Monday, October 14, 2013

ምርጥና እጹብ ድንቅ አስር የአብው ብሂላዊ ምክር፦



1. ትግል፣ ተናና መከራ ከሌሉ የድል አክሊል፤ ጠላት ከሌለ ድል ማድረግ አይቻልም። /ታላቁ ባስልዮስ/

2. በመንፈሳዊ መንገድ ውስጥ ዝግ ብለህ አትጓዝ። በጎዳና ላይ በምትመለከታችው ትዕይንቶች አማካይነት አትማረክ፤ አትቁምም ጠላቶችህም ሆኑ ወዳጆችህም ያሰናክሉህ ዘንድ አትፍቀድላቸው። /አቡነ ሺኖዳ/

3. የከበሩ አባቶቻችን ልጆች ልትሆኑ ከወደዳቹሁ እነርሱ የጻፉትን (ያስተማሩት) እንጂ ምንም ሌላ አትመኑ። /ቅዱስ አትናቴዎሰ/

4. ጠላት በበዛበት ቦታ የምኖር ከሆነ ብርቱ ወታድር እሆናለሁ። /አባ ጴሜን/

5. ፍቅር፦ በእውነት ሰማያዊ ኀብስትና የአእምሮ ምግብ ነው። /ቀለሜንጦስ ዘእስክንደርያ/

6. ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ጽናት ብዛት ያስረዳል፤ ባልንጀሮቹ ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል፣ የምቀኝነቱን ጽናት ያስረዳል። /ማር ይስሐቅ/

7. ፍቅር፦ መያዣ የሌለውን የሰው ልብ አስሮ ለመሳብ የሚያገለገል የሠላም መንገድ ነው። /አንገረ ፈላስፋ፤ ሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ/

8. አሁን የምንኖራት ሕይወት ምን ያህል ውድ እንደሆነች ልታውቅ ትወዳለህን? ይህች ሕይወት ለዘለዓለማዊ ሕይወታችን መሠረት የትግል ዐውድማ፣ እንዲሆም በገነት ያለችውን አክሊል የምትሰጥ ናት። /ዮሐንስ አፈወረቅ/

9. ልማት ማለት መሬትን መቆፈር ብቻ አይደለም። የሰውን ልቦና በትምህርተ ወንጌል ቆፍሮ ማለምለም፣ በሰው አእምሮ ፍቅርና ስምምነት መዝራትና መትክል፣ ሰውን ከስህተት መመለስና ማስተማር፤ ከልማቶች ሁሉ የበለጠ ነው። /ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ/

10. የትሕትና ከፍታ እጅግ ታላቅ ነው፤ የመታበይ ጥልቀት ደግሞ እጅግ ጥልቅ ነው፤ የመጀመረያውን እንድትከተል፥ ወደዚህኛው ደግሞ እንዳትወድቅ እመክርሃለሁ። /አባ ኤስድሮስ/


ዋቢ መፅሐፍ ብሂለ አበው 2005 @ማኅበረ ቀዱሳን

Saturday, August 24, 2013

“አዳም የት ነህ?” በቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)


ከሩቅ ይሰማኛል
የቤተ- ክርስቲያን ደውል

ነፍስን የሚያማልል
ልብን የሚያባብል

እንደ አዲስ የሆነ
እንደ አዋጅ የሆነ
ከቀኑ ሁሉ ጠዋት እሁድ የገነነ
ከእለት ሁሉ ግህዝ እሁድ የገነነ

ማለዳ ሰንጥቆ የሚያስገመግም
ሠመመን መሳይ ድምፅ ከሩቅ ሚሰማ
ቀላቀሎ የያዘ የካህናት ወረብ የካህናት ዜማ

ንፋስ የሚያመጣው አልፎ-አልፎ ሽው የሚል
ተነስ ቀድሰ የሚል አዳም የት ነህ የሚል

Tuesday, August 6, 2013

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም (ክፍል ሁለት)

