ከአንዳንድ ወንድሞቼና እኅቶቼ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል ስንንነጋገር ስለ ልሳን በ1ኛ ቆሮንቶስ በምዕራፍ 14፥2 ላይ ያልውን ሐረፈተ ነገር በመጥቀስ እንዲህ ብለውኝ ነበር "በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም" እና እኛ በልሳን ብንናገር ለእግዚአብሔር፣ ከእግዚአብሔር ጋር እንጂ ለሰዎች ወይንም ከሰዎች ጋር አይደለምነበር ያሉኝ። እኔም እነሱ ላነሱልኝ መጽሐፍ ቅዱስ በ1ኛ ቆሮንቶስ በምዕራፍ 14፥2 ላይ ያለውን ቃል ስለጠቀሱልኝ ነገሩን በአርሞ ለትንሽ ደቂቃዎች አሰላሰልኩና ማለፍ ሳላልፈለኩኝ እንዲህ ነበር ያልኳቸው።
እግዚአብሔር ወልድ ክርስቶስ እየሱስ ሐዋርያቱን በእየሩሳሌም እንዲቆዩና በመንፈስ ቅዱስ እንደሚጠመቁ ካዘዛቸው በኋላ በዓለ ኀምሳ በደረሰ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ እንደተጠመቁና በሌላ ልሳኖች እንደተናገሩ ለቃሉ ሰማእት ቅዱስ ሉቃስ በሐዋርያት ሥራ ክታቡ በምዕራፍ 2 አጠቃላይ ስለ በዓለ ኀምሳ ምንነትና በሁሉም መንፈስ ቅዱስ እንደሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች [ሰዎች ሊረዱት፣ ሊሰሙት፤ በሚችሉት ቋንቋ] ይናገሩ እንደነበር ገልጾልናል።
በመጀመርያ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በፃፈላቸው በመጀመርያ ክታቡ በምዕራፍ 13 በሰውና በመላእክት ልሳን ብንናገር እንኳን በመካክላችን "በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብንናገር ፍቅር ግን ከሌለ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆነናለ። /1ኛ ቆሮ 13፦1/ [በሰዎችና በመላእክት ልሳን ሲል የማኑሄ ሚስት የሶምሶን እናት፣ የነቢዩ ሳሙኤል እናት ቅድስት ሐና፤ እንዲሁም ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምና መአልኩ ቅዱስ ገብርኤል ሲነጋገሩ ሰዎች በሚሰሙት፥ በሚረዱትና በሚያዳምጡት ቋንቋ መሆኑን ልብ በሉ!]። ታዲያ እንዲህ ከሆንን ደግሞ ድሆችንም ልንመግብ ያለንን ሁሉ ብናካፍል፥ ሥጋችንን ለእሳት መቃጠል አሳልፈን ብንሰጥ፤ ፍቅር ግን ከሌለን ምንም አይጠቅመንም።
ስለዚህ፦ ምድርና ሰማይ እንደሚራራቁ ሁሉ በፍቅርና በልሳን ያለውን ልዩነት አጉልቶና አጥርቶ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የፃፈልንን ጠቅሼላቸው ወደ ዋናው ጉዳይ ተመለስኩኝና በ1ኛ ቆሮንቶስ በምዕራፍ 14 ላይ በቁጥር ሁለት ያለውን ቃል ስለጠቀሱልኝ "በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም" /1ኛ ቆሮ 14፥2/ ስላሉኝ የመለስኩላቸው መልስ በእዛው ምዕራፍ ከታች "ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፥ በልሳኖች ከመናገርም አትከልክሉ፤ ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን።" /1ኛ ቆሮ 14፥39-40/ የሚለውን አብረን ካነበብን በኋላ ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፥ በልሳኖች [አሁንም በልሳኖች ሲል ከላይ የገለፅኩላችሁን በደንብ መረዳት ያስፍልጋል] ከመናገርም አትከልክሉ፤ ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን። ቢሆንም ወንድም ታሬ ሰዎች በሚረዱት ቋንቋ ስለ “አንድ ኢትዮጵያዊ ካህን” (በfacebook ለማንበብ ታረቀኝ ወልዴ) የሚለውን ይጫኑ። ብሎ በሚገባን እንደገልፀው ሁሉ በልሳኖች ከመናገርም አትከልክሉ ካለ በኋላ "ሥርዓትና አገባብትን" ይሻል ምክንያቱም አሁንም በእዛው ምዕራፍ ወደ ላይ "እግዚአብሔርስ የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና፤ በቅዱሳንም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲህ ነው።" /1ኛ ቆሮ 14፥33/ እንደተባለው እንግዲህ ብዬ ነበር ንግግሬን ቀጠልኩኝ።
ከቁጥር አንድ እስከ አስራ ሦስት ድረስ አብረን እንድናነበው ጋበዝኳቸው እነሱም አወንታዊ ምላሽ ስለሰጡኝ መጽሐፍ ቅዱስ ገልጠን ምዕራፍ 13 ማንበብ ቀጠልን ቃሉ [እርስዎ ከቻሉ ባሉበት ስፍራ እንዲያነቡ እጋብዝዎታከሁ] አነበብነው። እንግዲህ የተመረጠ ዕቃ የተባለ፣ የእግዚአብሔር ሐዋርያ የሆነ፤ እንኳን እንዲህ ነው ብሎ የፃፈልን "ከሁላችሁ ይልቅ በልሳኖች እናገራለሁና እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ ነገር ግን ሌሎችን ደግሞ አስተምር ዘንድ በማኅበር እልፍ ቃላት በልሳን ከመናገር ይልቅ አምስት ቃላት በአእምሮዬ ልናገር እወዳለሁ። /1ኛ ቆሮ 14፥18-19/ ይለናል።
ሐዋርያው በልሳን ከመናገር ይልቅ "አምስት ቃላት በአእምሮዬ ልናገር እወዳለሁ።" ሲል በመጀመርያ ከልሳን ይልቅ ወደ አእምሮ መመለስ እንዳለብን ነው አስረግጦ የሚነግረን። "አምስት ቃላት" የተባሉትም አንድም እንድንበት የተገለጠልን የተዋህዶ ስም "ክርስቶስ" ሲሆን ሌላው ደግሞ "አምስቱ አህማደ ምስጢራት" ነው። ሰው በልሳን ቢጸልይ ማለት ሰዎች በማያቁት ቋንቋ ወይንም እራሱ የሚጸልየው ሰው ልሳኑ ሳይገባው ቢጸልይ አእምሮው የእግዚአብሔርን ቅዱስ ፍሬውን አያስተውልም። ለእዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ "በልሳን ብጸልይ መንፈሴ ይጸልያል አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው።" /1ኛ ቆሮ 14፥14/ ባዶ ፍሬ ነው ያለን።
እኛ ሰዎች አእምሮው እንዲኖረን እግዚአብሔር ለኛ ካለው ፍቅር የተነሳ "ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል። እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ" /1ኛ የጴ 4፥7/ ቀጥሎም ስለ "መንፈስና አእምሮ" ሰው በመንፈስ ሲጸልይ አእምሮም ደግሞ ይጸልይ፤ በመንፈስ ሲዘምር በአእምሮም ደግሞ ይዘምራል [ልክ እንደ ሐና አንደበቶቹና ከናፍርቶቹ ይጸልይ፣ ይዘምራል] ቃሉም እንዲህ ነው የሚለን "እንግዲህ ምንድር ነው? በመንፈስ እጸልያለሁ በአእምሮም ደግሞ እጸልያለሁ፤ በመንፈስ እዘምራለሁ በአእምሮም ደግሞ እዘምራለሁ።" እንዲያማ ካልሆነ፥ አንተ በመንፈስ ብትባርክ ባልተማሩት ስፍራ የተቀመጠው የምትለውን ካላወቀ እንዴት አድርጎ ለምስጋናህ አሜን ይላል? አንተማ መልካም ታመሰግናለህ፥ ሌላው ግን አይታነጽበትም። /1ኛ ቆሮ 14፥15-17/ አንተማ መልካም ታመሰግናለህ፥ ሌላው ግን አይታነጽበትም ሲል [ሰዎች በሚያቁትና በሚሰሙት ቋንቋ] ነገር ግን ሌሎች የተባሉት በራሳቸው ቋንቋ ካልሆነ እንዴትስ ይታነጻሉ እንዴትስ አሜን ይላሉ?።
