Sunday, December 1, 2013

ሰብአዊ መብት፥ "አላህ"ን እናመልካለን በሚሉት ዘንድ፦


"አላህ" እናመልካለን በሚሉት ዘንድ (ሁሉንም "አላህ" እናመልካለን የሚሉትን አይደለም። ውድ ሙስሊም ጓደኞቼ ይቅርታ አድርጉልኝ፤ ይህን የፃፍኩ "አላህ" የሚያመልኩ ሠዎች፣ በአብዛኛው በዓለም ታሪክ የደረሰውን፣ እየደረሰ ያለውን፣ የተመዘገበውና በገሃዱ ዓለም ካየሁት፣ ከሰማሁት፣ ካነበብኩት፤ እውነታ በመነሳትና በመቃኝት ነው እንጂ!)

"አላህ" እናመልካለን በሚሉት ዘንድና፥ እኔ በምኖርበት ሃገረ ጣልያን፥ የመጀመርያ ጥያቄያቸው አንድ አይነት እየሆነብኝ ነው። ምክንያቱም፥ ጣልያኑም ይሁን ስደተኛው፦ የመጀመርያ ጥያቄያቸው "የት ሃገር ዜጋ ነህን?" ሲሉ "ዘረኞች" ካስባላቸ፤ ሙስሊሞች ደግሞ የመጀመርያ ጥያቄቸው፦ "ሙስሊም ነህን? ነው። ታዲያ እነዛን "ዘረኞች" ከተባሉ እነዚህንስ ምንበላቸው? "አላህ" እናመልካለን በሚሉት ዘንድ፥ ቶሎ ብለው ሲተዋወቁህ ሙስሊም ነህን ነው ብለው ነው እንጂ እንደ ሰውነትህ መተዋወቅ አይፈልጉም፤ ይህም ማለት ደግሞ ለሰውነት ዋጋ እና እውቀና አለመስጠት ነው።

"አላህ" እናመልካለን በሚሉት ዘንድ፥ የሠዎች ሰብአዊ መብት እና የመኖር ስብዕና የተረጋገጠ አይደለም! "አላህ" እናመልካለን በሚሉት ዘንድ፥ ከእነርሱ ውጭ ያሉት፤ ቤተ-እምነቶችንም ለማጥፋት ዋነኛ ዓላማቸው ነው። "አላህ" እናመልካለን በሚሉት ዘንድ፥ በራሳቸው ቤተ-እምነት አስተምዕሮ ያለ ሠው ቢሆን እንኳን ካላመነበት በግድ እንዲቀበል፣ አልያም እንዲወገድ ይደረጋል። "አላህ" እናመልካለን በሚሉት ዘንድ፥ በነፃነት የመኖር ዋስትና አይታሰብም። "አላህ" እናመልካለን በሚሉት ዘንድ፥ በዓለም ላይ አብሯቸው በሚኖሩት ዘንድ፦ ሠላም ማሳጣት፣ ሁከት መፍጠር፣ የፍርሃት ድባብ ማሳደር፣ ድንጋጤ ማስረጽ፣ በተገኝው አጋጣሚዎች ሁሉ መረበሽ፤ ዋነኛ ስራዎቻቸው ነው።

"አላህ" እናመልካለን በሚሉት ዘንድ፥ ዓለም ለመቆጣጠር የቀየሱት እቅድ (እስትራዴጂ) በቤተ-እምነቶች መካክል ሰርጸው በመግባት ውዥንብርና መከፋፈልን መፍጠር ዓላማቸው ነው። "አላህ" እናመልካለን በሚሉት ዘንድ፥ ይህ ካልተሳካላቸው በሚዘገንን ሁኔታ ሠዎችን፥ በገንዘብ መደለል፣ ማሰቃየትና መስቀል፣ አስገድዶ መድፈር፣ እንግልት ማድረስ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ መግደል፣ ከገደሉ በኋላም፥ ጭራሹን ኢ-ሰብአዊ የሆነ ድርጊቶቻቸውን ማሳየት የእምነታቸው መለኪያ ነው።"አላህ" እናመልካለን በሚሉት ዘንድ፥ በራሳቸው ቤተ-እምነት ተቃውሞ ማሰማት አይቻልም፤ ካሰሙም ጉዳቸው ይፈላል።

