Friday, October 25, 2013

“ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሶዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሰራር”

              "ግብረ ሶዶማዊነት በኢትዮጵያ" በሚል፦ መምህር ደረጄ ዘወይንዬ፤ በግብረ ሶዶማዊያኖች፥ ላይ ባደረገው ጥናታዊ ዳሰሳ፣ ከድምጸ ተዋህዶ የሬድዮ ፕሮግራም አዘጋጆች ጋር ባደረገው የቃለ መጠይቅ ቆይታ፥ እንዴት ወደ ግብረ ሶዶማዊነት ሕይወት እንደገቡ፣ በግብረ ሶዶማዊነት ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል፣ ሥራዎቻቸውና እንቅስቃሴዎችቸውን፤ በተመለከተ ሰፋ ያለ፥ በተበራራና ግልፅ በሆኑ ቃላቶች፣ ግብረ ሶዶማዊያን ሕይወትና ተመክሮ በመነሳት፣ ስለ ግብረ ሰዶማውሪያን እንቅስቃሴ የሚያመለክትና ግንዛቤ የሚያስጨብጥ፣ ወደዚህ ሕይወት ለገቡት የመውጪያውና የማምለጫው በር፣ ወደዚህ ሕይወት ለመግባት ዳር ዳር ላሉ ደግሞ የደውል ምልክት ነውና። ታዲያ በግብረ ሶዶማዊያን ዙርያ የቀረበው በተጨባጭ ሁናቴ በመረጃና በማሰረጃ ስለሆነ ግንዛቤ እንዳስጨበጠን የታመነ ሃቅ ነው!


“ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሶዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሰራር” የሚለውን በደረጀ ነጋሸ ዘወይንዬ አዘጋጅና አቅራቢነት በቪዲዮ ወምስል ካቀረበልን ግብረ ሶዶማዊያን መካክል አንዱና ዋነኛ የሆነው አብይ (ኤሊያና) ስለራሱና ስለ ጓደኞቹ ስል ግብረ ሶዶማዊያን ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል፣ በእውነተኛ ታሪካቸው በተፃፈው መፅሐፍ አማካይነት ስለ ግብረ ሶዶማዊነት ሲናገር እንዲህ ነው የሚለው፦

* “ግብረ ሰዶማዊነት፥ እንደ ማግኔት ነው! አንድ ጊዜ ስቦ ካጣበቀ በኋላ የማይለቅ” ነው ብሎ ይገልፀዋል። (መፅሐፍ፦ የሰዶም ነፍሳት፥ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ)

Tuesday, October 15, 2013

“እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም”



(እውነት ነው እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም!!! እናሳ ከወለደች በኃላስ እንዴት አወቃት?)

አቤቱ ጌታችን ሆይ፦ ተቀዳሚ ተከታይ ስለ ሌለው ስለ ልጅህ ስለ ወደዳጅህ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ አማኑኤል ብለህ ይቅርታህን ከኛ አታርቅ፤ መሐላህንም አታፍርስ በእውነት ያለሐሰት።

በአብ በመንፈስ ቅዱስ ህልውና ሆነው የሚኖር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ። በሱም አብ መንፈስ ቅዱስ ህልውና ሆነው የሚኖሩ። ልቦናው አብ፣ ያንደበቱም ትንፋሽ መንፈስ ቅዱስ፤ የሚሆን ኢየሱስ ክርስቶስ። እርሱም የአብ የመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው የሚኖር ኢየሱስ ክርስቶስ።

በልዕልና ሳለ በመሠረት ያለውን የሚያይ። በውነት ከሰማይ በቸርነቱ ወርዶ ክብርት ድንግል ከምትሆን ከእመቤታችን በሰው ሥጋ ተወለደ። ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ ተወስኖ፣ ልጅነትን ሰጥቶ፤ በሥጋው ወገኖቹን ያደርግ ዘንድ።

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስም ልደቱ ነገር እንዲህ ነው፦ እናቱ እመቤታችን ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። ድንጋሌ ሥጋ ድንጋሌ ነፍስ ስላት። ከማየት፣ ከመስማት፣ ከመናገር፣ ከመዳሰስ፤ ድንግል ስትሆን።

ዕጮኛዋ ዮሴፍ ግን ደግ ሰው ነውና ሊገልጣት፣ ሊያጣላት አልወደደም። ሰውሮ ሊያኖራት ወደደ እንጂ! ይህንንም ሲያስብ እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ታየው፣ በሕልምም ተነጋገረው።

የዳዊት ልጀ ዮሴፍ ሆይ ዕጮኛህ ማርያምን መቀበል አትፍራ። ከሷ የሚወለደው በግብረ መንፈስ ቅዱስ ነውና። እነሆ፦ ወንድ ልጅ ትወልዳለች ስሙንም ኢየሱስ (መድኃኒት) ትለዋለች። እሱ ወገኖቹን ከኃጢአታቸው ፍዳ ያድናቸዋልና።

ይህ ሁሉ የተደረገው፥ ነቢይ ከእግዚአብሔር አግኝቶ፤ እነሆ፦ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል ብሎ የተናገረው ይደርስ፣ ይፈጸም ዘንድ ነው።

አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከኛ ጋር የሆነ ማለት ነው። ዮሴፍም ከእንቅልፉ ተነሥቶ የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዘው አደረገ። ዮሴፍም ለድንግልናዋ ሰገደ። ለንጽሕናዋ፣ ለቅድስናዋም። ተገዛ። ዕጮኛው የምትሆን ማርያምንም ወሰዳት። በኵር ተብሎ የተጠራ ልጅዋን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም። (ጻድቁ ዮሴፍ እመቤታችንን ድንግል ማርያም በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የመውለዷ ምስጥር፣ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት መሆኗን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፣ አልተረዳም ነበር።) /ድርሳነ ማሕየዊ ምዕ 113-38/



Monday, October 14, 2013

ምርጥና እጹብ ድንቅ አስር የአብው ብሂላዊ ምክር፦



1. ትግል፣ ተናና መከራ ከሌሉ የድል አክሊል፤ ጠላት ከሌለ ድል ማድረግ አይቻልም። /ታላቁ ባስልዮስ/

2. በመንፈሳዊ መንገድ ውስጥ ዝግ ብለህ አትጓዝ። በጎዳና ላይ በምትመለከታችው ትዕይንቶች አማካይነት አትማረክ፤ አትቁምም ጠላቶችህም ሆኑ ወዳጆችህም ያሰናክሉህ ዘንድ አትፍቀድላቸው። /አቡነ ሺኖዳ/

3. የከበሩ አባቶቻችን ልጆች ልትሆኑ ከወደዳቹሁ እነርሱ የጻፉትን (ያስተማሩት) እንጂ ምንም ሌላ አትመኑ። /ቅዱስ አትናቴዎሰ/

4. ጠላት በበዛበት ቦታ የምኖር ከሆነ ብርቱ ወታድር እሆናለሁ። /አባ ጴሜን/

5. ፍቅር፦ በእውነት ሰማያዊ ኀብስትና የአእምሮ ምግብ ነው። /ቀለሜንጦስ ዘእስክንደርያ/

6. ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ጽናት ብዛት ያስረዳል፤ ባልንጀሮቹ ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል፣ የምቀኝነቱን ጽናት ያስረዳል። /ማር ይስሐቅ/

7. ፍቅር፦ መያዣ የሌለውን የሰው ልብ አስሮ ለመሳብ የሚያገለገል የሠላም መንገድ ነው። /አንገረ ፈላስፋ፤ ሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ/

8. አሁን የምንኖራት ሕይወት ምን ያህል ውድ እንደሆነች ልታውቅ ትወዳለህን? ይህች ሕይወት ለዘለዓለማዊ ሕይወታችን መሠረት የትግል ዐውድማ፣ እንዲሆም በገነት ያለችውን አክሊል የምትሰጥ ናት። /ዮሐንስ አፈወረቅ/

9. ልማት ማለት መሬትን መቆፈር ብቻ አይደለም። የሰውን ልቦና በትምህርተ ወንጌል ቆፍሮ ማለምለም፣ በሰው አእምሮ ፍቅርና ስምምነት መዝራትና መትክል፣ ሰውን ከስህተት መመለስና ማስተማር፤ ከልማቶች ሁሉ የበለጠ ነው። /ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ/

10. የትሕትና ከፍታ እጅግ ታላቅ ነው፤ የመታበይ ጥልቀት ደግሞ እጅግ ጥልቅ ነው፤ የመጀመረያውን እንድትከተል፥ ወደዚህኛው ደግሞ እንዳትወድቅ እመክርሃለሁ። /አባ ኤስድሮስ/


ዋቢ መፅሐፍ ብሂለ አበው 2005 @ማኅበረ ቀዱሳን

Saturday, August 24, 2013

“አዳም የት ነህ?” በቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)


ከሩቅ ይሰማኛል
የቤተ- ክርስቲያን ደውል

ነፍስን የሚያማልል
ልብን የሚያባብል

እንደ አዲስ የሆነ
እንደ አዋጅ የሆነ
ከቀኑ ሁሉ ጠዋት እሁድ የገነነ
ከእለት ሁሉ ግህዝ እሁድ የገነነ

ማለዳ ሰንጥቆ የሚያስገመግም
ሠመመን መሳይ ድምፅ ከሩቅ ሚሰማ
ቀላቀሎ የያዘ የካህናት ወረብ የካህናት ዜማ

ንፋስ የሚያመጣው አልፎ-አልፎ ሽው የሚል
ተነስ ቀድሰ የሚል አዳም የት ነህ የሚል

Tuesday, August 6, 2013

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም (ክፍል ሁለት)

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ


ቤተክርስቲያን እመቤታችንን የምታከብርበት አስፈላጊና ዋና ዋና ምክንያቶች

1.        መንፈስ ቅዱስ ስለጸለላት /መንፈስ ቅዱስ በርሷ ላይ ስለሆነ/፣
2.      የእግዚአብሔር እናት /እመአምላክ ስለሆነች/፣
3.      ዘለማዊ ድንግል ስለሆነች፣
4.      ቅድስት ስለሆነች፣
5.      መንፈስ ቅዱስ ስለመሰከረላት፣
6.     ጌታ ራሱ ስላከበራት፤
7.      ስለ ተአምራቷና ስለተቀደሰው መታየቷ ናቸው። ይህም /በተለያየ ጊዜያት/ በግብጽ የመገለጽ ክብር ነው።

ክብሯም፦ በቤተክርስቲያን ንዋየቅዱሳት፣ በመዝሙራት፤ በቤተክርስቲያን ጸሎት ምልጃዋን በመለመን በዓላቷን በማክበር እና አንዱን ጾማችን በስሟ በመጾማችን ይገለጣል።