የሕይወት ውኃው ለማግኘት፥ ከእንስቶች የለያት፣
የሕይወት ውኃ ኾነና፥ እርሷን ምንጩ አደረጋት፣
ማንም ለመርካት ቢፈልግ፣ ድንግልን፥ ንጉሥ ሾማት፣
በእቅፏ እንድታቅፈው፥ እናቱ እንድትኾን የመረጣት።
የሕይወት ውኃ ኾነና፥ እርሷን ምንጩ አደረጋት፣
ማንም ለመርካት ቢፈልግ፣ ድንግልን፥ ንጉሥ ሾማት፣
በእቅፏ እንድታቅፈው፥ እናቱ እንድትኾን የመረጣት።
ክርስቶስን ለማግኘት፥ እስኪ ቅዱና ጠጡ፤
ከድንግል ዘር፥ ሕይወታችሁን አጣፍጡ!።
ከድንግል ዘር፥ ሕይወታችሁን አጣፍጡ!።
ከምንጩ አጥልቁ፥ መቅጃችሁን ከጉድጓዱ፤
ይገባችኋል የእናቱን ፍቅር፥ የናቃት ሲሰግድ፣
የእርሱን እፎይታ ታገኛላችሁ ከጥልቁ ስትቀዱ፣
ያኔ ሕይወታችሁን ስታጣፍጡ በፍቅሯ ስትነዱ።
ይገባችኋል የእናቱን ፍቅር፥ የናቃት ሲሰግድ፣
የእርሱን እፎይታ ታገኛላችሁ ከጥልቁ ስትቀዱ፣
ያኔ ሕይወታችሁን ስታጣፍጡ በፍቅሯ ስትነዱ።
(ህዳር ፳፪/ ፳፻፯ ዓ/ም)