(በዚህ በመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው፤ መንፈሳዊ ትምህር ላይ፥ እጅግ ጥልቅ፣ ምጡቅና ምዕሉ፤ በሆነ ትምርታቸው፦ መጽሐፍ ቅዱስን እነማን ማስተማር እንደሚገባቸው፣ በተለይ ደግሞ ፷፮ቱን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ብለው ለተቀበሉት፤ ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስን ፍሬ-ነገሮችን በጥያቄ መልክ በማንሳትና ለጥያቄ ነጥቦችም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሾችን በመስጠትና እናት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን፤ በመንፈሳዊ አስተምህሮ እንዳላትና አሰበጣጥራ በማዋሃድና በመተንተን እንደምታስተምረ፤ አስረግጠው ይናገራሉ!። የአንደበታቸውን ቃል፣ የትምርታቸውን ማዕደ በረከት፤ አብረን እንድንቋደስ፤ እነሆ፦ ከአባታችን ቃለ-ወንጌል የተወሰደ።)
ጉዳያችን፥ ከምዕራፍና ከቁጥር ጋር ከሆነ፦
ለምሳሌ፦ እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን የተቀበልናት፤ በማን ስም ነው? በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አይደል እንዴ! የክርስቶስ እናት ስለሆነች! ቅዱሳኑን የተቀበልነው በማን ስም ነው? በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እኮ ነው! ነቢያትን፥ የተቀበልነው
በማን ስም ነው? በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እኮ ነው! ሐዋርያትን፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም! ጻድቃንን፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም! ሰማዕታትን፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም! መስቀሉን፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም! ቁርባኑን፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም! እንዴት! ማስተዋል አቃተን?
ጉዳያችን፥ ከምዕራፍና ከቁጥር ጋር ከሆነ፤ ነጥብ በነጥብ እንነጋገራለን!። የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፳፫፤ ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌላዊ፥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ፅፏል፦ "በነቢያት፥ ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።" ማን? ኢየሱስ ክርስቶስ! የት ኖረ? በናዝሬት ኖረ! ለምን በናዝሬት ኖረ? "በነቢያት፥ ናዝራዊ ይባላል" ተብሎ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ።
አሁን፥ ይሄንን ትንቢት ይዘን የነቢያትን መጽሐት ብንመለከት፣ የነቢያትን መጽሐት ብንመረምር፤ ይሄንን ትንቢት አናገኘውም። ትንቢተ ኢሳያስ ላይ የለም "ናዝራዊ ይባላል" የሚለው ትንቢት። ትንቢተ ኤርምያስ ላይ የለም፣ ትንቢተ ሕዝቅኤል ላይ የለም፣ ትንቢተ ዳንኤል ላይ የለም፤ የነቢያት ትንቢት መጽሐት ሁሉ ላይ የለም። ታዲያ፥ ቅዱስ ማቴዎስ፥ ከየት አምጥቶ ጻፈው? ከየት አምጥቶ ነው "በነቢያት፥ ናዝራዊ ይባላል" ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ይሆን፤ ያለው? ምዕራፍና ቁጥር ስጡኝ? ቶሎ በሏ! ቅዱስ ማቴዎስ ከየት አመጣው? በነቢያት መጽሐት ከሌለ ከየት አመጣ?
