Tuesday, June 24, 2014

ሆ ማርያም ጽናትሽ፦



ተወልደሽ ከአባት ከእናትሽ፤
ከኹለት ቤተ እምነት ኾንሽ።

ከፍትሕ ፊት ቢያቆሙኝ፣
የክስ ፋይል ቢከፍቱብኝ፣
አንገቴን አቀርቅሬ አዳመጥኹኝ፤
ዳኛው ተናገሩ በቃ ትገደል አሉኝ።

በሕይወት ለመኖር፥ እድል ቢሰጠኝ፣
ለውሳኔ፥ ሦስት ቀን ብቻ ቢታወጅብኝ፣
በሃይማኖቴ አልግደረደርም ክርስቲያን ነኝ፤
አዋጁን ሰምቼ በአርምሞ ልቤን አጸናሁኝ።

ልቤ አይደነግጥም እጸናለሁ በአማላጁ፤
የማይተወኝ ገብርኤል ይቆማል ከደጁ።

ከትንታግ እሳት፥ የሚታደገኝ፣
ገብርኤል ነው ስሙ እወቁልኝ፣
የኢየሱስ ልጁ ነኝ የማይተወኝ፤
አለ የድንግል ልጅ ምንም አይነካኝ።

ምን እኾናለው ብኖርም ብሞትም፤
እኔ የኢየሱስ ነኝ አልደነገጥኹኝም።

ሆ ማርያም፦ ጽናትሽ ሃያልና ድንቅ ነው፣
የሃይማኖት ጽናትሽን እንዴት ተማርሽው፣
ሆ ማርያም ከወዴትና እንዴት አገኘሽው፣
እንደሚታረድ በግ አንገትሽን የሰጠሽው።

በሞሪያም ምድር የሄደውን፣
ምዕራፍና ጥቅስ ያላለውን፣
ዳግም ይስሐቅን አሳየሽን፤
ከሞት አፋፍ የነበረውን።

እኔማ፥ እኔማ አንብቤ ነበር፣
ያለያቸው ከክርስቶስ ፍቅር፣
ከቅዱሱ ቃል የቅዱሳኑን ክብር፤
በዘመኔ ዐየሁሽ የጽናትሽን ፍቅር።

በእጸ ሳቤቅ፥ ይስሐቅን ታድጎታልና፣
የማርያም ጽናት፥ ልዩና ድንቅ ነውና፣
ኅህቴ ማርያም፥ ጽናትሽ ይደርብኝና፤
ለታደገሽ አምላክ ይድረሰው ምስጋና።

(እንደ ሠልስቱ ደቂቅ፥ ማርያም ያህያ ኢብራሂምን በተስፋው ቃል ጎብኝቷት ከአንበሳ መንጋጋ ለታደጋት፤ ውዳሴና ክብር ምስጋና ለወልደ እግዚኣብሔር ለወልደ ማርያም ልጅ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን አሜን!!!)


[፲፯//፳፻፮ /]

Saturday, June 21, 2014

"መንፈሳዊ አገልግሎት" በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

"የእግዚአብሔርን ሥራ በቸልታ የሚያደግ ርጉም ይሁን" (ኤር ፵፰፥፲)

"እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፤ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።" (ሉቃ ፲፯፥፲)

አንድን አገልግሎት "መንፈሳዊ አገልግሎት" ነው የሚያሰኙት፤ እነዚህ አራት ነገሮች ሲኖሩት ነው

፩፤ አገልግሎቱ፦ ሠማያዊ ዋጋ፥ ታስቦ የሚደረግ ከኾነ ነው። የሚመራውም በመንፈስ፣ የሚሠራውም በመንፈስ ከኾነ ነው "መንፈሳዊ አገልግሎት" የሚባለው። ምድራዊ ዋጋ ታስቦ የሚደረግ ከኾነ "መንፈሳዊ አገልግሎት" አይደለም፤ ይኼ ሥራ ነው።

፪፤ አገልግሎቱ፦ በመንፈስ የሚደረግ ከኾነ ነው። የሚመራውም በሥጋ፣ የሚሠራውም በሥጋ ከኾነ፤ "መንፈሳዊ አገልግሎት" ማለት አይቻልም።