"አላህ" እናመልካለን በሚሉት ዘንድ፥ ለምሳሌ፦ በሊቃውንቶቻቸው ዘንድ፥ ከላይ የገለጽኳቸውም ይሁኑ ያልገለጽኳቸ -ሰብአዊ ድርጊቶች ሲፈጸሙ እያዮና እየሰሙ፣ እያነበቡና እየታዘቡ፣ ዝም ማለታቸውና አለማውገዛቸው፤ ከሃይማኖታቸው ፍራቻ የመነጨ ነው። 
                                                                                                                                                                  
"አላህ" እናመልካለን በሚሉት ዘንድ፥ አንዳንድ ሊቃውንቶቻቸው ዘንድ፥ የሰሙትንና የተመለከቱትን፣ ያነበቡትንና የታዘቡትን፣ -ሰብአዊ ድርጊቶች ፈፃሚዎችን ሲያወግዟቸው፤ ከስልጣናቸው መሻራቸው የሃይማኖት ሊቃውንቶቻቸው እንደማያከብሩ እናያለን  (“ወሲባዊ ጂሃድ /ጂሃድ አል-ኒቃ/” በሶሪያ! በሚለው የተዘገበውን ጹሑፍ ማንበብ ብቻ፥ ከበቂ በላይ በቂ ነው። ሙፍቲ ሼክ ዖትማን ባታኪ ወሲባዊ ጂሃድ /ጂሃድ አል-ኒቃሴተኛ አዳሪነት ወይም ዝሙት እንደሆነ መግለጻቸውን ተከሎ የገማቸ ነገ ር፦ በሥልጣናቸው አለመ ውና።)


                          Source፦ “ወሲባዊ ጂሃድ /ጂሃድ አል-ኒቃ/” በሶሪያ! 



Saturday, November 30, 2013

ፕሮቴስታንቶች (ተሐድሶ) የተሟላ መጽሐፍ ቅዱስን አይቀበሉ፦



ፕሮቴስታንቶች (ተሐድሶ) በሐዲስ ኪዳን ውስጥ በማስረጃነት ደረጃ የተጠቀሰ ጥቅስ የለም ይላሉ። ይህ አባባላቸው የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን በደንብ ካለማንበባቸው የተነሣ እንጂ በብዙ ቦታዎች እንደተጠቀሱ ማስረጃዎችን ከብሉይ ኪዳንም ከሐዲስ ኪዳንም እንደሚከተለው መጥቀስ ይቻላል!

ፕሮቴስታንቶች (ተሐድሶ)፦ ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚፈልጓቸውን ብቻ በመውሰድ ሌሎችን ትተዋቸዋል። በመሆኑም እነርሱ በሚቀበሏቸው እና ቤተ-ክርስቲያናችን በምትቀበላቸው መጻሕፍት ቁጥር መካክል ልዩነት አለ።

1.        የፕሮቴስታንቲዝም መስራች ማርቲን ሉተር ለእርሱ ትምህርት የማይመቹ የመሰሉትን መጻሕፍት እያወጣ ይጥል ነበር። ለምሳሌ፦ የያዕቆብ መልእክት ስለ ምግባር አስፈላጊነት ሰለሚያስተምርና ይህም ማርቲን ሉተር ስለ ጸጋ እና እምነት በቻ ይሰብከው ከነበረው ትምህርቱ ጋር አልሄድ ስላለው መልእክቱን ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አውጥቶት ነበር። እንዲያውም “Epistle of straw ገለባ መልእክት” ብሎ እስከ መጥራት ደርሶ ነበር።

2.      አንዳንድ ወገኖች ከ66ቱ መጻሕፍት ውጭ ያሉትን መጻሕፍት “አፖክሪፓ” ብለው ይጠሯቸዋል። ይህ ግን የተሳሳተ ስያሜ ነው። “አፖክሪፓ” በጥንት ዘመን ምሥጢራዊ ለሆኑት የጥንቆላ መጻሕፍት የሚሰጥ ስም ነውና። እኛ ግን፥ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍቱን፦ “ሁለተኛ የቀኖና መጻሕፍት - ዲዮካትሮኒካል” እንላቸዋለን።

3.      የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁለት ዓይነት የኖና ክፍሎች አሏቸው። እነርሱም፦ የመጀመርያ-ፕሮቶካኖኒካል፣ እና ሁለተኛ- ዲዮካትሮኒካል ይባላሉ።

