Sunday, May 17, 2015

“በፊቴም እረዱአቸው” (ሉቃ 19፥27) ምን ማለት ነው? በዲያቆን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ግንቦት 6 ቀን 2007 /(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ግንቦት 6 ቀን 2007 ዓ/ም) )  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ስመ እግዚአብሔር ቀዳማዊ ዘእንበለ ትማልም፤ ወማዕከላዊ ዘእንበለ ዮም፤ ወደኃራዊ ዘእንበለ ጌሰም ፤ብሉየ መዋዕል ዘእንበለ ዓም፤ ፈጣሬ ኩሉ ዓለም ዘእንበለ ድካም፤ ባህረ ምሕረት ዘእንበለ አቅም፤ ብኁተ ሕሉና እስከ ለዓለመ ዓለም አሜን "ወባህቱ ለእልክቱሰ ጸላእትየ እለ ኢይፈቅዱ እንግሥ ላእሌሆሙ አምጽእዎሙ ዝየ ወርግዝዎሙ በቅድሜየ= ነገር ግን እነዚያን በላያቸው ልነግሥ ያልወደዱትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው " /ሉቃ 1927/


መግቢያ
አንተ ደግሞ እርሱን እንዳትመስል ለሰነፍ እንደ ስንፍናው አትመልስለት።”(ምሳ 264)

ክርስትና ከሰብአዊነት ይልቃልመንፈሳዊነትም ከባለአእምሯዊነት ይበልጣልሃይማኖትም ከስሜት በላይ ነው

በቅርቡ ኢትዮጵያውያንና ግብጻውያን ቅዱሳን ሰማዕታተ ሊቢያ ላይ የተፈጸመውን ጭካኔ በተመለክተ ድርጊቱ የእምነቱን መርኅና የቁርአንን አስተምህሮ አይወክልም በሚል ዘውግ ከመሟገትና ከማውገዝ ይልቅ "መጽሐፍ ቅዱሳችሁም ቢሆን :- ነገር ግን እነዚያን በላያቸው ልነግሥ ያልወደዱትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው በፊቴም እረዱአቸው። ይላል እኮ" በሚል ቅዱሱን ቃል ጠቅሶ ለመክሰስና ነቅሶ ለማርከስ የሚዳክሩ በዝተዋል:: እንኳን ቁርአኑ መጽሐፍ ቅዱሱም ቢሆን እንዲህ ይላል የሚለው

          አንደኛ ቁርአኑ እረዱ ግደሉ ይላል ብሎ ማመን ሲሆን ሁለተኛው የመጽሐፍ ቅዱስን ብልጫ ማመናቸውን ያሳየ ነው ለኛ ግን መጽሐፍ ቅዱስ ልክ ለመሆኑ ማረጋገጫችን የቁርአን ምስክርነት ወይም የሙስሊሞቹ ቃሉን ማጣቀስ አይደለም ይህንንም ፈጽሞ ከምስክርነትም የምናገባውና ጠቅሰውልናል ብለን የምናመሰግናቸው ዓይደለም:: በአንጻሩ የረከሰውን ሲቀድስና የበደለውን ሲወቅስ ማየቱ፤ በቅዱሳን መጻፉን ተፈትኖ ማለፉንመረዳቱ፤በአዝማናት ጅረት ማለፉንለትውልድ መትረፉን መመልከቱ ብቻ ለኛ አምኖ መቀበል አክብሮ መከተል በቂ ምክንያት ነው:: በስንፍናቸው ለሚኖሩ እንደድክመታቸውና በእነርሱ አመክንዮ ቁርአንማ እንዲህ ይላል እያሉ መመለስ ለቤተክርስቲያናችን የሚያቅት አይደለም ሆኖም ከስንፍናቸው ላለመተባበር የመጡበትንም የጥፋት መንገድ በመናቅ የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት ብቻ እንናገራለን:: ጠቢቡ እንዲህ ሲል እንደነገረን "አንተ ደግሞ እርሱን እንዳትመስል ለሰነፍ እንደ ስንፍናው አትመልስለት።" (ምሳ. 26:4) እንግዲህ በዓይነ ሥጋ እያነበበ በዓይነ ህሊና መረዳቱን ለሚሻ ግን በመጀመርያ ቃሉን አብራርቶ ከማስረዳትና ፈቶ ከመግለጥ በፊት የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት በምን መንገድ መረዳት እንደሚገባ ጥቂት ነጥቦች እናስቀምጥ

