በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ልጅህ፥ ክፉ ከሆነ፦
* እንደ ቃየል በቅናት ካደገ የገዛ ወንድሙን ይገድላል። (ዘፍ ፬፥፭)
* እንደ ካም ካደገ ያንተኑ ሃፍረት ይገልጥብሃል። (ዘፍ ፱፥፳፩-፳፪)
* እንደ ዲና ካደገች ሂዳ ከጠላቶችህ ትወዳጃለች። (ዘፍ ፴፬፥፩)
* እንደ ዔሳው ካደገ ምቀኛ ይሆንብሃል። (ዘፍ ፲፯፥፵፩-፵፭)
* እንደ ይሁዳ ልጆች ካደገ የከፋ ይሆንብሃል። (ዘፍ ፴፰፥፩-፲፩)
* እንደ ሮቤል ካደገ ሚስትህን ይቀማሃል። (ኩፍ ፳፰፥፴፭-፵፬)
* እንደ አፍኒንና ፊንሐስ ካደገ ታቦት ሻጭ ይሆንብሃል። (፩ኛ ሳሙ፪፥፲፪)
* እንደ አምኖን ከደገ የገዛ ኅህቱን ይደፍርብሃል። /፪ኛ ሳሙ ፲፫፥፩-፲፱)
* አንደ አቤሴሎም ካደገ አንተንም ያሳድድሃል። (፪ኛ ሳሙ ፲፯፥፳፩-፳፬)
ልጅህ፥ መልካም ከሆነ፦
* አንደ ሴምና ያፌት ካደገ ሃፍረትህን ይደብቅልሃል። (ዘፍ ፱፥፳፫)
* አንደ ዮሴፍ ካደገ በችግርህ ደራሽ ይሆንልሃል። (ዘፍ ፴፱፥፯-፳፫)
* እንደ ይስሐቅ ካደገ ታማኝ ሆኖ ራሱን ይሰዋል። (ዘፍ ፳፪፥፱)
* እንደ ሳሙኤል ካደገ የእግዚአብሔር ሰው ይሆንልሃል። /፩ኛ ሳሙ ፫፥፲፯-፳)
* እንደ ዳዊት ካደገ የአገርህን ጠላት ያጠፋልሃል፤ በሰውም በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ ይሆንልሃል። /፩ኛ ሳሙ ፲፯፥፴፬-፶፬)
"ልጆች ቢኖሩህ (በክርስቶስ ፍቅር) ምከራቸው፤ ከሕፃንነታቸው ጀምረህ ትሕትናን አስተምራቸው።" (ሲራ ፯፥፳፫)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ክብር ለድንግል ማርያም!
ምንጭ፦ ዛክ ኢትዮጵያ
No comments:
Post a Comment