፫፤ አገልግሎቱ፦ በትህትና ከኾነ ነው። ከትዕቢት፣ ከሥልጣን፣ ከክብር፤ እነዚህን ከመሳሰሉት ነገሮች የራቀ ከኾነና በትህትናና ራስን ዝቅ በማድረግ የሚደረግ ከኾነ ነው፤ ይኼ ነው "መንፈሳዊ አገልግሎት" ማለት የሚቻለው። "መንፈሳዊ አገልግሎት" ምድራዊ ክብርን የሚያመጣ፣ ምድራዊ ሥልጣንን የሚያመጣና በምድር ሠዎችን በጣም ከፍ የሚያደርጋቸው ከኾነ "መንፈሳዊ አገልግሎት" መኾን አይችልም። "መንፈሳዊ አገልግሎት" ኾኖ ቢጀመር እንኳን "መንፈሳዊ አገልግሎት" ኾኖ አያልቅም።

፬፤ አገልግሎቱ፦ መሥዋዕትነት ካለበት ነው፤ "መንፈሳዊ አገልግሎት" አገልግሎት የሚባለው። የሚያገለግለው ሠው እራሱ መሥዋዕት እየኾነ የሚያገለግለው ከኾነ ነው። ሌላውን እየሰዋ የሚያገለግለው ከኾነ፣ ወይም ደግሞ ምንም ዐይነት መሥዋዕትነት የማይከፈልበት ከኾነ አገልግሎቱ፦ "መንፈሳዊ አገልግሎት" ነው ማለት አይቻልም። አንድን አገልግሎት፦ "መንፈሳዊ አገልግሎት" ነው የሚያሰኙት እነዚህ አራት ነገሮች ናቸው።

         "መንፈሳዊ አገልግሎት" በሚል (በሰባኪ ወንጌል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ) በዲ/ ዳንኤል ክብረት የተሰጠ መንፈሳዊ ትምህርተ ወንጌል ሰምተውና  አዳምጠው፤ ስጋዎትንና ነፍሶትን ይመግቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ተጋብዘዋል።

         እግዚአብሔር አምላክ፦ ለወንድማችን ቃለ ሕይወትን ያሰማልን፤ መንግሥተ ሠማያት ያውርስልን። አሜን!

Wednesday, June 18, 2014

"ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።" /፩ኛ ዮሐ ፭፥፲፱/



(በ፰//፳፻፮ / [15/6/2014 EC] በጣሊያን ሮማ ከተማ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፥ የደብረ ከነዓን ቅድስት ሥላሴ / ቅጽር ግቢ ካነሳዋቸው ፎቶዎች።)

ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በአንደኛው መልእክት በምዕራፍ አንድ ቁጥር አስራ ዘጠኝ ላይ እንዲህ ይላል፦ "ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።" /፩ኛ ዮሐ ፭፥፲፱/

አምላካችንና መድኃኒታችን፣ መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በዚህ ዓለም ላይ በነበረበት በሥጋ ወራት፤ "የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ" /፩ኛ ዮሐ ፫፥፱/ ይህ የተገለጠው፥ አምላክና መድኃኒት ነው። አልፋና ኦሜጋ ነው፣ አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው ነው፣ መጀመሪያውና መጨረሻው እርሱ ነው፤ እኔ ነኝም ይላል። /ራእ ፳፪፥፳፫/ እርሱ ከዳዊት ዘር የተወለደው፦ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የድንግል ማርያም ልጅ፣ አማኑኤል የተባለው፤ እርሱ መድኃኒትና ፈዋሽ፤ ለዓለም የተሰዋ በግ ነው።

ይኼ ሥም፥ አጋንት የሚንቀጠቀጡበት፣ ኃያላን በረዓድ የሚርበተበቱበት፣ ነገሥታት ጉልበታቸውን የሚያንበረከኩለት፣ ጥበበኞች መዕባ የሚያቀርቡለት፣ ምላስ ሁሉ የሚያመሰግነው፣ ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘለዓለም አባት፣ የሠላም አለቃ፣ አማኑኤል፣ ኤልሻዳይ፣ አዶናይ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

