ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፥ የዓለም መድኃኒት፣
ተወልዶ፥ ከድንግል ማርያም ቅድስት፣
ፍቅሩን ሲገልፅላት፥ እነሆ፦ እናቴ አላት፣
እኛም እንበላት፥ በክርስቶስ ፍቅር እናታችን ናት።
ክርስትና፥ ኦርቶዶክ ዘ ተዋሕዶ ነች፣
የቅዱሳኑን ስማቸው፥ ታከብራለች፣
ከክርስቶስ ስርዓት፥ ያልበረዘች፣
ሁሉን ነገሯን፥ ስለ እርሱ ያደረገች።
መጥምቁ ዮሐንስ፥ ክርስቶስን ሲሰብከው፣
የዓለም በግ፥ መድኅነ ኢየሱስ ነው ሲለው፣
አይሁድ ፈሪሳዊያን፥ ለካስ ሞኞች ናቸው፣
አፍጥነው ለመስቀል፥ እቅድ አዘጋጅተው።
በተንኮልና በሐሰት ተመካክረው ዋሉ፣
ሁከት እንዳይነሣ
በበዓል አይሁን አሉ።
ዕረቡ፥ የከንቱ ከንቱ ምክር ተፀነሰ፣
ቀኑ ጸጥ ብላ ዋለች ዕለት ሐሙስ፣
በዚች ሌሊት ተያዘ የዓለም ንጉስ፣
ዓለሙን በደሙ ሊያነፃ ክርስቶስ።