1 ሐሜት፦ ያለ
መሣሪያ ሰውን መግደል ነው።
2 ማጉረምረም፦
ባገኙት በቃኝ ብሎ አለማመስገን ነው።
3 ቁጣ፦
ከስድበ የሚያደርስ የክፉ አድራጎት መሠረት ነው።
4 ብስጭት፦
የተበሳጩበትን ነገር ሳይሆን ተመልሶ ራስን የሚጎዳ መርዝ፣ ከክህደት የሚያደርስ የኃጢያት ምንጭ፤
ጭንቀትን የሚያነድ ትንሽ ክብሪት ነው።
5 መዋሸት፦
እውነተኛ ሠው ሳይታዩ የሚጎዱበት ረቂቅ የሰይጣን ጦር ነው።
6 መርገም፦
አቅም ሲያን ወደ ላይ የሚወረወር የደካማ ሰዎች ቀስት ነው።
7 መሳደብ፦
ህሊናን የሚያቆስል ቁስሉ ቶሎ የማይድን አቅም የሌላቸው ሰዎች ዱላ ነው።
8 ዋዛ ፈዛዛ፦
በስልት የሚቃኙት የሥራ ፈቶች ገበና ነው።
9 የማይገባ
ሳቅ፦ ሐላፊ አገዳሚውን የሚያጠመዱበት የአመንዝራዎች ወጥመድ ነው።
10 መሳለቅ ፦
በአካል ጉዳተኛ ሰው ላይ የሚዘበቱበት የመርገም ስንቁ ወግ ነው።
ዋቢ መፅሐፍ ፦
ያለ ጭንቀት የመኖር ምስጢር