"ስለዚህ፥ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ" /፩ኛ ዮሐ ፫፥፱/ ለሠው ልጅ ጠላት የኾነው ርኩስ መንፈስ ቀርቦ፦ "ዲያብሎስም ረጅም ወደ ሆነ ተራራ አውጥቶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው።" ብሎ፤ ዲያብሎስ፥ ራሱን የስልጣን ባለቤት እንደኾነ በመቁጠር፤ ከአምላካችንና ከጌታችን ጋር ስለ ዓለማት ነገሥታት ክብርና ዝና፣ ላልተገባ የክፉ ስግደት እንዲሰግድለት በጠየቀው ጊዜ አምላካችን ክርስቶስ "ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል" /ሉቃ ፬፥፩-፲፫/ ብሎት፤ የዲብሎስን የተንኮል ሥራ እንዳፈረሰ፣ ርኩስ መንፈስ እንደገሰጸና ለመንፈሳዊ አባቶች ስልጣንን፣ ለእኛ ለምዕመናን አማኝ ደግሞ እንዴት መጽናት እንዳለብን የነፍሳችን መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ በቃል፣ በምግባር፤ አስተምሮናል።

Monday, June 16, 2014

ሃይማኖታዊ የሚመስሉ፥ ኢ-ሃይማኖታዊ፤ ጽንሰ-ሐሳቦችን ማርቀቅ፤ ለምን? (ክፍል ፪)



የ“ሼሪዓ”ው እስልምና ለክርስትና እና ለሌላው ቤተ-ሃይማኖት ያለው አመለካከት በጣም የተዛባና ፍጹፍ የኾነ ጥላቻ ነው። “ሼሪዓ”ው፥ ያስከተላቸው፣ እያስከተለ ያለውና የሚያስከትላቸው መዘዞች ብዙ ናቸው፤ ይኼንንም የምለው እንዲሁ ከመሬት ተነስቼ አይደለም። “ሼሪዓ”ው እስልምና የሃይማኖት ሊቃውንቶቻቸው ዘንድ ስለ ክርስትና፦ የሚጽፉት፣ የሚናገሩት፣ እንዲሁም አጠቃላይ በሌላ ቤቴ-ሃይማኖቶች ላይ ያላቸው አስተምህሮ መንፈሳዊነት አይታይባቸውም። ለዚህም ማስረጃ ይኾነኝ ዘንድ፦ የ“ሼሪዓ”ው አፍቅሪያን ግለሰቦችና ቡድኖች፥ የሌላ ቤተ-ሃይማኖት ማየት ያስጠላቸዋል፣ ይቀፋቸውማል።[፭] በዕንባና በለቅሶ፥ በታላቅም ጩኧት እየጮኡ የሳውዲው ዋሀቢ ሰባኪ፥ ክርስቲያኖችንና አይሁዶችን የሚረግም ከሱራት ቁራን እየጠቀሱ በስሜት ተውጦ ሲያለቅሱ እንደነበር [፮] እና  “ሼሪዓ”ው እስልምና አፍቃርያን ቡድኖች፤ በክርስቲያኖች ቤተ-ሃይማኖቶች ላይ የቃጠሎ፣ በክርስቲያን አማኞች ላይ ደግሞ፥ የትንኮሳ፣ የማሰቃየት፣ የመደብደብ፣ የመግደልና ከቀዬ የማባረር ተልኳቸውን ሲፈጽሙ እንዳየን፤ የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ነው። [፯]

የፖለቲካ ሠዎች የተባሉት፦ እነ አቶ ጀዋር መሐመድ እና የፖለቲካ አጋሮቻቸው፤ የፖለካ ሰዎስለው ለመታየክረው ነበር። ሃይማኖታዊያን ከሚመስሉ፥ ከኢ-ሃይማኖታዊ ከኾኑ ግለሰቦችና ቡድኖች ጋራ በማበር፣ የፖለቲካ ጽንሰ-ሐሳቦቻቸውን በማርቀቅና የፖለቲካ ጥላቻ አመልካከታቸውን እስልምና ሃማኖ በመጫን፤ በክርስቲያኖች ላይ የቃላ ጦር ሲሰነዝሩና ልቱ ዐየናቸው ሰማናቸው። የእነ አቶ ጀዋር መሐመድ፥ የፖለቲካ ጽንሰ-ሐሳቦቻቸውንና የጥላቻ አመልካከታቸውን በሙስሊሙን ሕብረተሰብ በመጫን፣ እስልምናና በክርስትና በቤተ-ሃይማኖቶች ላይ ግጭት እንዲፈጠር፣ ሕዝቡ እርስ-በርስ እንዲበላላ፣ ደም መፋሰስ እንዲር፣ እልቂት እንዲነግስ ለማድረግ የነደፉትን የጥላቻ ንድፍ-ሐሳብቸውን ሲዶልቱና ሲያስዶልቱ እጅጉን ታዘብናቸው[፰] ይልቅስ፥ የእነ አቶ ጀዋር መሐመድ፥ የፖለቲካ ጽንሰ-ሐሳቦቻቸውንና የጥላቻ አመልካከታቸውን ወዳጆች ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻችንና ኅህቶቻችን ሙስሊሞችም ሳይቀሩ ነው የተቃወ (ኾንም ያለበ ተቃሞ!)

እነ አቶ ጀዋር መሐመድ እና የፖለቲካ አጋሮቻቸው፤ ድ ቅችናችን የሀገራችን ሕዝበ-ሙስሊሙ ሕብረተሰብ፥ በክርስቲያኖች ላይ በላቻ እንዲነሱ፣ ክርስቲያኖችንን ለማጥፋት፦ "በሜንጫ፥ አንገት አንገታችንን እንዲጨፈጭፉ" የጥላቻ ስብከታቸውን ሰበ እኛ ክርስቲያኖች፥ በታላ ኢትዮጵያ ሀገራችንውቧ ክልላችን በኦሮምያ ላይ እንዳንኖር ህልውችንን ለመሻ ክሩ፣ ሕይ እንር፥ ድራሻችንን ከነ አካቴው እንድንጠፋ የላቻ ስብከታቸውን አስተጋቡ። ሀጅ ነጂብ በተራቸው፦ ''የኢትሕዝብ ህብረተ-ሰእብ ትንሹሚሊ ይኾል፣ዚህ ሚሊን ውስጥ ሰማያ ፐንት (80%) ኦሮሞ ነ,,,,'' ሲሉ ተደምጠዋል። በማከተልም፦ “የቀረው ሃያ ፐርሰንት (20%) የትም ሊደርስ አይችልም ሲሉ እንደተናገሩት ልብ እንበል! እንግዲህ እንደነ አቶ ጆዋር መሐመድ እና የፖለቲካ አጋሮቻቸው ዐይነቶች፤ ኢትዮጵያን ሊያስተዳድሩ ሥልጣን ቢኖራቸውና ቢችሉ ኖሮ የሃይማኖት ነፃነት ምን እንደሚመስል ቡዙ መተንተን አልያም ነብይ መኾን አያስፈልግም።[፱]

