Sunday, February 8, 2015
Friday, January 23, 2015
"በርታ ሠውም ሁን"፦ (፩ኛ መጽ ነገ ፪፥፫) አስራ ኹለቱ ምክረ ዘ መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ
በርቱ፥ ሠውም ሁኑ! ሠው ለመኾን የሚከተሉትን መንገዶች እንኺድ፦
፩፤ አምልኮታችንን፦ እናክብር።
፪፤ የእግዚአብሔርን ቃል፦ ምግባችንን እናድርግ።
፫፤ የአሕዛብን መንፈስ፦ ከኅሊናችን ውስጥ እናውጣ።
፬፤ የሎጂክ ኑሮዎቻችንና የሎጂክ የእውቀት ጠባዮቻችንን፦ በእግዚአብሔር አምላክ መንገድ ላይ እንጣለው።
፭፤ የአባቶቻችንን መንፈሳዊ ታሪክ፦ እንደገና ለመገመትና ለማንሳት እንሞክር።
፮፤ የቤተ-እግዚአብሔር መንፈስን፦ በፍቅርና በጸጋ የምንመላለስበትን ጉልበት እንድናገኝ፥ እንበርታ፤ እንጸልይ።
፯፤ በንስሐና በቅዱስ ቁርባን፦ የተባረከ ትውልድ፣ ጊዜ፣ ዘመን እንዲኖረን፤ ዕቅድ (ፕሮግራም) እናውጣ።
፰፤ የዘወትር ዕቅዶቻችን፦ በእግዚአብሔር መንፈስ የተመራ እንዲኾን፥ በጸሎት ለእግዚአብሔር መንገዳችንን አደራ እንስጥ።
፱፤ የዕውቀታችንን ግማሽ፦ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት እንዲኾን ለማድረ፥ እንደገና አዕምሮዎቻችን ወደ አምላክ እንመልስ፤ የነፍስ ትምህርት እንዲኖረን፥ እንዘጋጅ።
፲፤ የዚህን ዓለም ሃብት፦ እንደ ዕለት እንጀራ እንጂ እንደ ዘላለማዊነት አስበን፣ በክፉ ምትአታዊ አኗኗርና ዲያብሎሳዊ ስሜትና ሐሳብ ውስጥ ገብተን የሟርት ኑሮን አንያዝ።
፲፪፤ የመንፈስ ቅዱስ መግለጫ እንድንኾን፦ ዘወትር በአካኼዳችን፥ የእግዚአብሔር ግርማ ሞገስ የተላበስን፣ በእምነቱና በቅዱስ ቁርባን ፊታችን የተባረከና የተሻሸ፣ ሠማያዊ ወዝ ያላቸው ልጆች እንዲፈጠሩና እንዲወለዱ፤ እግዚአብሔር አምላክን፥ እንማጸን።
እነዚህ ሂደቶች በሕይወታችን ውስጥ ካሉ፦ ሠው የመኾን ብርታትና እድላችን ሠፊ ነው።
-----------------------------------------------------------------------------------------------
(ምንጭ፦ ሬዲዮ አቢሲኒያ፥ መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ
መንፈሳዊ ትምህርት፤ ክፍል ፳፫)
----------------------------------------------------------------------------
Subscribe to:
Posts (Atom)