Tuesday, November 26, 2013

ከቤተ-ክርስቲያን የተገኙ ልጆቿ፦


ከጻድቁ ኢዮብ ትምህርትና ምክር የተነሳ፥ በዙሪያው የነበሩትን የነነዌ መርከበኞችን፣ ነጋዴዎችን፣ መኳንቶችን፣ ከደቂቅ እስከ አዋቂ፣ አጠቃላይ በወቅቱ የነበሩትን ስለሁናቴው ሲገልጽል "ሰዎች፥ እኔን ሰምተው በትዕግሥት ተጠባበቁ፥ ምክሬንም ለማዳመጥ ዝም አሉ።" ብሎ ተናግሯል። ነቢየ ዕንባቆም "እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ ምድርም ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል።" /ዕን 220/ ብሏል። በማቴዎስ ወንጌልም፥ ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ ሰለ አምላካችንና ስለ መድኃኒታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የባህሪው አምላክነቱንና ሲያመለክት፤ "ኢየሱስም፦ ዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሠጸው።" /125/ ይላል፤ እዚህ ጋር እርኩሳንነን አጋንትን በቃሉ የሚያዝ ስለሆነ "ዝም በል ከእርሱም ውጣ" ብሎ ገሠጸው እንጂ "አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ" /ዮሐ 1723/ ይህንን አጋንት፥ አሶጣልኝ፣ ላሶጣ፣ ወይንም እናውጣ፤ ብሎ አልጻፈልንም፣ አልሰበከንምም። የሆነው ሆኖ ግን ይህንንም ሥልጣነ ፈውስ (አጋንትን መገሠጽ) ራሱ ባለቤቱ የሰጣቸው ጸጋ ነው።

እንግዲህ የእግዚአብሔር ልጆች በተቀደሰ መቅደሱ ቤተ-ክርስቲያን ያሳደገቻቸው ልጆቿ፥ ሲናገሩ፣ ሲያስተም፣ ሲዘምሩ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ከአንደበታቸው ሰምተው በትዕግሥት ይጠባበቃሉ፣ ምክሩም፥ ግሩምና ድንቅ ከመሆኑ ብዛት የተነሳ ለማዳመጥ ዝም ይላሉ! ምድሪቱንም በቃላቸው ይገስጿታል፥ ከመገሰጿም የተነሳ በፊታቸው ዝም ትላለች። እንዲሁም ከራሱ ከባለቤቱ የተቀበሉት ጸጋ ነውና፥ እነ ቅዱስ ጳውሎስ አጋንትን ሲገሥጹ እንደነበር በዘመነ ሐዲስ ተመዝግቦልናል። በዘመናችንም የተባረኩና የጸጋ ተካፋይ በሆኑት አባቶች ሥልጣነ ፈውስ (አጋንትን እየሠጹ) ዝም ሲያስብሉና ሲያሶጡ እያየን ነው፥ ደግሞም የእግዚአብሔ እጅ መች ይታጠፍና፤ ገና እናያለን።
 
 
እነዚህ ሁሉ፥ ከአንዲት፣ ከቤተ-ክርስቲያን የተገኙ ልጆቿ ናቸው፣ አምላካቸውና መድኃኒታቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ብዙ ሞግዚቶችና አእላፍት አሏቸው!





Sunday, November 24, 2013

ስለ ጾም ጠቃሚ ምክር፦



1. ጾም ማለት ከእግዚአብሔር የታዘዘ እውነተኛ ሕግ ነው። ነገር ግን የሥራውን ፍሬ መጀመሪያ እንገልጻለን፤ ጾም ማለት መጀመሪያ ዓይናችን ክፉ ነገርን እንዳያይ፤ ጆሮአችን ክፉ ነገርን እንዳይሰማ፤ አንደበታችን ክፉ እንዳይናገር መከልከል ነው እንጂ እንዲያው ሥጋና ቅቤን ብቻ መተው አይደለም።

መቼም የሰው ባሕርይ በዚህ ዓለም ሲኖር ሁል ጊዜ በደስታና በተድላ ለመኖር ነው የሚጥረው፤ ይኸውም ለሰው ልጅ ሐሳብ ሁለት መንገድ አለው፤ አንዱ በሕግ የተፈቀደ፤ ሁለተኛው በሕግ ያልተፈቀደ ነው። በሕግ ያልተፈቀደ ማለት እግዚአብሔርንና ሰውን የሚበድልበት የዓመጽና የኃጢአት ጎዳና ነው።