Wednesday, June 11, 2014

ሃይማኖታዊ የሚመስሉ፥ ኢ-ሃይማኖታዊ፤ ጽንሰ-ሐሳቦችን ማርቀቅ፤ ለምን? ክፍል ፩


ሃይማኖት ማለት፦ ሠማያዊ ነገርን በመሻት፥ መንግሥተ ሠማያትን ተስፋ በማድረግ፤ የሚኖርበት ማለት ነው። ታዲያ፥ የማንኛውም ሃይማኖተኞች መሪዎች ለሃይማኖት እምነት ተከታዮቻቸው (ለምዕመኖቻቸው) የሚያምኑበትን፥ እምነትና ሃይማኖት በፍቅርና ስለ ፍቅር ሊሰብኩላቸው፣ የሰበኩላቸውንም በልባቸው ውስጥ እንዲታተም ማስተማር አለባቸው። ተስፋ ስለሚያደርጉት ስለ ሠማያዊት መንግሥተ ሠማያት በመናፈቅ ከዓለማዊ ምኞት በጸዳ ኹኔታ አስረግጠው ማስተማር መኾን አለበት!። ለምን ቢሊ፥ የሠው ልጅ በእዚች ምድር እስከሚኖርበት ጊዜ ድረስ፦ ከተወለደበት ቀዬ ወደ ሌላ ቀዬ፣ ከነበረበት ከተማ ወደ ሌላ ከተማ፣ አድጎና ተምሮም የዕውቀር ማዕድ ካወቀባት ሀገር ወደ ሌላ ሀገር ሲሄድ የሚያጋጥሙትና በሕይወቱ የሚከሰቱ ክስተቶች ብዙ ነገሮች አሉʼ። ከክስተቶቹ አንዱ ደግሞ እምነትና ሃይማኖት ነው፤ በዚህ ጊዜ የ“ሃይማኖት፥ የነፃነት ምርጫ” ወደሚለው ክስተት ራሱን ይፈልጋል።

በሀገሩም ይሁን ከሀገሩም ውጭ፤ ባጋጠመው በዚህ የ“ሃይማኖት፥ የነፃነት ምርጫ” ክስተት ፍለጋ ከእናትና ከአባቱ የወረሰው ሃይማኖት ይኹን፣ በተለያየ ምክንያት የተቀበለውን እምነትና ሃይማኖት ይዞ ቢጸና እሰየው ያስብላል። ከእዚህ በተረፈ ሃይማኖቱን በየትኛውም መንገድ ከተማም ውስጥ ይኹን በየትኛውም ሀገር ላይ በሕይወት እስካለ ድረስ እምነቱንና ሃይማኖቱን ሊቀይር ይችላል፤ ወደ ሌላ እምነትና ሃይማኖት ራሱን ቀየረ ማለት የራሱን መንገድ ፈለገ ማለት ነው። የፈለገውን ሃይማኖትና እምነት የመከተል ከአምላክ የተቸረው ልዩ ሥጦታ ነው። ይኼን ሥጦታ ደግሞ የቀድሞ ቤተ-ሃይማኖቱ ከቻለች በድጋሚ አስተምራ በቀድሞው እምነትና ሃይማኖት እንዲጸና ማድረግ አለበዚያ ግን ለየአንዳንዱ ሠው ከአምላክ የተቸረውን የእምነትና የሃይማኖት ነፃነትን በጸጋ መቀበል አለባት።

ቢጣፍጠንም ቢመረንም፦ የሠውን ልጅ የእምነትና የሃይማኖት የነፃነት ምርጫውን ማክበር አለብን! ሊከበርለትም ይገባል!። በእስልምና ሼሪዓግንዚህ የተለየ ነው። የቀድሞውን ሃይማኖቱን ብቻ በመቀየሩ ምክንያት፦ እንደ ማፊያ ቡድኖችና እንደ ወንጀለኛ ድርጅቶች፤ ከዚህ ሃይማኖታዊ ድርጅት ከወጣህና ወደ ሌላ ሃይማኖት ከሄድህ ውርድ-ከራስህ፤ ዐይነት ነገር ይባላል። እንደ ማፊያዎቹ አባባል፦ “ምስጢር ታወጣለህ፣ አልያም ሀገርን ለጠላት አሳልፎ እንደሸጠ” ተቆጥሮ፤ የሞት ፍርድ ይበየንበታል። [፩] ዶ/ር ዛኪር እንዳሉት

የ“ሃይማኖት፥ የነፃነት ምርጫ” ከዶ/ር ዛኪር በፊት የነበሩት የሙስሊሞች መምህራን እንኳን የሠዎችን የእምነት ነፃነትን በመንፈግ እምነቱን ለሚቀይር ከፊቱ ላይ የመቃብር ቁፋሮ እንዳለ ያመላክታሉ። እንደተናገሩትም፥ እንደዚህ እያሉና እያስባሉ፦ “አንገትህን በሠይፍ እንቀላለን፣ በሕይወት የመኖርህ ህልውና ነገር ያከትማል፣ አትኖራትም፣ ንብረትና ልጆችህ ለሃይማኖታዊ ድርጅቱ” በማለት ጊዜ ያለፈበትና ሃይማኖቱን ለዘላቂያዊ በፖለቲካ ለማካሄድ የነደፉት፦ ሃይማኖታዊ የሚመስሉ፥ ኢ-ሃይማኖታዊ፤ ጽንሰ-ሐሳብቦችን ማርቀቅ ለምን? እንደፈለ ሙስሊሙ ሕብረተሰብ እንዴት እስከዛሬ አይረዳውም!!!።