Monday, May 4, 2015

ጀማል ማነው? ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት


ኤፍሬምና ጓደኞቹ

ጀማልየተባለ ሙስሊም ወንድማችን በሊቢያ ከተሠዉ ክርስቲያኖች ጋር አብሮ ተሠዉቷል እየተባለ ሲነገር ቆይቷልበአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞችና ሌሎችም የቅርብ ምንጮች ታሪኩ የተሳሳተ መሆኑን ቢናገሩም ሰሚ ለማግኘት ግን አልተቻለም፡፡ አንዳንዶቹም ታሪኩን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ፍቅር ማሳያ አድርገው ተሟግተዋል፡፡ እንደ እኔ ግን ይህንን ታላቅ ፍቅር ለማሳየትጀማልየተባለ መሥዋዕት መፍጠር አያስፈልገንም፡፡ ፍቅሩ ነበረ፤ አለ፡፡ ተጨማሪ ፈጠራው አያስፈልገውም ነበር፡፡

ኤፍሬም ሰማዕት ዘሊቢያ
ጀማልነው ተብሎ ሲነገርለት የነበረው ወንድማችን ግን ኤፍሬም የተባለ ኤርትራዊ፣ ቃኘው ሠፈር ይኖር የነበረ ክርስቲያን ነው፡፡ ቤተሰቦቹ ሁለት መርዶ እንደመጣባቸው እየገለጡ ነው፡፡ በአንድ በኩል በአሰቃቂ ሁኔታ በአይሲስ መሠዋቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞሙስሊምነው መባሉ ነው፡፡

      ኖርዌይ የነበሩ ኤርትራውያን ክርስቲያኖች ወዲያው ነበር ነገሩን የተቃወሙት፡፡ ነገር ግን አሥመራ ያሉት ቤተሰቦቹ እስኪረዱ ድረስ ትክክለኛ ስሙን ለመግለጥ አልተፈለገም፡፡ በዚህ መዘግየት የተነሣም ብዙ የፈጠራ ታሪኮች ተፈጠሩ፡፡

አንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ አቀንቃኞች በላኩልኝ የውስጥ መልእክት የጀማልን ሙስሊምነት መካድ ሙስሊሞች ለክርስቲያኖች ያላቸውን ድጋፍና ፍቅር መካድ ነው ሲሉ ገልጠዋል፡፡ ለእኔ ግን ከተፈጠረውጀማልይልቅ እዚሁ አዲስ አበባ ያለው መሐመድ ካሣ ይህንን ልዩ ፍቅር ከንጋት ኮከብ በላይ አጉልቶ አሳይቶኛል፡፡ ልቡ እስኪደክም ኀዘንተኞቹን ለማጽናናትና ለመርዳት የሚደክመው፤ ለምን ጉባኤ አይደረግም፣ መዘምራን ለምን አይመጡም፣ መምህራን ለምን አያስተምሩም እያለ ልቅሶ ቤቶቹን ከክርስቲያኖቹ በላይ ሲያገለግል የነበረው፤ ተዝካራቸው መውጣት አለበት ብሎ ከካህናቱ ጋር የሚሟገተው፣ ድንበር ተሻጋሪውና ድልድይ ገንቢው መሐመድ ካሣ ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ፍቅር ከበቂ በላይ ማሳያዬ ነው፡፡

ያየሁት፣ የነካሁት፣ የበለጠኝ ማስረጃዬ፤ ፈጠራ አያስፈልገኝም።

ኤፍሬም ሆይ በረከትህ ይደርብን።

 ------------------------------------------- / / / --------------------------------------------

Wednesday, April 22, 2015

“የሰማዕታት ደም የቤተ ክርስቲያን [ምርጥ] ዘር ነው” (ጠርጠሉስ)



