Showing posts with label ነገረ ጠቢባን. Show all posts
Showing posts with label ነገረ ጠቢባን. Show all posts

Friday, January 23, 2015

"በርታ ሠውም ሁን"፦ (፩ኛ መጽ ነገ ፪፥፫) አስራ ኹለቱ ምክረ ዘ መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ


በርቱ፥ ሠውም ሁኑ! ሠው ለመኾን የሚከተሉትን መንገዶች እንኺድ

፩፤ አምልኮታችንን፦ እናክብር።

፪፤ እግዚአብሔር ቃል፦ ምግባችንን እናድርግ።

፫፤ የአሕዛብን መንፈስ፦ ከኅሊናችን ውስጥ እናውጣ።

፬፤ የሎጂክ ኑሮዎቻችንና የሎጂክ የእውቀት ጠባዮቻችንን፦ እግዚአብሔር አምላክ መንገድ ላይ እንጣለው።

፭፤ የአባቶቻችንን መንፈሳዊ ታሪክ፦ እንደገና ለመገመትና ለማንሳት እንሞክር።

፮፤ የቤተ-እግዚአብሔር መንፈስን፦ በፍቅርና በጸጋ የምንመላለስበትን ጉልበት እንድናገኝ፥ እንበርታ፤ እንጸልይ።

፯፤ በንስሐና በቅዱስ ቁርባን፦ የተባረከ ትውልድ፣ ጊዜ፣ ዘመን እንዲኖረን፤ ዕቅድ (ፕሮግራም) እናውጣ።

፰፤ የዘወትር ዕቅዶቻችን፦ እግዚአብሔር መንፈስ የተመራ እንዲኾን፥ በጸሎት እግዚአብሔር መንገዳችንን አደራ እንስጥ።

፱፤ የዕውቀታችንን ግማሽ፦ እግዚአብሔር መንፈስ ያለበት እንዲኾን ለማድረ፥ እንደገና አዕምሮዎቻችን ወደ አምላክ እንመልስ፤ የነፍስ ትምህርት እንዲኖረን፥ እንዘጋጅ።

፲፤ የዚህን ዓለም ሃብት፦ እንደ ዕለት እንጀራ እንጂ እንደ ዘላለማዊነት አስበን፣ በክፉ ምትአታዊ አኗኗርና ዲያብሎሳዊ ስሜትና ሐሳብ ውስጥ ገብተን የሟርት ኑሮን አንያዝ።

፲፩፤ እግዚአብሔር ክብርና ጸጋ የተሞላ ኑሮ እንዲኖረን፦ ዕለት ዕለት ሠማያዊ ምስክነት ይኑረን።

፲፪፤ መንፈስ ቅዱስ መግለጫ እንድንኾን፦ ዘወትር በአካኼዳችን፥ እግዚአብሔር ግርማ ሞገስ የተላበስን፣ በእምነቱና በቅዱስ ቁርባን ፊታችን የተባረከና የተሻሸ፣ ሠማያዊ ወዝ ያላቸው ልጆች እንዲፈጠሩና እንዲወለዱ፤ እግዚአብሔር አምላክን፥ እንማጸን።


እነዚህ ሂደቶች በሕይወታችን ውስጥ ካሉ፦ ሠው የመኾን ብርታትና እድላችን ሠፊ ነው።

 -----------------------------------------------------------------------------------------------
(ምንጭ፦ ሬዲዮ አቢሲኒያ፥  መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ መንፈሳዊ ትምህርት፤ ክፍል ፳፫)
 ----------------------------------------------------------------------------


Sunday, November 30, 2014

መጀመሪያ ሰው ነኝ (ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት)



አንድ ወዳጄ በየገጸ ድሩና በየውይይት መድረኩ የሚሰማውንመጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ፣ መጀመሪያ ትግሬ ነኝ፣ መጀመሪያ አማራ ነኝየሚል ክርክር አየናአንተ መጀመሪያ ምድንነህ?›› ሲል ጠየቀኝ፡፡
 
እኔ መጀመሪያ ሰው ነኝ፡፡ የተፈጠርኩትም ሰው ሆኜ ነው፡፡ አምላክም የፈጠረው ሰውን ነው፡፡ ቡድን፣ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ጎሳ፣ ነገድ የሚባሉ ነገሮችን ፈጠረ የሚል መጽሐፍም ትምህርትም አላገኘሁም፡፡ ክብርም፣ ሥልጣንም፣ ጥበብም፣ ፈጣሪውን መምሰልም የተሰጠው ለሰው ነው፡፡ መላእክት ሲፈጠሩ በማኅበር ነው የተፈጠሩት፡፡ አንድ ላይ ነው የተገኙት፡፡ ሰው ግን ሲፈጠር በየተራ ነው፡፡ መጀመሪያ አዳም፣ ከዚያ ሔዋን፣ ከዚያ ቃየል፣ ከዚያ አቤል እያለ ተራ በተራ፡፡ ቡድኖቹን ሰው በኋላ ራሱ ፈጠራቸው እንጂ አብረውት አልተፈጠሩም፡፡

መጀመሪያ ሰውነቴ ነበረ በኋላ ቡድኔ መጣ፡፡ በኋላ የመጣው ቡድኔ በፊት የነበረውን ሰውነቴን ከዚህ አትለፍ ከዚህ አትውጣ፣ ከዚህ አትዝለል ከዚህ አትሻገር አለው፡፡ ቡድኔ በእኔ መጠራት ሲገባው እኔ በቡድኔ ተጠራሁ፡፡ ለእርሱ ህልውና ሲል እኔን ሰዋኝ፡፡ እርሱ ሳይመጣ በፊት ግን እኔ ሰውዬው ነበርኩ፡፡

መጀመሪያ ሰው ስለነበርኩ መጀመሪያ ሰው ነው መከበር ያለበት፣ መጀመሪያ ሰውነቴ ነው መብት የሚያስፈልገው፣ ሰውነቴን አሥረህ፣ ገርፈህ፣ ገድለህ፣ ነጥቀህ፣ ቀምተህ ቡድኔን ከየት ታገኘዋለህ? እኔን ትተህ እንዴት እኔ ለፈጠርኩት ቅድሚያ ትሰጣለህ? እኔን ንቀህ እንዴት እኔነት ተሰባስቦ ላቋቋመው ቡድን ክብር ትሰጣለህ? ይኼማ ሐሰት ነው፡፡ ሴሎቹን ገድለህ ሰውየውን ማኖር ትችላለህ? ገጾቹን ገንጥለህስ መጽሐፉን ታኖራለህን? ከብቶቹን አርደህ ስለ መንጋው መጨነቅስ ምን ማለት ነው?

Sunday, August 10, 2014

የሁላችንም ሐሳብ



         በቅንነት፥ ብንነጋገርና ብንሠራ፣ የሁላችንም ሐሳብ ለኢትዮጵያ ይጠቅማል እንጂ አይጐዳም!”  (ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ)