Saturday, July 6, 2013

ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ነው ወይስ ተማላጅ ?



    ኢየሱስን ክርስቶስ ክብር ይግባውና አማላጅ ነው የሚሉ ወገኖች የሚከተሉትን ጥቅሶች ማስረጃ ነው ብለው ያቀርባሉ።

                  “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።ዮሐ 146 ይህን በመጥቀስ አማላጃችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ይላሉ። ነገር ግን ይህን ጥቅስ የሚያስረዳን ስለ አማላጅነቱ ሳይሆን አብን ለማወቅ ክርስቶስን በቅድሚያ ማወቅና ማመን እንደሚገባ ነው። ዛሬ የይህዋ ምስክሮች ነን እንደሚሉት እንደ ጆቫዊትነሶች ወይም እንደ አሕዛቦች ክርሰቶስን ሳያምኑና አምላክነቱንና ፈጣሪነቱን ሳንቀበል አምላካችን አብ ብቻ ነው እያልን ብናወራ ዋጋ እንደሌለው የሚገልፅ ቃል ነው። ይህንንም ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያረጋግጥልን በዚሁ ጥቅስ ቀጥሎእኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር።”  ዮሐ 147 ብሏል።

            “በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።ስላለ ወደ አብ የሚወስደን አማላጅ ክርሰቶስ ነው የምንል ከሆነ፦አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፥ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም” /ዮሐ 637/ “አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም” /ዮሐ 644/ ከአብ የተሰጠው ካልሆነ ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም። /ዮሐ 665/  ሲል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተናግሯናልና እዚህ ጋር ደግሞ አማላጁ አብ ሊሆን ነው ማለት ነው። ይህ ደግሞ ትልቅ ስህተትና ኑፋቄ ነው። በሌላ ጥቅስ ላይ ደግሞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለእኛመንፈስ ቅዱስይቃትታል የሚል ፅፏልናመንፈስ ቅዱስንም አማላጅልንለው ይሆን? ታዲያ አብንም፣ ወልድንም፣ መንፈስ ቅዱስንም፤ አማላጅ እያሉ እንዴት ይዘልቁታል?

Thursday, June 20, 2013

“መጽሐፈ ጨዋታ ወ መንፈሳዊ”



ማርያም ሰማይን መሰለች፤ ከቶ እሳቱ አጥቁሯት ይሆን። {“በእሳት ሲነድድ” ዘጸ 3፥2 በእሳት ነበልባል” ሐዋ 7፥30} አይሁድ ቀን ሳለ በምድር ሲሄዱ የተናቀው ደንጊያ እንቅፋት ሆነባቸው። {“ግንበኞች የናቁት ድንጋይ” መዝ 11822፤ ማቴ 21 42፤ ማር 12 10-11፤ ሉቃ 20 17።} ምነው አስተውለው ቢሄዱ፤ ኒቆዲሞስ ግን በሌሊት ሲሄድ በውኃ ውስጥ መንገድ አገኘ። {ዮሐ 3፥1 ፣ 4፣ 9፤ 7፥50፤ 19፥39።}

ውኃም አ፭ ሺ ከ ፭፻ ዘመን መክና የነበረች አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ወለደች። {“አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል እግዚአብሔር።” ኢሳ 541አንቺ የማትወልጅ መካን፥ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፥ እልል በዪና ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና ተብሎ ተጽፎአል።” ገላ 427 “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው።” ዮሐ 112}

Wednesday, June 19, 2013

ሾፌሮችንና ተሳፋሪዎችን በመንገዳቸው ላይ የሚያጠቁ ክፉ መንፈሶች!

                        “በማለዳ መያ’ዝ” በመልአከ መንክራት ግርማ ወንዱሙ

ሰዎች በልዩ ልዩ ምክንያቶች የትራንስፖርት ዘዴዎች ማለትም በአውሮፕላን፣ በመርከብ፣ በባቡር፣ በመኪና በመጠቀም፤ ከቦታ ወደ ቦታ ይዘዋወራሉ። ጉዞ ጀምረው በሚገጥማቸው አደጋ፣ ያሰቡበት ሥፍራ ሳይደርሱ ወጥተው የቀሩ፤ ወደ ቤታቸውና ወደ ቤተሰባቸው ያልተመለሱ ብዙዎች ናቸው።

በመጓጓዣ ዘዴዎች ላይ የሚደርሱ የመጋጨት፣ የመከስከስ፣ የመገልበጥ፣ የመቃጠል፣ የመስመጥ ወዘተ .... አደጋዎች፤ ከግማሽ በላይ መንስኤያቸው ከክፉ መናፍስት ምሪት ጋር የተያያዙ ናቸው።

አውሮፕላን አብራሪዎች፣ የመርከብ ካፒቴኖች፣  የባቡርና የመኪና ሹፌሮች፤ ኃላፊነታቸው የመክበዱን ያህል፤ የማይጸልዩና መንፈሱን በጸሎት አስረው የማይነቀሳቀሱ ከሆነ፤ የመናፍስቱ ጥያቄዎች የማያቋርጥ የመንገድ ላይ ጦርነት ይሆንባቸዋል።

ብዙ ጊዜ በዲያቢሎስ አማካኝነት በሁሉም የመጓጓዣ ዘዴዎች ላይ የሚደርሰው አደጋ ተመሳሳይነት ያለው ነው። ለዚህ ገለፃችን፣ አንዱ የሆነውን በመኪና ላይ የሚያደርሰውን አደጋ፤ በምሳሌነት እንመልከት፦

Tuesday, June 18, 2013

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መድኃኒታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው የሚናገረውን?


        ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በተለያየ መልክቶቹ "ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።" /ገላ 614/ ቢል "ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።" /ገላ 18/ ቢለን እንኳን በአንድም በሌላም መንገድ ስለቅዱሳን ይሁንም ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሳይነግረን፣ ሳያስተምረን፣ ሳይሰብከን፤ ግን አላለፈም።

        ለዚህ ደግሞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ክርስቲያኖች ባስረዳቸው እውነተኛ አስተምህሮ ድንግል ማርያም ንጽሕት፣ ድንግል መሆኗን፤ መስክሯል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ለክርስቶስ አገልግሎት በተጠራበት ግዜ "እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና" /2ኛ ቆሮ 11 2/ ይላል። ታዲያ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በትንቢተ ሕዝቅኤል /44 2/ የተነገረውን የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ ሲናገር እመቤታችን ድንግል ማርያም ንጽሕት፣ ድንግል፣ ለክርስቶስ በክርስቶስ እንደሆነች አስረግጦ አስረድቶናል።

"ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ" ሕዝ 37፥3 M/ Paulos MelekaSelase


        እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል! ስንወድቅ ስንነሳ፥ እግዚአብሔር ያውቃል!!! መግባት መውጣታችን ያውቃል። ማግኘት ማጣታችን ያውቃል። መውደቅ መነሳታችን ያውቃል። መብላት መጠጣታችንን ያውቃል። መራብ መጥገባችን ያውቃል። መጠጣት መርካታችን ያውቃል። ጥማታችንን ያውቃል። እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል!!!

        አቤቱ፥ አንተ መቀመጤንና መነሣቴን አንተ ታውቃለህ፤ መንገዶቼን ሁሉ እነሆ የቀደመውንና የኋላውን ሁሉ አንተ ታውቃለህ!!! (መዝ 138/9 1-6) / ጳውሎስ መልክዓ ሥላሴ (B. Th)

         "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ" ሕዝ 373  በሚል (ሰባኪ ወንጌል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ) በመ/ ጳውሎስ መልክዓ ሥላሴ (B. Th) የተሰጠ መንፈሳዊ ትምህርተ ወንጌል ተመልክተው ስጋዎትንና ነፍሶትን ይመግቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ተጋብዘዋል።