እንግዲህ፥ እኛ ትንሽ በተነፈስን-ቁጥር፤ ምዕራፍ-ቁጥር? የሚሉ አንበሶች፥ ለምን ቅዱስ ማቴዎስን አይጠይቁትም? "አንተ ማቴዎስ፥ በነቢያት ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ በናዝሬት ኖረ ብለህ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ተናግረሃል? የነቢያት መጽሐት ላይ የለም፤ ከየት አመጣኸው? ምዕራፍ-ቁጥር?" ብለው ለምን አይጠይቁት? ለምን አይጠይቁትም? እንግዲህ
ሄደው ይጠይቁ! ከቻሉ፥ ሠማይ-ቤት ሄደው፦ "አንተ ማቴዎስ፥ ወንጌል ላይ እንዲ ጽፈሃል፤
ምዕራፍ-ቁጥር? ቶሎ ውለድ!" ይበሉት። ከእርሱ ጋር ከተስማሙ ከእኛ ጋር አንስማማ? አንስማማ ወይ? ከቅዱሳን ጋር ባለመስማማታቸው ነውኮ ከእኛ ጋር መስማማት ያቃታቸው! አይደለም እንዴ? ከነ-ቅዱስ ማቴዎስ ከተስማሙ፤ ከእኛም ጋር ይስማማሉ!፤ የሚያጣላን፥ ነገር የለም! የሚያጋጨን፥ ነገር የለም!
ችግሩ፥ የምዕራፍና የቁጥር ችግር ከሆነ፦ ወገኖቼ! በልበ-ነቢያት የቀረ፥ ለሐዋርያት የተገለጠ ነገር አለ̕፤ በልበ-ሐዋርያት የቀረ፥ ለሊቃውንት የተገለጠ ነገር አለ̕። እንደገና ደግሞ ሁሉ-ነገር አልተጻፈም። በጹሑፍ፥ የተላለፈ ነገር አለ̕፤ ቃል በቃል፥ የተላለፈ አለ̕። ይሄንን ትንቢት፥ በእርግጥ ነቢያት ተናግረውታል። ነገር ግን፥ በምርኮ ጊዜ የጠፉ መጽሐት ነበሩ፤ በዚያ ላይ፥ ትንቢቱ ተጽፎ ነበረ። መጽሐቱ ቢጠፉም፥ ትንቢቱ ስላልጠፋ፣ ቃል በቃል እየተነገረ፣ ከቅዱስ ማቴዎስ ስለደረሰ፤ ቅዱስ ማቴዎስ፥ በቃል ያገኘውን፤ በወንጌሉ ሊጽፈው ችሏል ማለት ነው።
እንግዲህ፥ ወንጌልን እናስተምራለን የሚሉ ሠዎች፤ ይሄንን ነገር ቢጠየቁ መልስ አላቸው? መልስ አላቸው ወይ? በደንብ
ተናገሩ! አላቸው ወይ? የላቸውም። ከሌላቸው፥
ወንጌልን ቁጭ ማድረግ አለባቸው፤ ከሌላቸው ወንጌልን ማስተማር
የለባቸውም። ይሄንን ጥያቄ፥ የቤተ-ክርስቲያን አባቶች ይመልሱታል። ስለዚህ፥ መጽሐፍ ቅዱስን ማስተማር የሚገባቸው፤ አባቶቻችን
ናቸው ወይስ አይደሉም? ናቸው!። በዚህ፥
ደስ ይበለን! እውነቴን ነው የምለው፤ ትምክህት አይደለም! ይሄ እውነት፥ እውነትን መናገር፣ እውነትን መመስከር እንጂ!
ትምክህት፣ ትዕቢት፤ አይደለም። ክርስትና ማለት፥ እውነቱን እውነት፣ ሐሰቱን ሐሰት ማለት ነው። እኛን፥ ምዕራፍና ቁጥር ብለው
የሚጨቀጭቁን፤ ወንጌሉን ተሸክመዋል።
ወንጌላዊያን፥ ነን ይላሉ፤ እሺ ምዕራፍና ቁጥርን ይንገሩና?
በነቢያት፥ “ናዝራዊ ይባላል የተባለው” እስኪ ያምጡት! ካላመጡት ደግሞ
ወንጌሉን ቁጭ ነው! ከመልአከ ምዕረት፥ እግር ሥር ቁጭ ብሎ መማር ነው! ከአባቶች፥ እግር ሥር ቁጭ ብሎ መማር ነው! ይሄ ነው እውነቱ።
ሁለተኛ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ ሦስት ቁጥር ስምንት፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መለስ ብሎ፥ የነቢያት አለቃ የሆነውን፣
የእግዚአብሔርን ባለመዋል፣ ሙሴን አሰበው። ቅዱስ ጳውሎስ፥ ማንን አሰበ? እየነገራችሁኝ!
