Saturday, January 4, 2014

በገ’ና ዋዜማ፥ ገና ነው ገ’ና


እንኳን አደረሳችሁ!
የምስራች ለሁላችሁ።

አዳም ሆይ፦ አትብላ ከተባልከው በልተህ፤
††† ,,,, ከአምላክህ እቅፍ፥ ከገነት ተባረህ፤
ትኖር ጀመር፥ ከሔዋን ጋር ተባብረህ፤
ምን ያደርጋል! ፅድቅ ከአንተ ተገፎብህ።

በነቢያትና በፃድቃን የተነገረው በሙሉ፤
ቃል በማዕፀን እንደ ተወሰነ ይናገራሉ።

ብሥራት አብሳሪው ቅዱስ ገብርኤል፤
ኤልሳቤጥ ትመስክር ስለ ድንግል፤
ስምዖን ሲባርክ ማርያምን ባርኳል፤
የሠው ልጅ ሁሉ ገና ይማጸናታል።

††† ,,,,,,,,,,,, በገ’ና ዋዜማ፥ ገና ነው ገ’ና፤
የእረኞች የይባቤ ምስጋና መች ተሰማና፤
የእናቱ ፅናት ልጇን በማዕፀኗ ይዛለችና፤
የነቢያት ትንቢታቸው ሲፈጸም ነው ገ’ና።

ወንድ ልጅ፥ ተወለደልን፤
የአዳም ዕንባ ሊያብስልን።

ኢየሱስ በእቅፏ ውስጥ ነበረና፤
እናቱም ፍቅሯን መግባዋለችና።

ለማንም ሠው የነፃነት መብቱ፤
የተጠበቀ ነው በተዋሕዶ ቤቱ።

መለየትን፥ ከመፈልግ በፊት፤
ነገር ግን፥ እውነቱን ይረዳት፤
እውነቱ ምንድን ነው? ለምትሏት፤
ኢየሱስ ነው፥ የዓለም መድኃኒት።

ብላ ትሰብካለች፥ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ፥ በድንግልና ተወልዶ።

የጌታን፥ የበረከት ስጦታ ሳይቀበሉ፤
ክርስቶስን ተቀብለናል ይላሉ፤
ኧረ ገና ነው ገ’ና፥ ስጦታውን ላልተቀበሉ፤
ኢየሱስ ብቻውን፥ በግርግም አይገኝም በሉ!

ኢየሱስ ክርስቶስን ከተቀበላቹ፤
ድንግል ማርያምንም አብራቹ ።

በነቢያት፥ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ ተብሎ ተተንብዮለታል፤
በሐዋርያት፥ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ ተመስክሮለታል።

ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክ ነው የሚሉ፤
እናቱን ማርያምን ወላዲተ አምላክ ይላሉ።

ምስክሩም ከሠው ጥበብ አይደለ፤
ከሥጋና ከደም ዕውቀት እንዳይደለ፤
ጌታ ለስምዖን ጴጥሮስ እንዲህ አለ፤
ገላጩ፥ አባቴ በሰማያት ያለ’።

የጌታን፥ የበረከት ስጦታ ሳይቀበሉ፤
ክርስቶስን ተቀብለናል ይላሉ፤
ኧረ ገና ነው ገ’ና፥ ስጦታውን ላልተቀበሉ፤
ኢየሱስ ብቻውን፥ በግርግም አይገኝም በሉ!


(ማያ፦ "ገ’ና" የሚለው ከአናቱ ላይ ጭረት ያለው የክርስቶስን ልደት የሚያበስር፤ ሲሆን ጠብቅ ተብሎ የሚነበብ ነው። ይሄኛው "ገና" ደግሞ አንድ ያልተቋጨ፣ ያላለቀ፣ ያልተገባደደ፤ ይህን የመሰለውን ነገር እንዳለ የሚያመላክት ነው። ስለዚህ ይሄ "ገና" ላልቶ የሚነበብ ነው። በእኛ ቋንቋ ጠብቆና ላልቶ የሚነበቡ ቃላቶች ላይ የመልዕክቱ ሁኔታን ስለሚያዛባውና በአንባቢያን ላይ ችግር እንዳይፈጥር እንደዚህ ጽፌዋለሁ።)

No comments:

Post a Comment