Monday, June 17, 2013

አስሩ ምርጥ ብሒላዊ ምክር፦

1 ሐሜት፦ ያለ መሣሪያ ሰውን መግደል ነው።

2 ማጉረምረም፦ ባገኙት በቃኝ ብሎ አለማመስገን ነው።

3 ቁጣ፦ ከስድበ የሚያደርስ የክፉ አድራጎት መሠረት ነው።

4 ብስጭት፦ የተበሳጩበትን ነገር ሳይሆን ተመልሶ ራስን የሚጎዳ መርዝ፣ ከክህደት የሚያደርስ የኃጢያት     ምንጭ፤ ጭንቀትን የሚያነድ ትንሽ ክብሪት ነው።

5 መዋሸት፦ እውነተኛ ሠው ሳይታዩ የሚጎዱበት ረቂቅ የሰይጣን ጦር ነው።

6 መርገም፦ አቅም ሲያን ወደ ላይ የሚወረወር የደካማ ሰዎች ቀስት ነው።

7 መሳደብ፦ ህሊናን የሚያቆስል ቁስሉ ቶሎ የማይድን አቅም የሌላቸው ሰዎች ዱላ ነው።

8 ዋዛ ፈዛዛ፦ በስልት የሚቃኙት የሥራ ፈቶች ገበና ነው።

9 የማይገባ ሳቅ፦ ሐላፊ አገዳሚውን የሚያጠመዱበት የአመንዝራዎች ወጥመድ ነው።

10 መሳለቅ ፦ በአካል ጉዳተኛ ሰው ላይ የሚዘበቱበት የመርገም ስንቁ ወግ ነው።

ዋቢ መፅሐፍ ፦ ያለ ጭንቀት የመኖር ምስጢር

Saturday, June 15, 2013

በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ "ባርያ" ማለት ምን ማለት ነው?


ወዳጆች ሆይ ቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ  በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሠላምና ፍቅር ይሁንላቹ!

* በመጽሐፍ ቅዱስ ያ ማለት በብዙ መንገድ የየራሱ ታሪክና ጥልቅ የሆነ ሐተታን ቢጠይቅም እኔ ግን እግዚአብሔር እንደ ፍቃድ በሦስት አበይት የሥአገልግ እይታ እንመለከተው ዘንድ እነሆ፦

1ኛ፦ በፊት በነበረው እርዮተ ዓለም ለምድ የሥአገልግዎቹን በቅጥር መልክ ሳይሆን በአስገባሪዎች አማካኝነት የባርነትን ስራ እንደ ህጋዊነት ይሸጡ ይለውጡ እንደነበር  መጽሐፍ ቅዱስ እንዲ ብሎ ይገልጽልናል “በብር የተገዛ ባያ” /ዘ 1244/ እንዲል!  

2ኛ፦ በባርነት ሳይፈልጉና ሳይፈቅዱ በግዳጅ ያለምንም ክፍያ እንዲያውም እየተደበደቡ፣ ስቃይና መከራ እየተቀበሉ፣ እየተገደሉ፣በሚወልዷቸውም ልጆች ጭምር ዓይናቸ እያየ፣ በመሪር ልቅሶና እሪታ አንጀታቸው እየተላወሰ ወንድ ልጆቻቸው ለሞት፥ ሴት ልጆቻቸውን ደግሞ፤ በጽኑ ሥራ፥ በጭቃ፥ በጡብም በእርሻም ሥራ ሁሉ፥ በመከራም በሚያሠሩአቸው ሥራ ሁሉ፥ ሕይወታቸውን ያስመርሩአቸው እንደነበር፥ እንዲሁም ግብፃውያን የእስራኤልን ልጆች በመከራ እንደገዙአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ በሰፊው ያትትልናል። /ዘጸ 1፥ 13-14/

3ኛ፦ ሦስተኛው ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔር መልአክቶች፣ለሟቹ፣ አገልጋዮቹ፣ ነቢያቶች፣ አጠቃላ ለመንፈሳ አገልግ ሲሉ ራሳቸውን በተጋጋ ይጠሉ። መሆ እንደ እግዚአብሔር ቃል ለመንፈሳዊ አገልግሎት ይህን ቃል የተጠቀሙትን በአጭሩ እንይ፦