Sunday, November 30, 2014

መጀመሪያ ሰው ነኝ (ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት)



አንድ ወዳጄ በየገጸ ድሩና በየውይይት መድረኩ የሚሰማውንመጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ፣ መጀመሪያ ትግሬ ነኝ፣ መጀመሪያ አማራ ነኝየሚል ክርክር አየናአንተ መጀመሪያ ምድንነህ?›› ሲል ጠየቀኝ፡፡
 
እኔ መጀመሪያ ሰው ነኝ፡፡ የተፈጠርኩትም ሰው ሆኜ ነው፡፡ አምላክም የፈጠረው ሰውን ነው፡፡ ቡድን፣ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ጎሳ፣ ነገድ የሚባሉ ነገሮችን ፈጠረ የሚል መጽሐፍም ትምህርትም አላገኘሁም፡፡ ክብርም፣ ሥልጣንም፣ ጥበብም፣ ፈጣሪውን መምሰልም የተሰጠው ለሰው ነው፡፡ መላእክት ሲፈጠሩ በማኅበር ነው የተፈጠሩት፡፡ አንድ ላይ ነው የተገኙት፡፡ ሰው ግን ሲፈጠር በየተራ ነው፡፡ መጀመሪያ አዳም፣ ከዚያ ሔዋን፣ ከዚያ ቃየል፣ ከዚያ አቤል እያለ ተራ በተራ፡፡ ቡድኖቹን ሰው በኋላ ራሱ ፈጠራቸው እንጂ አብረውት አልተፈጠሩም፡፡

መጀመሪያ ሰውነቴ ነበረ በኋላ ቡድኔ መጣ፡፡ በኋላ የመጣው ቡድኔ በፊት የነበረውን ሰውነቴን ከዚህ አትለፍ ከዚህ አትውጣ፣ ከዚህ አትዝለል ከዚህ አትሻገር አለው፡፡ ቡድኔ በእኔ መጠራት ሲገባው እኔ በቡድኔ ተጠራሁ፡፡ ለእርሱ ህልውና ሲል እኔን ሰዋኝ፡፡ እርሱ ሳይመጣ በፊት ግን እኔ ሰውዬው ነበርኩ፡፡

መጀመሪያ ሰው ስለነበርኩ መጀመሪያ ሰው ነው መከበር ያለበት፣ መጀመሪያ ሰውነቴ ነው መብት የሚያስፈልገው፣ ሰውነቴን አሥረህ፣ ገርፈህ፣ ገድለህ፣ ነጥቀህ፣ ቀምተህ ቡድኔን ከየት ታገኘዋለህ? እኔን ትተህ እንዴት እኔ ለፈጠርኩት ቅድሚያ ትሰጣለህ? እኔን ንቀህ እንዴት እኔነት ተሰባስቦ ላቋቋመው ቡድን ክብር ትሰጣለህ? ይኼማ ሐሰት ነው፡፡ ሴሎቹን ገድለህ ሰውየውን ማኖር ትችላለህ? ገጾቹን ገንጥለህስ መጽሐፉን ታኖራለህን? ከብቶቹን አርደህ ስለ መንጋው መጨነቅስ ምን ማለት ነው?

Sunday, November 23, 2014

መልካምና ክፉ ልጅ


   በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ሜን!


ልጅህ፥ ክፉ ከሆነ፦

* እንደ ቃየል በቅናት ካደገ የገዛ ወንድሙን ይገድላል። (ዘፍ ፬፥፭)

* እንደ ካም ካደገ ያንተኑ ሃፍረት ይገልጥብሃል። (ዘፍ ፱፥፳፩-፳፪)

* እንደ ዲና ካደገች ሂዳ ከጠላቶችህ ትወዳጃለች። (ዘፍ ፴፬፥፩)

* እንደ ዔሳው ካደገ ምቀኛ ይሆንብሃል። (ዘፍ ፲፯፥፵፩-፵፭)

* እንደ ይሁዳ ልጆች ካደገ የከፋ ይሆንብሃል። (ዘፍ ፴፰፥፩-፲፩)

* እንደ ሮቤል ካደገ ሚስትህን ይቀማሃል። (ኩፍ ፳፰፥፴፭-፵፬)

* እንደ አፍኒንና ፊንሐስ ካደገ ታቦት ሻጭ ይሆንብሃል። (፩ኛ ሳሙ፪፥፲፪)

* እንደ አምኖን ከደገ የገዛ ኅህቱን ይደፍርብሃል። /፪ኛ ሳሙ ፲፫፥፩-፲፱)