 አባታችን አዳም ከሕግ የወጣ መንገድ ያልታዘዘውን ሥራ ሠርቶ በልቶ ከገነት ወጥቶ ወደ ግዞት እንደሄደ ያመለክተናል። በሕግ የታዘዘ መንገድ ማለት ሰው በዚህ ዓለም ሲኖር ሀብታምም ቢሆን ወይም ድሃ፤ ያንኑ የመጀመሪያ ዕድሉ የሰጠውን ሀብት በምስጋና ተቀብሎ ፈጣሪውን እያመሰገነ በጾምና በጸሎት፤ ወይም በሐዘንና በደስታም ቢሆን እግዚአብሔርንና ወንድሙን ባይበድልና ሳያስቀይም ‹‹ላብህን ከግንባርህ ጠርገህ እንጀራህን ብላ›› /ዘፍ3፡19/ እንደተባለው ሕግን ቢፈጽም፤ እስከ ዘለዓለም የሕይወቱ ምንጭ ሳይደፈን ይኖራል።

የጥፋት ልጆች ዛሬ ግን ሰዎች ጾምና ጸሎትን እግዚአብሔር የማይፈቅደው ሕግ ነው፤ እግዚአብሔር የሚወደውና የታዘዘው ሕግ ያገኙትን ሁሉ ሳይጸየፉ መብላትና በደስታ መኖር ነው፤ ብለው በሆቴል ሜዳ ያገኙትን እንደ ጨፌ ሣር የለመለመ መብልና መጠጥ እየተመገቡ እናያለን። ነገር ገን ይህ እግዚአብሔር የሚወደው ሕግ ይሆን? በእውነት እግዚአብሔር የሚወደው ሰው አጭር ጊዜ በሆነ ሕይወቱ በዚህ ዓለም ላይ ሲኖር ለእርሱ ሲል የተሰቀለለትንና የሞተለትን ፈጣሪው ሁል ጊዜ እያሰበ በጾምና በጸሎት በሐዘንና በትዕግሥተ ሆኖ ወደ ፈጣሪው ዓይነ ሕሊናውን ሰቅሎ፤ ዘለዓለማዊ የሆነውን ብርሃናዊ ሕይወት ተጎናጽፎ መኖር ነው። በዚህ ዓለም ተድላና ሕይወት ለእኛ ነውና የተፈጠረው ብለው ሲፈነጥዙ፤ ቢኖሩ፣ ‹‹ሞት ሲመጣ ጥሩ ቄስ፤ ጦር ሲመጣ ግዙ ፈረስ›› የተባለው ተረት በእነርሱ ላይ ይፈጸማል

Tuesday, November 19, 2013

የተቃውሞ ሰልፍ በሮም ከተማ



       



       የተቃውሞ ሰልፍ በሮም ከተማ የሳዑዲ አረቢያ ኤንባሲ፤ በመሄድ የተቃውሟችን ድምፃችንን ለማሰማት፥ በሰልፍ ላይ ትውለደ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊን፣ ሃገር ቢለየንም ደማችን አንድ ነው ብለው ትውልደ ኤርትራውያንና ኤርትራዊያን፣ እንዲሁም በሰልፍ ላይ የተካፈሉ በርከት ያሉ የኢትዮጵያዊያን ወዳጆች ጣልያዊያን፤ አብረን ነበርን። ለሦስት ሰዓታት ያህል፥ በሳዑዲ ሃገር፦ በዜጎቻችን ላይ የሳዑዲ ሕዝብና መንግስት የሚደርሱባቸውን ጥቃት፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ ግድያ፤ በጥብቅ ተቃውመን፤ ለዓለሙ ሕዝብ በአጽኖት እንዲመለከተውና እንዲከታተለው እኛ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያን ወዳጆች በሙሉ፤ ተቃውሟችንን በጋለ ሃገራዊ የፍቅር ስሜት፣ በሠላማዊ መንገድ፤ በሚገርምና በሚያስደንቅ ሁኔታ አሰምተናል።

ይህንን ሃገራዊና የማንንታችንን ጥያቄ በመጠየቅ፥ ላስተባበሩና በተቃውሞ ሰልፍ ላይ የታደሙትን፣ እንዲሁም የሮም ከተማ አስተዳደርን እጅግ ከፍ አድርጌ ከልብ አመሰግናቸዋለሁ።