Sunday, January 26, 2014

መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ! /1ኛ ቆሮ ፪፥፲፫/

         እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በእኛ ላይ አድሮ መንፈሳዊውን ቃል የሚያናግረን፣ መልካም የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥልቅ ሐሳብና እንድንማማር የሚያደርገን እርሱ ባለቤቱ ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከዘመነ ልቦና እስከ ኦሪት ድረስ ስለ ድንግልና በሰፊው ከሚያትቱልን ዓበይት ክፍል አንዱ በኦሪት ዘፍጥረት ላይ ነው። ስለ ርብቃ፥ ድንግልዋን ጠብቃ ስለመኖሮ፦ "ወንድ የማያውቃት ድንግልም ነበረች" ይላል። /ዘፍ ፳፮፥፲፬/ እንዲሁም፥ ስለ ዮፍታሄ ልጅ ስለ ድንግሊቱ፤ /መሣ ፲፩፥፴-፵/ በአጠቃላይ ስለ ድንግልና ጠበቆ መገኘትና ድንግልና ጠበቆ አለመገኘት፤ በእግዚአብሔር ዘንድና በእስራኤላውያን እምነትና ሃይማኖት አንፃር ምን ያህል ትልቅ ሥፍራ እንዳለው ሊቀ ነቢያት ሙሴ በዘ ዳግም ምዕራፍ ፳፪ ከቁጥር ፲፫-፳፰ መመልከት፤ ማንበብና ማገናዘብ ብልህነት ነው እግዚአብሔር በነቢያት አንደበት አድሮ ትንቢቱንና የእግዚአብሔር ልጆች በሕይወታቸው ምን መምሰል እንዳለባቸው በተለያየ ጊዜያት ተናግሯል። በሐዲስ ኪዳንም፥ ስለ ድንግል ማርያምም በነቢየ ኢሳያስ ቀን አስቆጥሮ፣ ትንቢት ተናግር፦ "ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።" /ኢሳ ፯፥፲፬/ ተብሎ የተተነበየው ትንቢት ጊዜውና ሰዓቱ ሲደርስ "እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።" /ማቴ ፩፥፳፫፤ ሉቃ ፩፥፳፯/

ለማጠየቅም፥ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም፤ ወደ ገላትያ በላከላቸው ክታቡ ላይ፦ "ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ" በማለት፤ "ሴት" ብሎ ስለ እናቱ ድንግሊቷ ድንግል ማርያም፣ "የተወለደውን ልጁን" ብሎ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይገልፃቸዋል።

ሌላውና ዋናው ርዕሰ-ጉዳዬ "የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም" /ማቴ ፩፥፳፭/ የሚለው ሐረፍተ ነገር (ቃል) ነው። እራሳቸው ስተው ሌላውን ለማሳት ደፋ ቀና የሚሉ ሠዎች፦ ይህንንም አሳባቸውን እንዲያጠናክርላቸው "አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች።" እና "ቃየንም ሚስቱን አወቀ ፀነሰችም፥ ሄኖሕንም ወለደች።" /ዘፍ ፬፥፩ እና ፲፯/ በማለት ታላቅ የሆነ የስህተተ ስህተት፤ የጥፋት ጥፋት እየሠሩ ይገኛሉ። በመቀጠልም የልባቸውን ምኞት ለማሳካት እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ በማለት፦ "እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም" ካለ ከወለደች በኋላ አወቃት ማለት ነው፤ በማለት የተዛባ ትርጓሜ ያክሉበታል፤ እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን!

Sunday, January 19, 2014

SARĀBĀMON OF NIKOU (ቅዱስ ሰራባሞን)


By Dr Amsalu Aefera Assistant Prof – SARĀBĀMON OF NIKOU IN ETHIOPIAN LITERATURE.

ስለ ቅዱስ ሰራባሞን ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን? በዘመነ ሰማዕታት የተነሳ፣ አርዮስንና መሊጦስን በትምህርቱ የተቃወመና የረታ፣ ብዙ ገቢረ ተአምራትን የሠራ፣ የኒቅዩ (በግብጽ ውስጥ የምትገኝ ሀገረ ስብከት) ሊቀ ጳጳስና ሰማዕት ነው። እንመልከት። በረከቱ በሁላችንም ላይ ይደርብን።

St. Sarābāmon, Bishop of Nikou, lies among those important oriental saints whose reputation reached the Ethiopian Orthodox Church. According to his vita (see further below), he was a descendant of the proto-martyr Stephen and raised as a Jew in Jerusalem under the birth name of Simon.  After journeying to Alexandria, he was baptized by Archbishop Theonas (282-300), the 16th Pope of Alexandria, and then set about studying Scripture, including the Epistle of Ignatius and Balkiros.  He then became a monk in El-Zogag[1] monastery.  When the Alexandrian Patriarchate passed to Peter, the Seal of the Martyrs (300-311), Simon was made a patriarchal assistant, and later was appointed bishop of Nikou, with the ordained name of Sarābāmon, upon the death of John, the incumbent of that office.  The Ge‘ez version of the vita states:

የጥምቀት ጥልቅ ምስጢሩ

ዛሬ ገሃድ ነው፥ የጌታ ዕጹብ ድንቅ ሥራ፤
ዓለም እንዲያውቀው፥ የአምላክ ብርሃን በራ።

አብ በደመና፥ በክብር ተገለጠና፤
ክርስቶስ፥ በዮርዳኖስ ተጠመቀና፤
የሠላም ርግብ፥ መንፈስ ቅዱስ መጣና፤
የሦስት አካላት፥ ምስጢር ተገለጠና።