ስለዚህ ስለ ልሳን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በአጽኖት "እንግዲያስ በልሳኖች መናገር ለማያምኑ ምልክት ነው እንጂ ለሚያምኑ አይደለም፥ ትንቢት ግን ለሚያምኑ እንጂ ለማያምኑ አይደለም።" ማለት አንድ ሰው በክርስቶስ ክርስቲያን ከተሰኘ በኋላ በልሳን መናገሩ [ሰዎች ሊረዱት፣ ሊሰሙት፤ በማይችሉት ቋንቋ] እንደ አለማመን ነው፥ የሚያምኑት ግን በክርስቶስ ክርስቲያን ከተሰኙ በኋላ ትንቢት ቢናገሩ [ትንቢት መናገር ማለት ለወደፊቱ የሚሆነውን በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገላጭነት መናገር ማለት ነው] ለሚያምኑ ነው እንጂ!።
አሁን እየተነጋገርን ያለነው መነሻው ስለ ልሳን ቢሆንም መድረሻው፣ መቋጫው፣ ነገር ሁሉ የሚደመደመው በፍቅር ብቻ ነው። "በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም" /1ኛ ቆሮ 14፥2/ የሚለውን ለመጠቅለል ከምዕራፍ 13 ጀምሮ ማንበብ ግድ ይለናል።
ምክንያቱም፦ ትንቢትምና ልሳን ቢሆንም እንኳን እንደሚሻር ልብ በሉ! የእግዚአብሔር ሥርዓትን ጠንቅቀን ለማወቅና እንደ እግዚአብሔር አሳብና ፍላጎት ለመሆን፥ የእግዚአብሔርን ፍቅር በልቦናችን ሞልተን ለሰዎች ይህን ታላቅ የሆነውን ፍቅር በምድራችን እንደ ጠዋት ጠል ስናርከፈክፈው እንደሆነ ብቻ ነው። ይህ ፍቅር በልቦናችን ሳንሞላው በምድራችን እንደ ጠዋት ጠል ሳናርከፈክፈው፥ በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብንናገር ፍቅር ግን ከሌለ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል እንሆናለ። "ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።" /1ኛ ቆሮ 13፥ 8/
ምክንያቱም፦ ትንቢትምና ልሳን ቢሆንም እንኳን እንደሚሻር ልብ በሉ! የእግዚአብሔር ሥርዓትን ጠንቅቀን ለማወቅና እንደ እግዚአብሔር አሳብና ፍላጎት ለመሆን፥ የእግዚአብሔርን ፍቅር በልቦናችን ሞልተን ለሰዎች ይህን ታላቅ የሆነውን ፍቅር በምድራችን እንደ ጠዋት ጠል ስናርከፈክፈው እንደሆነ ብቻ ነው። ይህ ፍቅር በልቦናችን ሳንሞላው በምድራችን እንደ ጠዋት ጠል ሳናርከፈክፈው፥ በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብንናገር ፍቅር ግን ከሌለ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል እንሆናለ። "ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።" /1ኛ ቆሮ 13፥ 8/
ከልሳን ይልቅ፥ ፍቅር፣ ፍ፤ ቅር ፍቅር!!!
No comments:
Post a Comment