ጠርጠሉስ የተባለውና 2ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (160 AD - 220 AD) የነበረው ታላቅ ፀሐፊና የክርስትና ጠበቃ ስለ ሰማዕታት ደም በተናገረበት ሥፍራ ያስቀመጠው ነው። ተርቱሊያን/ Tertullian ወይም በእኛ አጠራር ጠርጠሉስ የሚባለው ሊቅ ከመጀመሪያዎቹ የክርስትና አባቶች ጋር የሚቆጠር እንዲያውም የላቲኖች (በላቲን የምትናገረው፣ የምትጽፈው) ቤተ ክርስቲያን ወይም የምዕራብ ቤተ ክርስቲያን አባት ተብሎ መጠራት እንዳለበት ብዙዎች የሚስማሙበት ሊቅ ነበር። በእኛ በኦርቶዶክሳውያንም ሆነ በካቶሊኮቹ ዘንድ ብዙም ስሙ ሲጠቀስ የማይሰማው ከጻፋቸው ጽሑፎች መካከል ከቤተ ክርስቲያን ትምህርት የወጡ ስላሉበት ነው። ይሁን እንጂ ይህንን ሊቅ በዚህ ሥፍራ መጥቀስ የፈለግኹት አገሩና ምንጩ የሰሜን አፍሪካ (የዛሬዋ ቱኒዚያ) አካል በሆነችው በካርቴጅ የተገኘ በመሆኑ ጭምር ነው። []

እንዴት ዓይነት መከራ ይቀበሉ እንደነበረ፣ እንዴት ዓይነት ሰማዕታት ይቀበሉ እንደነበረ፣ በነገሥታቱ ፊት፥ ቀርበው ሲመሰክሩ እንዲህ አሉ፦ አውግዙን፣ አሰቃዩን፣ ስቀሉን፥፣ ግደሉን፣ አጥፉን፤ የእናንተ ክፋት ለእኛ እውነተኝነት ምስክርነት ነው! የእናንተ እንዲህ ክፉ መኾን፣ የእናንተ እንዲህ አረመኔ መኾን፣ የእናንተ እንዲህ ደካማ መኾን፤ የእኛ እውነተኝነት ይመሰክራል። []

አሰቃዩን፥ ስቀሉን፣ ግደሉን፣ አጥፉን፤ የእናንተ ይኼ ክፋታችሁ፥ የእኛ እውነተኝነት ይመሰክራል። በእናንተ በተሰቃየን ቁጥር፥ እየበዛን እንኼዳለን፤ የሰማዕታት ደም የቤተ ክርስቲያን ዘር ነው። ባሰቃያችሁን ቁጥር እየበዛን እንኼዳለን። የሰማዕታት ደም የክርስትና ዘር ነው። እኛ ሁላችን በሰማዕታት ደም የተዘራን ነን! []

Monday, April 20, 2015

የምናዝነው ስንት ሰው ሲሞት ነው? ‹ሰማዕታተ ዘ ሊቢያ› ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት



በየመን፣ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ስለሚሞቱት ዜጎቻችን የሚሰጡት መንግሥታዊ መግለጫዎች ሁለት ነገር የጎደላቸው ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ሰብአዊ ስሜት፡፡ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ስለሌላው ሰብአዊ ፍጡር መከራና ስቃይ ሲሰማ መጀመሪያ አንዳች የኀዘን ስሜት ይሰማዋል፡፡ ከዕውቀት ይልቅ ስሜት ለሰዎች ቅርብ ነውና፡፡ ባለሥልጣን ቢሆን፣ ፖሊስ ቢሆን፣ ዳኛ ቢሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሆን ሰው ነውና ስሜት አለው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ያዝናል፣ ይከፋዋል፣ ልቡ ይረበሻል፣ ሆዱ ይባባል፣ ኅሊናው ይደማበታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ስለዚህም የመጀመሪያው ሥራው ማዘን ቀጥሎም ኀዘኑን በወጉ መግለጥ ነው፡፡


ሰሞኑን የማያቸው መግለጫዎቻችን ግን የኀዘን ወግ በሀገራችን የሌለ የሚያስመስሉ ናቸው፡፡ መሪዎቻችን ወደ አደባባይ ወጥተው ለሞቱት ወገኖቻችን እንደ ኢትዮጵያዊነት ኀዘናቸው የሚገልጡት፣ ጥቁር ልብስ ለብሰው የምናያቸው፣ ነጠላ የሚያዘቀዝቁት ስንት ሰው ሲሞትብን ነው? የሚያስብሉ ናቸው፡፡ ኀዘንኮ ፖለቲካ አይደለም፣ ፓርቲ አይደለም፣ ርእዮተ ዓለም አይደለም፣ ሊብራልም አብዮታዊ ዲሞክራሲም አይደለም፡፡ ኀዘን ሰብአዊነት ነው፡፡ የሚመራቸው ዜጎቹ፣ የሚያሠማራቸው በጎቹ ሲታረዱና ሲሞቱ ኀዘኑን በይፋ የማይገልጥ መሪና እረኛ መቼ ነው ኀዘኑን የሚገልጠው?