Wednesday, June 4, 2014

“እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ።” /ዮሐ ፰፥፵፬/



የእግዚአብሔር ቃል ክብር ለሚገባው ክብር መስጠት እዳለብን ያስተምረና፤ /ሮሜ ፲፫፥፯/ ቢኾንም ግን አንዳንድ የፕሮቴስታንቶች ፓስተሮች (የተቃዋሚ አገልጋዮች) ይኼንን አምላካዊ ቃል ወደ ጎን በመተው የራሳቸውን ሥጋዊ ምኞቶቻቸው እንዳዛዘቸው እየፈጸሙና እያስፈጸሙ ነው። አባታችሁ ዲያብሎስ ከመፈሳ ይልቅ ምኞት ላሳወራቸው፤ ምኞታቸውን የተከተልጉትንና የኙትን ነገሮ ሁሉተ-ክርስቲኒቷ ላይ እጃቸውን በኃይል በመጫን ያሻቸውን ማድረ ጀምረዋል።

ቢኾንም ግን ከመጀመርያው ጀምሮ ፕሮቴስታንቶች፥ ከካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሲያፈነግጡ፤ የነበራቸው እምነትና ሃይማኖት ከካቶሊካውያን የወረሱትን መሠረታዊ የካቶሊካውያንን ሥርዓት በመያዝ ነበር። ሉተር፥ ከካቶሊካውያን ያፈነገጠበት ዋናው ምክንያት፦ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን በወቅቱ ለአንዳንድ ነገሮች የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስለፈለገች ስለነበር  ያዘጋጀችውን ትኬት “የመንግሥተ ሠማያት የመግቢያ ትኬት” ነው፤ ትኬቱን ግዙ እያለችና እያስባለች በነበረበት ወቅት በሉተር አማካኝነት ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ተቃውሞ  ገጠማት። ይኼም ተቃውሞ እየበረታና እያየለ ኼዶ፤ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን የራሷን ልጆች የነበሩትን እነ ሉተርን በማግለልና እነ ሉተርም የራሳቸውን ተቃውሞ በሀገሩ ላይ በተለያዩ  ከተሞች የሚገኙ የቀድሞ የካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን በሮች ላይ የተቃውሞውን ሐሳቦቹን ጽፎ ለጥፎ ነበር።

ይኹን እንጂ፥ የፕሮቴስታንቶች እምነትና ሃይማኖት እንደዚህ ከመቀየሩ በፊት፦ ለመድኃኒታችንና ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳንና ለሰማህታት ባዘዛቸው መንገድ፥ ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያም፣ ለቅዱሳኑ፣ በአጠቃላይ ከካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን የወረሱትን ሃይማኖታና ባህላዊ፣ ትውፊትና ቅዱሳት መጽሐፍቶቻቸውን እስከተወሰነ  ጊዜያት ድረስ ይጠቀሙበት ነበር።

ከዛ በኋላ የተነሱ ልዩ ልዩ የፕሮቴስታንቶች መሪዎችና ፓስተሮች የተዛባ አስተሳሰባቸውን በመርጨት፦ ለድንግል ማርያምና ለቅዱሳን፣ ለሰማህታትና ለፃድቃን፣ ለደናግልና ለአባቶች፤ እንዲሁም ደግሞ ለቅዱሳት መጽሐፍትና ለቅዱሳት ሥዕላት፤ ማንቋሸሽ፣ ማብጠልጠል፤ ጥቅም አልባ ማድረግ፤ ከምዕመናኑ፥ ልቦናና ኅሊና ፍቆ ማውጣት፤ የነደፉት ንድፈ-ሐሳባቸውን በመጫን ያላቸውን ጥላቻ ቀስ በቀስ ቀጠሉበት።