* አንደ አቤሴሎም ካደገ አንተንም ያሳድድሃል። (፪ኛ ሳሙ ፲፯፥፳፩-፳፬)

ልጅህ፥ መልካም ከሆነ፦ 

* አንደ ሴምና ያፌት ካደገ ሃፍረትህን ይደብቅልሃል። (ዘፍ ፱፥፳፫)

* አንደ ዮሴፍ ካደገ በችግርህ ደራሽ ይሆንልሃል። (ዘፍ ፴፱፥፯-፳፫)

* እንደ ይስሐቅ ካደገ ታማኝ ሆኖ ራሱን ይሰዋል። (ዘፍ ፳፪፥፱)

* እንደ ሳሙኤል ካደገ የእግዚአብሔር ሰው ይሆንልሃል። /፩ኛ ሳሙ ፫፥፲፯-)

* እንደ ዳዊት ካደገ የአገርህን ጠላት ያጠፋልሃል፤ በሰውም በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ ይሆንልሃል። /፩ኛ ሳሙ ፲፯፥፴፬-፶፬)

"ልጆች ኖሩህ (በክርስቶስ ፍቅር) ምከራቸው፤ ከሕፃንነታቸው ጀምረህ ትሕትናን አስተምራቸው።" (ሲራ ፯፥፳፫)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ክብር ለድንግል ማርያም!

ምንጭ፦ ዛክ ኢትዮጵያ

Thursday, November 13, 2014

"ምስጢራዊ ቡድን" ክፍል ፪ በመምህር ምሕረትተአብ አሰፋ


(የደብረ መዊዕ /ሚካኤል / ስብከተ ወንጌል ሐላፊ

 በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።” (፩ኛ ጴጥ ፫፥፲፭)

የዚህምስጢራዊ ቡድንየተሰኘው ትምህርታዊ ምላሽ ዓላማ፦ ከውጭ ኾነው፥ ቤተ ክርስቲያናችንን መዋጋት የተሳናቸው፣ እኛን አኽለውና እኛን መስለው ወደ ውስጣችን በመግባት፣ በዲቁናና በቅስና ከተቻለም እስከ ጵጵስና መሐረግ በመድረስ፣ ቀን ጠብቀውና ጊዜ አመቻችተው፣ ጸረ-ክርስትናን የኾነን እምነት እንደ አዲስ እንደተቀበሉ በማወጅ፣ የእምነቱ ተከታይዎች ላይ ጥርጣሬ በመዝራትና ከተቻለም አስክዶ በመውሰድ፤ ጸረ-ክርስትናን እንቅስቃሴ የሚያደርጉትን ወገኖች ማጋለጥ ሲሆን፤ በሌላ መልኩ፥ እነዚህ ጸረ-ቤተ ክርስቲያ ኃይሎች የዘሩትን የኑፋቄ ትምህርት ሰምተው፣ ግራ የተጋቡ አማንያንን ለማረጋጋትና የያዙት እምነት እውነተኛ የሕይወት መንገድ መሆኑን፣ ቤተ ክርስቲያንም፥ ለሚጠይቋት ሁሉ በቂና ከበቂ በላይ የኾነ መልስ እንዳላት ለማስገንዘብ ነው።

ከዚህ በፊት (በምስጢራዊ ቡድን በክፍል እና በማፈናጠር ይመልከቱ) እንደገለጽነው አንድ ሠው የፈለገውን እምነት እንዲያምንና ያመነበትን እምነት እንዲከተል ሕገ-መንግሥታዊም ሆነ ሕገ-እግዚአብሔራዊ ነፃነት እንዳለው ቢታወቅም፤ የራስን እምነት፥ በነፃነት ማራመድ፣ ያወቁትን ለራስ እምነት ተከታዮች ማሳወቅ እየተቻለ፤ የሌላውን እምነት፥ ማንቋሸሽና ማጥላላት፣ መለኮታዊ የሆኑትን ቅዱሳት መፃሕፍትን መንቀፍ፣ አማንያኑን መዝለፍ፤ ተገቢ ነው ብለን አናምንም!

