ማርያም ሰማይን መሰለች፤ ከቶ እሳቱ አጥቁሯት ይሆን። {“በእሳት ሲነድድ” ዘጸ
3፥2 “በእሳት ነበልባል” ሐዋ 7፥30} አይሁድ ቀን ሳለ በምድር ሲሄዱ የተናቀው ደንጊያ እንቅፋት ሆነባቸው። {“ግንበኞች
የናቁት ድንጋይ” መዝ 118፥ 22፤ ማቴ 21፥ 42፤ ማር 12፥ 10-11፤ ሉቃ 20፥ 17።} ምነው አስተውለው ቢሄዱ፤ ኒቆዲሞስ ግን በሌሊት ሲሄድ በውኃ ውስጥ መንገድ አገኘ። {ዮሐ 3፥1 ፣ 4፣ 9፤ 7፥50፤ 19፥39።}
ውኃም አ፭ ሺ ከ ፭፻ ዘመን መክና የነበረች አሁን የእግዚአብሔር ልጆች
ወለደች። {“አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል እግዚአብሔር።” ኢሳ 54፥1፤ “አንቺ የማትወልጅ መካን፥ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፥ እልል በዪና ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና ተብሎ ተጽፎአል።” ገላ 4፥27፤ “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው።” ዮሐ 1፥12}