Wednesday, June 18, 2014

"ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።" /፩ኛ ዮሐ ፭፥፲፱/



(በ፰//፳፻፮ / [15/6/2014 EC] በጣሊያን ሮማ ከተማ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፥ የደብረ ከነዓን ቅድስት ሥላሴ / ቅጽር ግቢ ካነሳዋቸው ፎቶዎች።)

ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በአንደኛው መልእክት በምዕራፍ አንድ ቁጥር አስራ ዘጠኝ ላይ እንዲህ ይላል፦ "ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።" /፩ኛ ዮሐ ፭፥፲፱/

አምላካችንና መድኃኒታችን፣ መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በዚህ ዓለም ላይ በነበረበት በሥጋ ወራት፤ "የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ" /፩ኛ ዮሐ ፫፥፱/ ይህ የተገለጠው፥ አምላክና መድኃኒት ነው። አልፋና ኦሜጋ ነው፣ አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው ነው፣ መጀመሪያውና መጨረሻው እርሱ ነው፤ እኔ ነኝም ይላል። /ራእ ፳፪፥፳፫/ እርሱ ከዳዊት ዘር የተወለደው፦ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የድንግል ማርያም ልጅ፣ አማኑኤል የተባለው፤ እርሱ መድኃኒትና ፈዋሽ፤ ለዓለም የተሰዋ በግ ነው።

ይኼ ሥም፥ አጋንት የሚንቀጠቀጡበት፣ ኃያላን በረዓድ የሚርበተበቱበት፣ ነገሥታት ጉልበታቸውን የሚያንበረከኩለት፣ ጥበበኞች መዕባ የሚያቀርቡለት፣ ምላስ ሁሉ የሚያመሰግነው፣ ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘለዓለም አባት፣ የሠላም አለቃ፣ አማኑኤል፣ ኤልሻዳይ፣ አዶናይ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

"ስለዚህ፥ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ" /፩ኛ ዮሐ ፫፥፱/ ለሠው ልጅ ጠላት የኾነው ርኩስ መንፈስ ቀርቦ፦ "ዲያብሎስም ረጅም ወደ ሆነ ተራራ አውጥቶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው።" ብሎ፤ ዲያብሎስ፥ ራሱን የስልጣን ባለቤት እንደኾነ በመቁጠር፤ ከአምላካችንና ከጌታችን ጋር ስለ ዓለማት ነገሥታት ክብርና ዝና፣ ላልተገባ የክፉ ስግደት እንዲሰግድለት በጠየቀው ጊዜ አምላካችን ክርስቶስ "ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል" /ሉቃ ፬፥፩-፲፫/ ብሎት፤ የዲብሎስን የተንኮል ሥራ እንዳፈረሰ፣ ርኩስ መንፈስ እንደገሰጸና ለመንፈሳዊ አባቶች ስልጣንን፣ ለእኛ ለምዕመናን አማኝ ደግሞ እንዴት መጽናት እንዳለብን የነፍሳችን መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ በቃል፣ በምግባር፤ አስተምሮናል።

አምላካችን መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ተወልዶ የእግዚአብሔር የራሱን መንግሥት ለልጆቹ ያወርስ ዘንድ፤ በምግባር፣ በቃል፣ በሥራ ራሱን ለእኛ ሲል አሳልፎ ነፍሱን በገዛ ፍቃዱ እስኪለይ ድረስ መግቦቱን ሳያቋርጥ በበረከት አትረፈረፈው። በዓለም ሳለን (መንፈሳዊነትን መተውና መናቅ፥ የዓለምን ምኞትትንና ዝባዝንኬውን መውደድ) ሥጋና ነፍሳችን ዲያብሎስ ወደ ሲኦል አውርዶ የግብር ልጆቹ አድርጎን ነበር። ግን ግን "የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ" /፩ኛ ዮሐ ፫፥፱/