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ


ቤተክርስቲያን እመቤታችንን የምታከብርበት አስፈላጊና ዋና ዋና ምክንያቶች

1.        መንፈስ ቅዱስ ስለጸለላት /መንፈስ ቅዱስ በርሷ ላይ ስለሆነ/፣
2.      የእግዚአብሔር እናት /እመአምላክ ስለሆነች/፣
3.      ዘለማዊ ድንግል ስለሆነች፣
4.      ቅድስት ስለሆነች፣
5.      መንፈስ ቅዱስ ስለመሰከረላት፣
6.     ጌታ ራሱ ስላከበራት፤
7.      ስለ ተአምራቷና ስለተቀደሰው መታየቷ ናቸው። ይህም /በተለያየ ጊዜያት/ በግብጽ የመገለጽ ክብር ነው።

ክብሯም፦ በቤተክርስቲያን ንዋየቅዱሳት፣ በመዝሙራት፤ በቤተክርስቲያን ጸሎት ምልጃዋን በመለመን በዓላቷን በማክበር እና አንዱን ጾማችን በስሟ በመጾማችን ይገለጣል።

Saturday, July 6, 2013

ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ነው ወይስ ተማላጅ ?



    ኢየሱስን ክርስቶስ ክብር ይግባውና አማላጅ ነው የሚሉ ወገኖች የሚከተሉትን ጥቅሶች ማስረጃ ነው ብለው ያቀርባሉ።

                  “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።ዮሐ 146 ይህን በመጥቀስ አማላጃችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ይላሉ። ነገር ግን ይህን ጥቅስ የሚያስረዳን ስለ አማላጅነቱ ሳይሆን አብን ለማወቅ ክርስቶስን በቅድሚያ ማወቅና ማመን እንደሚገባ ነው። ዛሬ የይህዋ ምስክሮች ነን እንደሚሉት እንደ ጆቫዊትነሶች ወይም እንደ አሕዛቦች ክርሰቶስን ሳያምኑና አምላክነቱንና ፈጣሪነቱን ሳንቀበል አምላካችን አብ ብቻ ነው እያልን ብናወራ ዋጋ እንደሌለው የሚገልፅ ቃል ነው። ይህንንም ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያረጋግጥልን በዚሁ ጥቅስ ቀጥሎእኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር።”  ዮሐ 147 ብሏል።

            “በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።ስላለ ወደ አብ የሚወስደን አማላጅ ክርሰቶስ ነው የምንል ከሆነ፦አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፥ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም” /ዮሐ 637/ “አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም” /ዮሐ 644/ ከአብ የተሰጠው ካልሆነ ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም። /ዮሐ 665/  ሲል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተናግሯናልና እዚህ ጋር ደግሞ አማላጁ አብ ሊሆን ነው ማለት ነው። ይህ ደግሞ ትልቅ ስህተትና ኑፋቄ ነው። በሌላ ጥቅስ ላይ ደግሞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለእኛመንፈስ ቅዱስይቃትታል የሚል ፅፏልናመንፈስ ቅዱስንም አማላጅልንለው ይሆን? ታዲያ አብንም፣ ወልድንም፣ መንፈስ ቅዱስንም፤ አማላጅ እያሉ እንዴት ይዘልቁታል?

Thursday, June 20, 2013

“መጽሐፈ ጨዋታ ወ መንፈሳዊ”



ማርያም ሰማይን መሰለች፤ ከቶ እሳቱ አጥቁሯት ይሆን። {“በእሳት ሲነድድ” ዘጸ 3፥2 በእሳት ነበልባል” ሐዋ 7፥30} አይሁድ ቀን ሳለ በምድር ሲሄዱ የተናቀው ደንጊያ እንቅፋት ሆነባቸው። {“ግንበኞች የናቁት ድንጋይ” መዝ 11822፤ ማቴ 21 42፤ ማር 12 10-11፤ ሉቃ 20 17።} ምነው አስተውለው ቢሄዱ፤ ኒቆዲሞስ ግን በሌሊት ሲሄድ በውኃ ውስጥ መንገድ አገኘ። {ዮሐ 3፥1 ፣ 4፣ 9፤ 7፥50፤ 19፥39።}