ማንን አሰበ? ሙሴን
አሰበ። ሙሴ፥ የማን ባለመዋል ነው? የእግዚአብሔር፥ ባለመዋል ነው። የማን ወዳጅ ነው? የእግዚአብሔር፥
ወዳጅ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ፥ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ስለሆነ፣ እግዚአብሔር የመረጠው ስልሆነ፣ አባቶቹን ነቢያትን አል̕ረሳም። የዛሬ
ችግር፥ ትውልዱ አባቶቹን ነቢያትን እረሳ፣ አባቶቹን ሐዋርያትን እረሳ፣ አባቶቹን ጻድቃንን እረሳ፣ አባቶቹን ሰማዕታትን እረሳ፤
ማስታወስ አቃተው። ቅዱስ ጳውሎስ ግን ነቢዩን ሙሴን አስታወሰ፤ አስታውሶ ስለ ሙሴ ተናገረ።
ምን ብሎ ተናገረ? ነቢየ ሙሴ፥ የግብፅ ጠንቋዮች እንደተቃወሙት። ሙሴ ቅዱስ ነው፥ ቅዱሱን ሠው የተቃወሙት ጠንቋዮች ናቸው፤ ቅዱሱን ሠው የተቃወሙት አስማተኞች ናቸው። ዛሬም፥ ቅዱሳኑን የሚቃወሙ ጠንቋዮች
ናቸው፤ ቅዱሳኑን የሚቃወሙ አስማተኞች ናቸው፤ ቅዱሳኑን የሚቃወሙ የዛር-መንፈስ ያደረባቸው ናቸው እንጂ! የእግዚአብሔር መንፈስ፥
ያደረባቸው ቅዱሳኑን አይቃወሙም። ለምን? የእግዚአብሔር መንፈስ፥ እርስ በእርሱ፤
አይቀዋወምም። የእግዚአብሔር መንፈስ፥ እርስ በእርሱ፤ አይጣላም። በቅዱሳን ያደረ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። በእነዚም ሠዎች
ያደረው የእግዚአብሔር መንፈስ ቢሆን ኖሮ፤ ይቀዋወማሉ ወይስ ይስማማሉ? ንገሩኝ!
ይስማሙ ነበረ። መንፈሱ ሲቃረን ነው፣ እርኩስ መንፈስ
ነው፣ ቅዱስ መንፈስ ያደረበትን የሚቃወም፤ እውነቱን እውነት፣ ሐሰቱን ሐሰት።
አሁን የምርጫ መልስ አይደለም፤ ጥያቄ ተጠይቆ፥ ኤ, ቢ, ሲ,
ዲ, አይሰራም እዚህ ጋር፤ እውነቱን እውነት፣ ወይም ሐሰት
ነው የምንማረው። እውነቱን ምን ማለት ይገባል? እውነት! ሐሰቱንስ ሐሰት!። ሸፋፍነን፣ አድበስብሰን፣ ብናልፍ፤ እኛው ነው የምንቸገርበት። “አደባብሰው ቢያርሱ
በአረም ይመለሱ ነው” እኛኑ ነው የሚያስጨንቀን። ታዲያ ቅዱስ ጳውሎስ፥ አባቱን ሙሴን አሰበ፣ አባቱን ሙሴን አስታወሰ፣ ጠንቋዮች እንደተቃወሙት፣ አስማተኞች እንደተቃወሙት፣ መተተኞች እንደተቃወሙት፤ ምን ብሎ ጻፈለት?