ይኼ የተገለጠው፥ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ "ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው" ተብሎ እንደፃፈ፤ ለሐዋርያትና ከሐዋርያትም በኋላ ለአባቶቻችን እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ስልጣንን ቷቸዋል። ሐብተ-ፈውስ ጸጋ በመጽሐፍ ቅዱስ፥ በሐዲስ ኪዳንና በስንክሳር በታሪክ መጽሐት ውስጥ ተመዝግበው እናገኛለን። ለሐዋርያቶች፥ ለነ ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ለነ ቅዱስ ጳውሎስ፤ የተሰጠው የጸጋ ሥልጣንና ሥጦታ በእነርሱ ብቻ አላቆመም። ከእነርሱ በኋላ ለተነሱት ቅዱሳን አበውም ሐብተ-ፈውስ የጸጋ ሥልጣንና ሥጦታ ተሰጥቷቸዋል፣ ሥልጣንም ነበራቸው። ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱን እንመልከት፦

፩፤ ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝንዊ፥ በደብዳቤ ጋኔን ስለማውጣቱ

በምናኔ ኑሮ፥ በምንኩስና ሕይወት ገዳም አቅንቶ፤ ይህ ቅዱስ አባት ሚልኪ ቁልዝንዊ ይኖር እንደነበረ ስንክሳር የተባለው የቤተ-ክርስቲያናችን የታሪክ መጽሐፍ ይገልጽልናል። አባ ሚልኪ፥ አጋንንትን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የማስወጣት ጸጋ ነበረው። ከሩቅ ሀገር ሠዎች ወደ እርሱ ዘንድ መጥተው በአጋንንት ስለተለከፉት ወገኖቻቸው ሲነግሩት፤ አባ ሚልኪ፥ በአቱን ለቆ ላለመውጣት በደብዳቤ “የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ሚልኪ ቁልዝንዊ፥ በፈጣሪዬ  ሥም ከበሽተኛው (በርኩስ መንፈስ የያዝከው) ለቀህ ውጣ! ብሎሃል” ብሎ ይጽፍና ይሰጣል (ይልካል)። ሠዎች ያንን ደብዳቤ ይዘው ከሀገራቸው ሲደርሱ በበሽተኞች (በርኩሳን መንፍስ በተያዙት) ላይ ያነባሉ። አጋንንቱም፦ “ሚልኪ ቁልዝንዊ አምላክ አነደደን፣ የአባ ሚልኪ ጸሎት ድል አደረገን” በማለ ለቀ ይሄሉ።ኞች፥ ተረፈ ደባቸ  ይድሉ። ንንቱም የተመላለ ራቸውም። (መጽሐፈ ስንክሳር፥ ስለ ቅዱስ ሚልኪ፤ መስከረም ፩ ላይ የተመዘገበ።)
፪፤ ቅዱስስ ዘገብሎንም፥  በደብዳቤ ጋኔን ስለማውጣቱ
ቅዱስስ ዘገብሎን፥ ጋኔን (ርኩስ መንፈስ) ያወጣ ነበር። ቅዱስስ ዘገብሎን፥ እንደ ሚልኪ ቁልዝማሚ በክርታስ ላይ ጽፎ አጋንንትን (ርኩስ መንፈስ) ያስወጣቸው ነበር። “ሳዊሮስ ዘገብሎን፥ የናዝራዊ ኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ! አንተ ርኩስ መንፈስ ውጣ ብሎሃል” በማለክርስ ይልል። ብ፣ ፎ ወደ ሩቅ ሀገ ለወዳጆና ለደቀመዛሙርት  እንደመላ ማለው።ቤውኮ በጋኔን ከታመሙት ሕሙንድ  ነበብ፤ የሳስ ዘገብሎን ጸሎት አነደደን፣ የሳስ ዘገብሎን አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈረደብን፣ ወጣን፣ ለቀቅን እያሉ፤ እየለፈለፉ አጋንንቱ በሽተኞችን ለቀው ይወጣሉ። ሕሙማን (በአጋንንት የተያዙ) ወዲያውኑ ፈውስ ያገኛሉ። ከዚያ ወዲያ ፍጹም ጤነኞች ኾነው ይኖሩ ነበር። (መጽሐፈ ስንክሳር፥ ስለ ቅዱስስ፤ መስከረም ፯ ላይ የተመዘገበ።)
እነዚህ ሁለቱ ቅዱሳ አባቶች፥ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈር የእግዚአብሔር ነዋ በጊዜው ዘመኑን እየዋጁ፥ የርኩሳንን መንፈስ በመገሰጽ፣ የአጋንንት የመሰሪነት ሥራ ከሠዎች ላይ በማስወጣት፤ የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር በደብዳቤ ጋኔኖችን ስለማውጣታቸው ነው።
የሳይንስና የቴክኖሎጂ ዕድገት በሰለጠነበትና በተስፋፋበት በዚህ ጊዜ፤ እግዚአብሔር አምላክ፥ የዘመናት አምላክ ነውና ልጆቹ ዘመኑን እንዲዋጁ፣ ዘመናትን እንዲቀድሙ እንጂ ዘመን እንዳይቀድማቸው፣ በልዩ የጸጋው፥ ሥልጣንና ሥጦታ ስለቸራቸውና ስላደላቸው፤ በዘመናችንም አባታችንን መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙንና ሌሎችም አባቶችን አስነሳልን