ውኃም አ፭ ሺ ከ ፭፻ ዘመን መክና የነበረች አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ወለደች። {“አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል እግዚአብሔር።” ኢሳ 541አንቺ የማትወልጅ መካን፥ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፥ እልል በዪና ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና ተብሎ ተጽፎአል።” ገላ 427 “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው።” ዮሐ 112}

Wednesday, June 19, 2013

ሾፌሮችንና ተሳፋሪዎችን በመንገዳቸው ላይ የሚያጠቁ ክፉ መንፈሶች!

                        “በማለዳ መያ’ዝ” በመልአከ መንክራት ግርማ ወንዱሙ

ሰዎች በልዩ ልዩ ምክንያቶች የትራንስፖርት ዘዴዎች ማለትም በአውሮፕላን፣ በመርከብ፣ በባቡር፣ በመኪና በመጠቀም፤ ከቦታ ወደ ቦታ ይዘዋወራሉ። ጉዞ ጀምረው በሚገጥማቸው አደጋ፣ ያሰቡበት ሥፍራ ሳይደርሱ ወጥተው የቀሩ፤ ወደ ቤታቸውና ወደ ቤተሰባቸው ያልተመለሱ ብዙዎች ናቸው።

በመጓጓዣ ዘዴዎች ላይ የሚደርሱ የመጋጨት፣ የመከስከስ፣ የመገልበጥ፣ የመቃጠል፣ የመስመጥ ወዘተ .... አደጋዎች፤ ከግማሽ በላይ መንስኤያቸው ከክፉ መናፍስት ምሪት ጋር የተያያዙ ናቸው።

አውሮፕላን አብራሪዎች፣ የመርከብ ካፒቴኖች፣  የባቡርና የመኪና ሹፌሮች፤ ኃላፊነታቸው የመክበዱን ያህል፤ የማይጸልዩና መንፈሱን በጸሎት አስረው የማይነቀሳቀሱ ከሆነ፤ የመናፍስቱ ጥያቄዎች የማያቋርጥ የመንገድ ላይ ጦርነት ይሆንባቸዋል።

ብዙ ጊዜ በዲያቢሎስ አማካኝነት በሁሉም የመጓጓዣ ዘዴዎች ላይ የሚደርሰው አደጋ ተመሳሳይነት ያለው ነው። ለዚህ ገለፃችን፣ አንዱ የሆነውን በመኪና ላይ የሚያደርሰውን አደጋ፤ በምሳሌነት እንመልከት፦

Tuesday, June 18, 2013

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መድኃኒታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው የሚናገረውን?


        ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በተለያየ መልክቶቹ "ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።" /ገላ 614/ ቢል "ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።" /ገላ 18/ ቢለን እንኳን በአንድም በሌላም መንገድ ስለቅዱሳን ይሁንም ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሳይነግረን፣ ሳያስተምረን፣ ሳይሰብከን፤ ግን አላለፈም።

        ለዚህ ደግሞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ክርስቲያኖች ባስረዳቸው እውነተኛ አስተምህሮ ድንግል ማርያም ንጽሕት፣ ድንግል መሆኗን፤ መስክሯል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ለክርስቶስ አገልግሎት በተጠራበት ግዜ "እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና" /2ኛ ቆሮ 11 2/ ይላል። ታዲያ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በትንቢተ ሕዝቅኤል /44 2/ የተነገረውን የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ ሲናገር እመቤታችን ድንግል ማርያም ንጽሕት፣ ድንግል፣ ለክርስቶስ በክርስቶስ እንደሆነች አስረግጦ አስረድቶናል።