ትልቋ ባህር አየች፥ ሸሸች፤
ዮርዳኖስም፥ ወደኋላ ተመለሰች፤
ኮረብቶች ዘለሉ፥ እንደ ጠቦቶች፤
ንዕማን ከለምጹ፥ ኢዮብን ከቁስሉ አዳነች።

ከደማስቆ ወንዝ ይልቅ፥ በዮርዳኖስ ተጠምቀው ቢውሉ፤
ከያዕቆብ አምላክ ፊት፥ የምዕረት ብርሃን ተቀበሉ።

የጥምቀት ጥልቅ ምስጢሩ፥ መዳኛ ነው፤
በወንጌል የተጠመቀ፣ ይድናል እንደተባለው፤
አይሁድ አለቃ፥ ለኒቆዲሞስ የተነገረው፤
እግዚአብሔር መንግሥት መውረሻ ነው።

የሥላሴ ልጅነት የሚገኝበት፥ እያው ምስጢር፤
ጥበብ አለን፥ አወቅን ከሚሉት ሲርቅና ሲሰወር።

ጌታም አለ፦ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፤
ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ፥ እንዴት ታምናላችሁ?።

እወነቱ ይሄ ነው! እኛም ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለድን፤
ወደ እግዚአብሔር መንግሥት፥ ልንገባ እንዳይቻለን፤
የድንግል ልጅ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ አስታወቀን፤
እነሆ፦ በጥምቀት ከእርሱ ጋር እንተባበራለን።

ዛሬ ገሃድ ነው! የጌታ ዕጹብ ድንቅ ሥራ፤
ዓለም እንዲያውቀው፥ የአምላክ ብርሃን በራ።

(እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!!)

Thursday, January 9, 2014

አዲስ ትርጉም፣ ቀላል አማርኛ፣ የማይፈልግ፤ እውነተኛው መፅሐፍ ቅዱስ!



                        መፅሐፍ ቅዱስ፥ ድሮና ዘንድሮ፣ በሮሜ ምዕራፍ ላይ
 
        
ይህ የአማርኛመፅሐፍ ቅዱስ 1937 ኢትዮጵያ ስትጠቀምበት የነበረው መፅሐፍ ቅዱስ ነው። አዲስ ትርጉም፣ ቀላል አማርኛ፣ የማይፈልግ፤ ግልፅ ሆኖ፤ የተፃፈና አቀማመጡም ግልፅ የሆነ ነው።

        
ዘንድሮ ባለው መፅሐፍ ቅዱስ፥ በሮሜ ምዕራፍ ቁጥር ፴፫-፴፬ ላይ እንዲህ ይላል

"
እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።" /ሮሜ ፰፥፴፫-፴፬ /

        
1937 ኢትዮጵያ ስትጠቀምበት የነበረው መፅሐፍ ቅዱስ ነው። ድሮው መፅሐፍ ቅዱስ ሮሜ ምዕራፍ ቁጥር ፲፬ ደግሞ እንዲህ ይላል፦

"
እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሰዎች የሚነቅላቸው ማነው? እርሱ ካጸደቀ ማነው የሚኰንን? ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ፥ ከሙታንም ተለይቶ ተነሣ፤ በአብ ቀኝ ተቀምጧል፤ ስለኛ ይፈርዳል።" /ሮሜ ፰፥፴፫-፴፬ /


                                  †††
ክርስቶስ ኢየሱስ ይፈርዳል!!! †††

              
እንግዲህ እራስችሁን መርምሩ፦ <<ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።>>





Saturday, January 4, 2014

በገ’ና ዋዜማ፥ ገና ነው ገ’ና


እንኳን አደረሳችሁ!
የምስራች ለሁላችሁ።

አዳም ሆይ፦ አትብላ ከተባልከው በልተህ፤
††† ,,,, ከአምላክህ እቅፍ፥ ከገነት ተባረህ፤
ትኖር ጀመር፥ ከሔዋን ጋር ተባብረህ፤
ምን ያደርጋል! ፅድቅ ከአንተ ተገፎብህ።

በነቢያትና በፃድቃን የተነገረው በሙሉ፤
ቃል በማዕፀን እንደ ተወሰነ ይናገራሉ።

ብሥራት አብሳሪው ቅዱስ ገብርኤል፤
ኤልሳቤጥ ትመስክር ስለ ድንግል፤
ስምዖን ሲባርክ ማርያምን ባርኳል፤
የሠው ልጅ ሁሉ ገና ይማጸናታል።

††† ,,,,,,,,,,,, በገ’ና ዋዜማ፥ ገና ነው ገ’ና፤
የእረኞች የይባቤ ምስጋና መች ተሰማና፤
የእናቱ ፅናት ልጇን በማዕፀኗ ይዛለችና፤
የነቢያት ትንቢታቸው ሲፈጸም ነው ገ’ና።

Friday, January 3, 2014

ሦስቱ ስንቆች፦


የሕይወትን ውጣ-ውረድ ለማሸነፍ ስትታገል፥ መሠናክሉ ብዙ ነው። ነገር ግን፥ ለሕይወትህ ምንግዜም ቢሆን ቢያንስ ሦስት ነገሮች ስንቅ ማድረግ ያለብህ ነገር አለ።



 
መሠናክሉን ለማለፈ፥ ሦስቱ ስንቆች፦ አንድም በአርምሞ፣ ሁለትም በትግዕስት፣ ሦስትም በፅናት፤ ነው።

ሁልጊዜም እነዚህን ነገሮች ለራስ ገንዘብ ካደረኻቸው፤ የሕይወትን ውጣ-ውረድን በመቋቋምህ ምክንያት፥ ከራስህም አልፈህ ለሠዎች ተምሳሌት ትሆናለህ።