፥ ከዚህ እስልምና ውጪ ያሉትን ክርስቲያኖችንና መጽሐፉ የመጣላቸውን /አይሁድን/ እረዷቸው፣ ግደሏቸው
የሚል ከኾነ፤ መጀመርያውንስ ሠዎችን ለምን ፈጠረ? ዓለምንስ ለምን አዘጋጀ? ለምንስ በዓለም የሚኖሩትን የሠዎችን “የሃይማኖት፥
ነፃነትና ምርጫ” በግድ ለመንፈግና ለማፈን ፈለገ? “አላህ” ፈጣሪ ከኾነ፥ ፍጥረቱን ለምን በደም መፋሰስ እንዲያምን ያደርጋል?
ለምንስ ከሌሎች ሠዎች ጋራ ያላቸውን ማህበራዊም ይኹን በማንኛቸውም ትውውቅ ላይ እንደ ሠውነቱ ከመተዋወቅ ይልቅ “እስላም
ነህ?” ብለው እንዲጠይቁ ለምን ያስሮጣቸዋል?።
እንግዲህ የ“ሃይማኖት፥ ነፃነትና ምርጫ”ን የተጠማ ነፍስ (ሙስሊም) የነፍሱን ቁስል የሚያድንለትን ሃይማኖት ሳይኾን
ይኖራል። ይኼ አማኝ፦ በፍርሃትና በመሸማቀቅ የሚኖር አማኝ ይኾናል፤ ሲሞት፥ ነፍሱ ግን ወደ አምላኩ ዘንደ ለፍርድ እስኪቀርብ
ድረስ፤ ባልና ሚስት፣ ሕዝብና ነገድ፣ ቤተ-ስእብና ቤተ-ዘመድ፣ ጓደኛና ወዳጅ፣ ሕዝብና መንግሥት፣ መንግሥትና መንግሥት፤ በዚህ
በ“ሼሪዓ” ሕግ ጥላሸት በመቀባባት የሚያመጣው ጣጣው ብዙ ነው። በከርሰ-መቃብር ያለውማ ተገላገለ! ለምን ቢባል? አሁን የሃይማኖት ምርጫ የለበትም፤ ከፊቱ የሚጠብቀው ነገር ቢኖር ከፈጣሪው የፍርድ ቃል እስኪሰማ ድረስ ነፍሱ እንደ
እሱ ያሉትን ነፍሳትን ይጠብቃል፤ የዛን ጊዜያትም የሚሰማው መለኮታዊ ድምጽ ብቻ ነው። በሕይወት ያለው ግን “የሃይማኖት፥
ነፃነትና ምርጫ” ለማግኘት የሚያደርገው ሱታፌ (ተጋድሎ) ከሞተው ይልቅ በሕይወት ላለው በ“ሼሪዓ”ው ጣጣው ብዙ ነው።
ለአንድ እናትና አባት
ወይም ቤተ-ሰእብ፤ ልጃቸው፥ የቱንም
ያህል ኢ-አማናዊ ቢኾን፣ የቱንም ያህል
ሰዎቹን ሳይበድል፣ “የሃይማኖት፥ ነፃነትና ምርጫ” በመሻቱ ብቻ፣ ወንጀለኛ ነው ተብሎ፤ በሕግ ፊት አቅርበውት የግርፋትና የሞት ብይን ቢፈርዱበት ቤተ-ሰእብ በልባቸው እያለቀሱ፣ መሪር ኅዘን ይተሰማቸው፣ በሃይማኖት ማስገደድ ሥም፥ ያጡትን ውዱ ልጃቸውን የት ይኾን፦
“አቤት፥ የፍርድ ያለ! የፍትህ ያለ! የአምላክ ያለ! የሀገር ያለ!” የሚሉት?። በሃይማኖት ሥም፥ አስታኮ ሲወርድ ሲዋረድ
የመጣውን የንጹሃንን የሠዎች ደም ማፍሰስ ያመጣው ይኼ የ“ሼሪዓ” ሕግ ቤተ-ሰእቦቹ ያለምንም አማራጭ እንዲቀበሉት ያስገድዳል። ለቤተ-ሰእቦቹና