ለሚወደው ለልጁ ለጢሞቴዎስ፦ “ኢያኔስና ኢያንበሬስም
ሙሴን እንደ ተቃወሙት እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው” ቅዱሳንን የሚቃወሙ፣ ባለ አእምሮ ናቸው ወይስ
አእምሮ የጠፋባቸው? “አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም
የተጣሉ ሰዎች ሆነው፥ እውነትን ይቃወማሉ።” /፪ኛ ጢሞ ፫፥፰/
ቅዱስ ጳውሎስ፥ ሙሴን የተቃወሙት ጠንቋዮች፤ ስማቸው ማንና ማን እንደሆነ ነገረን። ስማቸውን እነማን ናቸው አለ̕? እገሩኝ! “ኢያኔስና ኢያንበሬስ”፤ ወደ ኦሪቱ ተመልሰን፥ የሙሴን
ታሪክ ብናነብ፣ ጠንቋዮቹ ሙሴን እንዴት እንደተቃወሙት፤ ብንመለከት፦ “ኢያኔስ” የሚለውን ስም እናገኛለን? “ኢያንበሬስ”የሚለውን ስም እናገኛለን? ይሄ ጥያቄ
ነው። በኦሪቱ፥ ይሄን
ታሪክ የምናገኘው ኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ ፯ ቁጥር
፲፩ ላይ ነው።
(ለዚህና ለመሰል ጥያቄያችን ሁሉ
እግዚአብሔር መልስ አለው እንዳለው በማመላከትና እውነተኛውን የመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው፥ አስተምሮታቸውን ለበለጠ ለመረዳት፥ መንፈሳዊ ትምህርታቸውን እንዲያዳምጡ ምክሬን እለግሶታለሁ። እግዚአብሔር አምላክ፦ ለአባታችን መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው፥ ቃለ ሕይወት ያሰማልን፤ መንግሥተ ሠማያት ያውርስልን! እያልኹኝ፥ እኛም ሰምተንና አዳምጠን፥ አንድም ሠላሳ፣ ስልሳ፣ መቶ፤ ፍሬ እንድናፈራ የእግዚአብሔር ፍቃድ ይሁንልን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወድንግል ማርያም
ክብር!!! አሜን።)
መጽሐፍ ቅዱስን
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ሁሉም ያነበዋል
ምእራፍ እና ቁጥሩን ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ሁሉም ይጠቅሰዋል
በዚህ ብቻ አይበቃም ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ተርጓሚ ያሻዋል/፪/
እንደ ፈቃዳችን ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ብንተረጉመው/፪/
በውጥን የሚያስቀር ,,,,,,,,,,,,,, ስህተቱ ብዙ ነው/፪/
ምእራፍ እና ቁጥሩን ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ሁሉም ይጠቅሰዋል
በዚህ ብቻ አይበቃም ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ተርጓሚ ያሻዋል/፪/
እንደ ፈቃዳችን ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ብንተረጉመው/፪/
በውጥን የሚያስቀር ,,,,,,,,,,,,,, ስህተቱ ብዙ ነው/፪/
ከቶ በሰው ፍቃድ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ትንቢት እንዳልመጣ/፪/
ይነግረናል መጽሐፍ ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ከሕግ እንዳንወጣ
ይነግረናል መጽሐፍ ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ከሕግ እንዳንወጣ
ይመክረናል መጽሐፍ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ከሕግ እንዳንወጣ
እንጠይቅ መምህራን
,,,,,,,,,,,,,, ያሉ
በደረጃ/፪/
እናንብብ መጽሐፍት ,,,,,,,, ይሁኑን ማስረጃ/፪/
መጽሐፍ ቅዱስን
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ሁሉም ያነበዋል
ምእራፍ እና ቁጥሩን ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ሁሉም ይጠቅሰዋል
በዚህ ብቻ አይበቃም ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ተርጓሚ ያሻዋል/፪/
ምእራፍ እና ቁጥሩን ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ሁሉም ይጠቅሰዋል
በዚህ ብቻ አይበቃም ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ተርጓሚ ያሻዋል/፪/
/ዝማሬ፥ በሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደ ቂርቆስ/
No comments:
Post a Comment