መቼም ዛፍ እራሱን ለመከላከል ካልሆነ በቀር መኪና ገጭቶ አያውቅም እንደተባለ፤ ሳንደርስባቸው ለደረሱብን፣ ሳንነካቸው ለነኩን፤ ዶግማችንና ቀኖናችን እንዲሁም ሥርዓታችንን አልፎም ትውፊታችንን ለመናድ ለሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች እንደየ አመጣጣቸው ተገቢውን መልስ መስጠት ግድ ይለናል።

ሁኔታዎች አሳሳቢ እየሆኑ ነው፤ የተነገሩት ትንቢቶች በአፋጣኝ እየተፈጸሙ ነው። ወደድንም ጠላንም፥ አሁን የመጨረሻው መጨረሻ ላይ ነን።

ስለዚህ በአፋጣኝ ይህንን ቪሲዲ ይመልከቱና ላላዩት በማሳየት ክርስቲናዊ ግዴታዎን ይወጡ።
 
የኻሊድ ካሳሁንና የዳኢ ኻሊድ ክብሮም የተዛባ  አስተምህሮታቸውንና እነርሱ ስተው፣ ሌላውን ለማሳት የተደረገውን ሴራ የሚያጋልጥ፣ ጥልቅና ድንቅ፣ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፍቃድ አጋዥነት ምጡቅ ምላሽ በወንድማችንና በመምህራችን በመምህ ምሕረትተአብ አሰፋ የተዘጋጀ ምስለ-ወድምፅ (ቪሲዲ) ይመልከቱና ላላዩት በማሳየት ክርስቲናዊ ግዴታዎን ይወጡ!


 

  ቀጣዩን፥ "ምስጢራዊው ቡድን" ክፍል ፪/ለን ይህን በማፈናጠር ይመልከቱ!


Sunday, August 24, 2014

“ጆሮዬም ሹክሹክታውን ሰማች” (ኢዮ ፬፥፲፪)


ይኼንን ርዕስ የተናገረ  “ጆሮዬም ሹክሹክታውን ሰማች” ያለ ፃድቁ ው። ፃድቁ ብ በክፉ በሽታና በጽኑ በተከዘ ጊዜ፥  ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት እንደመጡ ታላጽሐፍ ቅዱስ ይተርክልናልም፣ ተጽፎም እናነባለን

ቢኾንም ግን ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች በትንሹ ሐዘኑን ሊጋሩት ሞከሩ፣ ነገር ግን እስከ-መጨረሻው ሐዘኑን ሊጋሩት አልሉም። የኢዮብን፥ ሐዘኑን ሊጋሩት የመጡት ሰዎች እንኳን ከልባቸው ሊያዝኑለት ይቅና ሌላ የሐዘን ቁስል እንደጨመሩበት፣ ከማጽናናትም ይልቅ፥ እንዳይጽና በቁስሉ ቁስል ጨመሩበት፣  የኢዮብን፥ ብርታቱንና የጥንካሬውን እንዲሁም የፈሪሐ-እግዚአብሔሩን ውጤት ፍሬ-አልባ ለማስመሰል ያደረጉት ጥረት በፃድቁ ብ ዘንድ ዋጋ የለውም ነበር። ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆቹ ከንቱ ውትወታ፤ በፃድቁ ኢዮብ ዕይታ ሲታዩ እንዲህ ይገልፆቸዋል፦ "ለእኔም በምሥጢር ቃል መጣልኝ፥ ጆሮዬም ሹክሹክታውን ሰማች" ይላቸዋል።

በምሥጢር ቃል ማምጣታቸውና ጆሮውም ሹክሹክታቸውን መስማቱ፤ ለመጣበት ፈተና በብቃት ማለፍና ለመንፈሳዊ ተጋድሎውና ለሕይወቱ መቅረዝ እንዳደረገው እንመለከታለ። ወደ ታች ወረድ ሲል ደግሞ “የዝምታ ድምጽ ሰማሁ” ይላል። (ኢዮ ፬፥፲፮)

በዝምታ ድምጽ ውስጥ ብዙ መልእክት አለ! ነቢየ ኤልያስም በዝምታ ድምጽ ውስጥ ነበር እግዚአብሔር የተገለጠለት። እነሆም፦ “በእግዚአብሔርም ፊት ትልቅና ብርቱ ነፋስ ተራሮቹን ሰነጠቀ፣ ዓለቶቹንም ሰባበረ፥ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም። ከነፋሱም በኋላ የምድር መናወጥ ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በምድር መናወጥ ውስጥ አልነበረም። ከምድር መናወጥ በኋላም እሳት ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥም አልነበረም። ከእሳቱም በኋላ፥ ትንሽ የዝምታ ድምፅ ሆነ። በዚ በዝምታ ድምፅ ነበር የእግዚአብሔር ድምጽ የተሰማው። (፩ኛ ነገ ፲፱፥፲፪)