ለዘመዶቹ፣ ለጎደኞቹና ለወዳጆቹ ግን፥ የግፍ ግፍ ነው! የአመፆች ኹሉ ዋነኛ አመፃ ነው!፤ ለምን? “ምን ይደረጋል!” ብለው ብቻ
በጸጋ ከመቀበል ውጪ በ“ሼሪዓ” ሕግው አማራጭ የላቸውም።
አንዳንድ ሙስሊም ወገኖቼ፦ “በሃይማኖት ሥም ማስገደድ የለም! የሠው ልጅ፥ የፈለገውን ሃይማኖት፣ በነፃነትና ባሻው ምርጫ
በገዛ-ፍቃዱንና ነፃነቱን ተጠቅሞ የሚፈልገውን እምነትና ሃይማኖት ማመንና መከተልና መብቱ ነው!” ብለው እውነቱን ሲናገሩ፤ አንዳንድ
ሙስሊሞች ደግሞ፦ የለም! የምን “የሃይማኖት፥ ነፃነትና ምርጫ”
አላህን ብቻ ይከተላል ወይም ትከተላለች!። ከዚህ ውጭ የምን ሃይማኖት! በእስልምና ቤተ-ሰእብ ከተወለደማ፤ ፈለገም አልፈለገም፣
እስከ ሕይወቱ መጨረሻ ይከተላል፤ ወደ ሌላ ሃይማኖት እሄዳለው ካለ በሕይወት የመኖሩ ህልውና የሦስት ቀን ዕድል ይሰጠዋል”
ይላሉ።
እንግዲህ እንደ እነዚህ ሠዎች አባባል፦ በሃይማኖት ማስገደድ ካለ፥ ምኑን ሃይማኖት ኾነ? እንዲያስገድዱስ፥ የሠውን
ክቡር ህልውናን፣ ስብህናን፣ ኅሊናን፣ የሚፈታተን፤ የሞት ሽታ የነገሰበት፥ የሞት ሽታ የሚሉ ቃላቶች ተናግሮ በተግባር
ለመፈጸም፣ የሚነሳ እጆችና እግሮች ኧረ እንዴት ያለ ሃይማኖተ ነው? ይኼ ነው ታዲያ የሠላም ሃይማኖት የሚባለው ወይ? የዚህን
ልጅ፥ በኢ-ፍትሐዊ፣ ፍርደ-ገምድል ፍርድ፣ የፈረደበት፥ የተወላገደ የ“ሼሪዓ”ው ሕግና ዳኞች፤ ምን ያህል ለሠው ልጅ ስብህናና ህልውን፣
የማያስቡ እንደኾኑ ይታያሉ። ፍርደ-ገምድል፣ አድሎአዊ፣ ፍትሐዊ ያልኾነና ጭካኔያዊነት የተሞላበትና የተላበሰበት፣ ፍርድ ነው!።
በ“ሃይማኖት፥ የነፃነት ምርጫ” መከልከል በ“ሼሪዓ” ሕግ መሰረት የግርፋትና በሞት ብትገደልበት፣ እንግዲህ ይህ ውድ
ወዳጅና ፍቅረኛውን፣ የትዳር አጋሩን፣ የሕይወት መሠረቱን፣ የልጆቹን እናት፤ በሃይማኖት ሰበብ ምክንያት ቢያጣት፦ የኅሊና
ሁከት፣ የመንፈስ ጭንቀት፣ ለ“ሼሪዓ”ው ሕግና ለሃይማኖቱ በመጀመርያ ከነበረው ከፍተኛ አመለካከት ወዲያውኑ በመቀየው የወረደና
ዝቅተኛ አመለካከት እንዲኖረው ያስገድደዋል።
ይኼ ሠው ውዱና አፍቃሪ ባለቤቷ ነው፤ ኅሊናውና አዕምሮው ሲሟገተው እንዲህ ብሎ እንዲያስ ያደርገዋል፦ “ፈጣሪ፥
የሚታመነውና የሚከበረው፣ የሚመለከውና የሚወደደው፤ ከንፉግ ሰውና ከልበ-ሰፊ ከኾነ ሠው ካነሰ ምኑ ላይ ነው አምላክ የኾነ?