ስለዚህ በክርስቶስ ስልጣን፥ አጋንት ሲሽመደመዱ፣ ወደ ሲኦልና ወደ ማረፊያዬ ልግባ እያሉ ሲቅበዘበዙ፣ ወደ ቤቴ ልሂድ እያሉ እንደነበሩት ሁሉ፤ አሁንም መግቦቱ የማያልቅበ የዓለም ቤዛ ኢየሱስ ክርስቶስ በአባቶቻችን ላይ እያደረ ልጆቹን እያስነሳ፦ የመተትን፣  የቡዳን፣ የጥንቆላን፣ የመስተፋቅርን፣ የዛርን፣ ቢን፣ የዓይነ ጥላን,,,,, አጠቃላይ፤ "የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርሱ" አባቶቻችንን እያስነሳ ነው። በእኛ ዘመን ትውሉዱን ይታደጉት ዘንድ፦ አባታችንን መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙንና ሌሎችም አባቶችን አስነሳልን። እነዚህ አባቶች እንዲህ ይላሉ፦ "ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።" /፩ኛ ዮሐ ፭፥፲፱/ ቃሉ ስለሚል፤ አባቶቻችንም ከእግዚአብሔር ጋር ስለኾኑ ዓለም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እያሳዩን ነው። የዲያብሎስን ሥራ እያፈርሱ እየሰማን፣ እያየን ነው። እየው,,,, እንደዚህ በአርምሞ ተሰብስበን፣ በተመስጦ ተመስጠን፤ የመድኃኒታችን የመድኅነ ዓለም የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር በዓለም ላይ ይብለጥ እየተገለጠ እያየን ነው!

ጌታ ሆይ፦ ለአባታችን ሠላምና ጤና እንዲሁም የአገልግሎት ዕድሜያቸውን አርዝምልን፤ እንደነዚህ ያሉትን አባቶቻችንን አብዛልን፣ ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ለቤተ-ክርስቲያናችን፣ ለሀጉራችን ለአፍሪቃ፣ ለዓለማችን፤ ሠላምን፣ ፍቅር፣ አንድነትን ስጠን!!!
 
ክብር ለታረደው በግ፣ ድንግል ልጅ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን! አሜን፥ ተመስገን!!!

4 comments:

  1. ቃለ ህይወት ያሰማልን

    ReplyDelete
  2. GOD HEAR MY PAYER

    ReplyDelete
  3. ቃለ ህይወት ያሰማልን
    መልካም ሰው መልካም ይናገራል

    ReplyDelete