Thursday, June 20, 2013

“መጽሐፈ ጨዋታ ወ መንፈሳዊ”



ማርያም ሰማይን መሰለች፤ ከቶ እሳቱ አጥቁሯት ይሆን። {“በእሳት ሲነድድ” ዘጸ 3፥2 በእሳት ነበልባል” ሐዋ 7፥30} አይሁድ ቀን ሳለ በምድር ሲሄዱ የተናቀው ደንጊያ እንቅፋት ሆነባቸው። {“ግንበኞች የናቁት ድንጋይ” መዝ 11822፤ ማቴ 21 42፤ ማር 12 10-11፤ ሉቃ 20 17።} ምነው አስተውለው ቢሄዱ፤ ኒቆዲሞስ ግን በሌሊት ሲሄድ በውኃ ውስጥ መንገድ አገኘ። {ዮሐ 3፥1 ፣ 4፣ 9፤ 7፥50፤ 19፥39።}

ውኃም አ፭ ሺ ከ ፭፻ ዘመን መክና የነበረች አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ወለደች። {“አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል እግዚአብሔር።” ኢሳ 541አንቺ የማትወልጅ መካን፥ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፥ እልል በዪና ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና ተብሎ ተጽፎአል።” ገላ 427 “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው።” ዮሐ 112}


ከቶ ልጅነት አይቀርም {“አንተ ልጄ ነህ።” መዝ 2፥7፤ ማቴ 3፥17፣ 17፥5 ፤ ማር 1፥10 ፤ ሉቃ 3፥22 ፤ ሐዋ 13፣3 ፤ ዕብ 11፣5 ፣ 5፣5 ፤ 2ኛ ጴጥ 1፥17።} ኢየሱስ ክርስቶስ ከዮሐንስ ጋር እጫወት ብሎ ከዮርዳኖስ ባሕር ላይ ወደቀ። {ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ ባሕር እንደሄደ። መዝ 114፥5 ፤ ማቴ 3፥13 ፤ ዮሐ 10፥40።} በርሱም ደንጋጤ ሰማያት ተከፈተ፣ አባቱም ከላይ ሆኖ ልጄ ወዳጄ ሲል  በራሱ ላይ ዋለ። መንፈስ ቅዱስም ርግብ ሆኖ በራሱ ላይ ዋለ። {እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው እንዳለ። ማቴ 3፥16-17 ፤ ማር 1፥10-11 ፤ ሉቃ 3፥22 ፤ ዮሐ 1፥32-34።}

ዮሐንስ፦ እነሆ የእግዚአብሔር በግ {ዘፍ 22፥8 ፤ ኢሳ 53፥7 ፤ ዮሐ 1፥29፣ 36።} እያለ ለምን ያሳየዋል፥ ያለጊዜው ይታረድ ብሎ ነውን። {ዮሐ 2፥4፣ 7፥6፣ 7፥8።}  ቢታረድስ፥ {ማቴ 10፥39 ፤ ማር 8፥35፣ 15፥39 ፤ ሉቃ 23፥46 ፤ ዮሐ 19፥30፤ቲቶ 2፥4 ፤ 1ኛ ዮሐ 3፥16።} የታደሉና የተመረጡ ጀግኖች ይበሉታ እንጂ ፈሪ አይበላውም። {“የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል።” ዮሐ 6፥ 54-57።} እርሱም ምስጢር አይችልም ብናበላውና ብናጠጣው ከአባቱ ዘንድ ያየውን ሁሉ ነገረን።

ለቀበሮዎች ጉድጓድ አላቸው፣ ለሰማይ ወፎች ማረፊያ ዛፍ አላቸው፣ ለሰው ልጅ ግን እራሱን የሚያስጠጋበት የለውም፤ ይላል። {ማቴ 8፥20 ፤ ሉቃ 9፥58።} ለካ፥ ሰማይና ምድር ቢጠበው ነው ከሰው ውስጥ መጥቶ ያደረው፤ {ዮሐ 3፥16 ፤ ሮሜ 8፥4 ፤ ገላ 4፥4ዕብ 11፥18 ፤ 1ኛ ዮሐ 4፥9፣ 10፣ 14።} እንደባርያም የመሰለው። {ፊል 2፥7።}

ኢየሱስ ሠርግ ቢጠሩት በቃና ዘገሊላ፥ ውኃውን ጠጅ አድጎ አጠጣ፣ በሰው ሠርግ እንደዚህ የሆነ፤ { ዮሐ 2፥1-11፣ 4፥46} በራሱ ሠርግ እንዴት ይሆን!። {ማቴ 22፥1-14፣ 25፥1-46።} የእግዚአብሔር ልጅ ሠርግ አይቼ፥ ከድግሱም በልቼ፣ ጠጠቼ፤ ከዚያ ወዲያ ምነው በሞትሁ። {ራእ 19፥7-9}

ኢየሱስ ክርስቶስ ኑ የአባቴ ቡሩካን ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን ውረሱ ይላል፤ {ማቴ 25፥34} ዓለም ሳይፈጠር ምን ኖሮታል፤ ጥበቡ አይታወቅ። {ዳዊ 5፥16 ፤ ምሳ 2፥6 ፤ መክ 1፥13 ፣ 7፥10 ፤ ሮሜ 11፥13 ፤ 1ኛ ቆሮ 2፥7 ፤ ቆላ 2፥3።}

ዋቢ መጽሐፍ፦ መጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወ መንፈሳዊ ገፅ ፲፰-፲፱ ክፍል ፬ (ከዘነበ ኢትዮጵያዊ በ1957 ዓ/ም)
           *********************      ****************        ********************

ማሳሰቢያ፦ መጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወ መንፈሳዊ የነበባችሁ ካላቹ ከላይ በቀረበው ዓይነት አይደለም መጽሐፉ የተፃፈው። ይህ ጹሑፍ “መጽሐፈ ጨዋታ ወ መንፈሳዊ” በሚለው ክፍል ሲሆን ክፍል 4 ገፅ ከ18-19 መጽሐፉ ላይ ምንም ዓይነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ምዕራፍና ቁጥር የለውም።

ቢሆን ግን መጽሐፉ ሳነበው ስለመሰጠኝ “መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም።” /1ኛ ቆሮ 2፥13/ በሚለው መሠረት እንደ እግዚአበሔር ፍቃድ ሙሉ ጹሑፉ አቅርቤዋለሁ። ታዲያ በቅንፍ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን  ምዕራፎችና ቁጥሮችን ያደረኩት እኔ ነኝ።


No comments:

Post a Comment