ደግሞስ በፍቅር መሐል አብሮ መኖር ሳያቅተን በአምላክ ሥም ምክንያት እንዳጣት የሚያደርጉት ኧረ ለምንድን ነው? እንዳጣትና
እንድለያት እንኳን ቢፈልጉ ስለምን የሞት ድግስ ይደግሳሉ? ደግሞስ በሃይማኖትና በፍቅር መኖር ቢያቅተን በሠላም መንገድ
መለያየት እያለ? ልጆቼስ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህፀኗ ተሸክማ፣ ወልዳ፥ ጡት አጥብታ፣ አዝላ እየተንከባከበች፣ በፍቅር
አሳድጋ፤ ሙስሊምነታቸው በጨቅላ ዕድሜያቸው ሳሉ ያለ ልጆቼ ፍቃድና ዕውቅና የሚታወጅባቸው ኧረ ስለ ምንድነው? እኔስ አባታቸውም
ብኾን የሃይማኖት ነፃነታችን እስከምን ድረስ ነው?” እያለ፤ ስለ “ሼሪዓ”ው አድሎአዊነት ሕግ ብዙ ያስባል፤ በእስልምና “ሼሪዓ”ው
ውስጥ ያሳለፈው የሕይወት መንገድ ሳይኾን የያገኘው የሞት መንገድ እንደኾ ነው የሚረዳው።
ምርጥና ድንቅ፣ ሠላም ፈላጊ የኾኑ ሙስሊሞች አሉ። (ጥያቄዬ ለእነዚህ ብቻ ነው) ሙስሊሞች፥ ክርስቲያን ከኾኑ ሠዎች
ጋር ተጣምረው በፍቅር የኖሩና እየኖሩ ያሉ ብዙዎች አሉ፤ የሃይማኖት አጥራቸውን ለየቅል አድርገው ትዳር መስርተው በጣፈጠ ፍቅር
የሚኖሩ፣ ፍቅረኛ ያላቸው፣ የልቦናቸውን፣ የኅሊናቸውን፣ የአንጀታቸውን፣ የሚገላለጹና የሚነጋገሩ፣ የችግርና የደስታ ተካፋይና
ተጋሪ የኾኑ፣ ወዳጅና አፍቃሪ ልቦና ያላቸውን፤ ውድ ሙስሊሞች ወገኖቼ በጥሞና እና በአርምሞ እንድትመልሱልኝ የምሻለሁ ጉዳይ
አለ። የ“ሼሪዓ”ው ሕግና “የሃይማኖት፥ ነፃነትና ምርጫ” መከልከል፣ እንዲሁም ደግሞ “በሃይማኖት ሥም ማስገደድ” ትክክል ነው
ብላችሁ ታስባላችሁ? ሕጉና ቅጣቱስ ታምናላችሁ?
እስቲ አስቡት ወንድሞቼና ኅህቶቼ (ሙስሊሞችንም ይጨምራል)፦ እንደዚህ ዐይነት ነገር በምትወዳትና/ጂው
በምታፈቅራት/ሪው፣ ውድ፥ የትዳር ባለቤትህና/ሽ፣ የልጆችህ እናት ብትኾን አልያም የልጆችሽ አባት ቢኾን ኖሮ፤ ምን ይሰማችሁ
ነበር??? እንደዚህ ዐይነቶችን ሠዎች ስንቶቹን አውቃላችሁ? ከቤተ-ሰእብ ጀምሮ እስከ ዘመድ፣ ከወዳጅ ጓደኛ ጀምሮ እስከ
በዐይን እስከምታውቋቸው ሠዎች ስንቶች ይኾኑ? የ“ሼሪዓ”ው ሕጉ ተፈፃሚነት እንዴት ነው ልባችሁን በኅዘን አይሰበርም ወይ?
ሙስሊም ኾንክ፣ አይሁድም ኾንክ፣ ክርስቲያንም ኾንክ፣ ኢ-አማንያዊያንም ኾንክ፤ በዚህ ምድር ላይ የምንኖረው አንድ
ጊዜ ብቻ ነው። ነገር ግን የሚመጣውን ሠማያዊት መንግሥት ለመውረስ በዓለም ሳለን መልካም ነገሮችን በማድረግ በመንፈሳዊ ጎዳና
መመራት ይጠበቅብሃል እንጂ ዕድሜ ዘለዓለማችንን በምድር ላይ አንኖራትም! ከመቶ ለሚያንስ ለምንኖርባት ዓለም ፍቅርና ሠላም፣
ሕብረትና አንድነት፤ ተማምሮ ወደ መጣንባት መሄድ ይሻላል እንጂ! ያውም ከመንፈሳዊያን ሠዎች እጅግ ስለ ፍቅር በትጋት ማስተማር
እንጂ!።
ለማሳያ ያህል፦ በሱዳን ሀገር ለአንዲት ክርስቲያናዊት “የሃይማኖት፥ ነፃነትና ምርጫ” በሱዳን ሃይማኖቴን አልቀይርም
በማለቷ የሞት ፍርድ የተፈረደባት[፲፪] መርየም ኢብራሂም ነፃ ልትወጣነው ሲል ቢቢሲና የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘግበውታል። [፲፫] ግን እኮ ይኼንን ያደረጉት፥ ሱዳን ከተለያዩ ዓለማት ያላትን ዲፕሎማሲያዊ