Tuesday, August 19, 2014

ከፕሮፌሰራችን ዕይታ፦ የማልስማማበት



ፕሮፌሰራችን መስፍን ወልደ ማርያም ለሃገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለሀሕጉራችን፤ ትልቅ አስተዋጽዎ ካበረከቱ አንዱ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ስለ ፕሮፍ አጠቃላይ ስለሰሩት መልካም ስራዎች፣ ስላበረከቱት ታላቅ አስተዋጽዎ በዚች አነስተኛ ጹሑፍ ለመዘከር አይደለም፤ ይልቅ የፕሮፋችን ዕይታ፣ ተመክሮ፣ ልምድ፣ ሕይወት፤ በዚህ ባሳለፍነው ተከታታይ አምስት ሳምንታት ከምንወዳትና ከምናከብራት፥ ከመዓዛ ብሩ ጋር እያደረጉት ያለውን ቃለ-መጠይቅ እያዳመጥናቸው ነው።

ሦስት ነገስታንን በሕይዎታች የተመለከቱ እኚህ ፕሮፋችን፥ በንግግራቸውም ረጋ ያሉና አንደበተ ርዕቱ ናቸው፣ እጅግ ማራኪ በኾነ አገላለጽ ታሪኮችን ያማክላሉ፣ የራቀውን አቅርበው እያጣጣሙ እያስቃኙን ነው። ቢኾንም ከፕሮፌሰራችን ዕይታዎቻና ቅኝቶች፦ የማልስማማበት ነገሮች ቢኖሩም፤ ከማልስማማበት አንዱ ደግሞ “የመንፈሳዊ ልዕልና” ብለው በዘረዘሩት ውስጥ “የቱ ጳጳስ፣ የቱ ቄስ ነው? ድኾች ተጠቅተዋል፣ ፍትሕ ጎደለ፣ ሠው ተበደለ ብሎ የጮ። የለም!። ካሉ በኋላ በእርሶ ጊዜ፦ አቡነ ባስልዮስ፥ ከንጉስ እጅ እርስዎና ከእርስዎ ጋር ሊገረፉ የነበሩትን ሠዎች ስለታደጉ ብቻ “ከአቡነ ባስልዮስ በኋላ ማንም!” የለም ማለትዎን ስለማልቀበለው ከአቡነ ባስልዮስ በኋላ፦ ድኾች ተጠቅተዋል፣ ፍትሕ ጎደለ፣ ሠው ተበደለ ብው የጮኹ አሉ!፤  ለዚህም  ከታች ያለውን አነስተኛ ጹሑፍ ላዘጋጅ ወደድሁኝ። እንደ መረጃና እንደ-ማስረጃ ይኾነን ዘንድ እንሆ ኹለቱን፦

Sunday, August 10, 2014

የሁላችንም ሐሳብ



         በቅንነት፥ ብንነጋገርና ብንሠራ፣ የሁላችንም ሐሳብ ለኢትዮጵያ ይጠቅማል እንጂ አይጐዳም!”  (ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ)      

Sunday, July 6, 2014

ነገረ ክርስቶስ፦ ክፍል አንድ፤ በቀሲስ ታምራት ውቤ



            በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
         እግዚአብሔር ባዘጋጀልን ጉባኤ መንፈስ ቅዱስ በገለጠልን መጠን ስለጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መማር እንጀምራለን።

ስለ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቱ የሚዳስሳቸዉ ነጥቦች

  ቀዳማዊ ወድኅራዊ ሕያዉ ዘላለማዊ አምላክ ስለመሆኑ፤
 
  ቅድመ ዓለም ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት ድኅረ ዓለም ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያለ አባት ስለመወለዱ (ስለ ሁለቱ ልደታት
 
ስለ ድንቅ ልደቱና የልጅነት ህይወቱ፣ ስለ ጥምቀቱ፣ ስለ ትምህርቱና ስለ ተዓምራቱ፣ ስለ ህማሙ፣ ስቅለቱ፣ ሞቱ፣ ትንሣኤዉና ዕርገቱ፣ ዳግመኛም ለፍርድ ስለ መምጣቱወዘተይሆናል
 
        በቅድሚያ አንድን አካል "አምላክ" ነው ለማለት የአምላክነት ባህርያት ምን እንደሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል የሁሉ ነገር የማንነቱ መገለጫ ባህርዩ ነውና ሰለዚህ የአምላክነት ባህርያት የሚባሉትና የየትኛዉንም ሃይማኖት ተከታይ ወይም ፍልስፍና አራማጅ የሚያስማሙት፡-