የሰይጣን አመሉ፦
ሰይጣን አምላክ እንዳለ ያምናል ይንቀጠቅጥማል፤
ቢኾንም
ግን፥ የጌታን ቸርነቱንና ኃይሉን ይክዳል፤
ሰይጣን
ለአመሉ፥ ከቅዱስ ቃሉ ጥቅስ ይጠቅሳል፤
የብርሃን
መልአክ እንዲመስል፥ ራሱን ይለውጣል።
የሰይጣን ጉዞ፦
የክርስቶስን፥ የባህሪይ አምላክነት ያስክድሃል፤
ከድንግል ማርያም ፍቅር፥ ሊያርቅህ
ይኳትናል፤
ከቅዱስ
መልአክት ተራዳኢነት እቅፍ ያስርቅሃል፤
በመንፈሳዊ
ሕይወት፥ እንዳትጎለብት ይጎስምሃል።
የቅዱሳን አበው ተጋድሎ፦ እንደ-ኢምኒት አድርጎ ያሳይሃል፤
ዶሮ
ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ፥ ሦስት ጊዜ አምላክህን ያስክድሃል፤
የቅዱሳን ምልጃ፥ እንኳን በአጸደ ነፍስ በአጸደ ሥጋ የለም ይልሃል፤
ለምዕመናን
ተስፋ አስቆራጭ እንድትኾን በቅዱስ ስፍራ ይሾምሃል፤
ከእውነታኛው
የሃይማኖት መንገድና ከኢየሱስ
ጥልቅ ፍቅር ያስርቅሃል፤
አንዴ
ከመንገዱ ፍቅቅ ስላደረገኽ በዓለማዊ ዕይታና ምኞት ይዘፍቅሃል።
ፆም ፀሎት ሥግደት እንዳታደርግ ይወተውትሃል፤
በሥጋ
ወደሙ እንዳትከብር እንከን ይፈጥርብሃል።
በመጨረሻም፥ በራስህ እንድትታበይ ያደርግሃል፤
በአንድ
ምላስ፦ እውነተኛው ቃልህን ያሳጥፍሃል፤
እኔስ
ከማንና ከማን አንሳለው እንድትል ያነሳሳሃል፤
ባደፈ
ልብስ በእግዚአብሔር
ፊት ሊከስህ ይቆማል።
No comments:
Post a Comment