ስለሚቀዘቅዝና ስለሚጎዳባት፣ እንዲሁም ደግሞ የገንዘብ እርዳታና ጉርሻ ስለምትከለከት ስለምታውቅ፤ ታላላቅና ኃያላን የሚባሉት
ሀገራት ራሳቸው በሱዳን መንግሥት ላይ ታላቅ ጫና በማድረጋቸው እንጂ
የሱዳኑ የ“ሼሪዓ”ው ሕግ ፈቅዶ አይደለም!። (ቢፈቅድ እሰየው ደግ አደረገ፤ የ“ሼሪዓ” ሕግ በታወጀባቸው በሀረብ
ሀገራት ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ማስተማር ሕጉ አይፈቅድም፤ ነገር ግን አሁን አሁን በጥቂቱም ቢኾን ሻል ያለ ይመስላል።) የ“ሼሪዓ”ውን
ሕግ ምን ያህል ከየሀገራትና ከዓለማት ዲፕሎማሲያዊ ጋር እንዴት እንደሚያሻክር ልብ በሉ!። ለዚህም ነበር የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ
ምክትል ሚኒስትሩ አብዱላህ አል አዝራቅ ‹‹ጉዳዩ ውስብስብ ነው፣ ጎሳንና ማኅበራዊ ሕይወትን ይነካካል፤ በመሆኑም የሞት ፍርዱ
ተፈጻሚ አይሆንም›› ሲኩ የገለጹት።[፲፬] (እንደ አፋቸው ካደረጉት ጥሩ ለውጥ ነው።)
ጎሳንና ማኅበራዊ ሕይወትን የሚያነካካ ከኾነ ሃይማኖትንስ አይነካካም ትላላችሁን? ቢጣፍጠንም ቢመረንም፦ የሠዎችን ልጅ
የእምነትና የሃይማኖት፥ የነፃነት ምርጫውን ማክበር አለብን! ለዚህም ደግሞ ግንባር-ቀደም ትክክል ያልኾነው፣ በሠው ልጆች ላይ፥
የደም መፍሰስን የሚናፍቀው፣ አፉን ከፍቶ የሞት ፍርድ የሚፈርደውን፣ አድሎአዊው የግድያና የሞት ሽታ የሚሻውን የ“ሼሪዓ”ውን
ሕግ ሊያርሙትና ሊያስተካክሉት፣ ይገባቸዋል!፤ ቢችሉ ደግሞ ነቅሰው ማውጣትና ማስወገድ አለባቸው!። “የተሻሩት” ሕግ እንዳላቸው
ሁሉ፤ ለዚህ ዐይነቱ የሠዎችን ደም መጣጭ ለኾነው ሕግ ደግሞ ከተሻሩት ሕጎቻቸው ውስጥ ቢያጠቃልሉት እነሆ፦ አንድ እርምጃ
ይራመዳሉ! በ“ሃይማኖት፥ ነፃነትና ምርጫ” እና “በሃይማኖት ሥም ማስገደድ የለም!” የሚባለውን
ከቃል ይልቅ
በተግባር ሲተገብሩት ደስ ሊያሰኝ ይችላል።
ምስጋናዬ፦ ለአንዳንድ ሙስሊሞች የ“ሼሪዓ”ውን የፍርድ ብይን በመቃወም፥ በቃል፣ በጹሑፍና በተለያየ መንገድ ሐሳባችሁን
የገለፃችሁ፤ እንዲሁም ደግሞ ፍርዱ “ትክክል አደለም ብዬ ብናገር የሼሪዓውን እስልምናን ሙሉ ለሙሉ የተቃወምኩኝ ስለሚመስላቸው”
ብላችሁ በዝምታ ውስጥ ኾናችሁ፤ በልቦናችሁ የ“ሼሪዓ”ውን አድሎአዊው ሕግ ትክክል እንዳልኾነ፤ “በሃይማኖት ሥም ማስገደድ
የለም!” እያላችሁ፤ ለኅሊናችሁ፣ ለልባችሁ እውነቱን ያስረዳችሁ፤ ላቅ ያለ ሠላምታዬ ይድረሳችሁ! ቸርን ሁሉ እመኝላችኋለሁ፣
በሠላም፥ በፍቅርና ስለ ፍቅር ከያላችሁበት ሠላምታዬ ይድረሳችሁ!!!
ለሀገራችን ኢትዮጵያ፣ ለአህጉራችን ለአፍሪቃ፣ ለዓለማችን፦ የሠውን ልጅ በ“ሃይማኖት ሥም ማስገደድ” ሳይኖር የፈለገውን
“ሃይማኖት፥ በነፃነት ምርጫ” እንዲጠቀም፤ ምኞቴም፣ተስፋዬም፣ እምነቴም፤ ነው!
<<<<<<<<<<<<<<<<<<< ይቆየን >>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
No comments:
Post a Comment