Friday, March 21, 2014

ተግሣጽን አትቀበሉምን? /ኤር 35፥13/



የክብሩ ሞገሥ፦ በሠማያት፣ በምድር፣ በጥልቁም ሥፍራ ያለ፤ እግዚአብሔር ለፈጠረን ፍጥረቱ (በተለይ ለእኛ በአምሳሉ ለፈጠረን ሠዎች) ስለሚወደንና ስለሚያፈቅረን ይገሥጸና! በነጐድጓድና መባርቅት፣ በከባድም ደመና ድምፅ፣ በብርቱ የንፋሳት ውሽንፍር ድምፅ፤ እግዚአብሔር፥ ህዝቡን ይገስጻል!።

ከነዚህ፥ ከተፈጥሮ ተግሣጽ ይልቅ ግን ተግሣጽን በአንደበተ-ቃል (ከሠዎች በሚወጣ ቃል) ሲገሥጽ በብሉይም በሐዲስም እናያለን። ለምሳሌ ያህል፥ በብሉይ፦ እግዚአብሔር፥ በሚወዳቸውና እንደ ሐሳቡና እንደ ትህዛዛቱ የሚሄዱትን አገልጋዮቹን በመላክ፣ በነቢዩ ኤርምያስ አንደበት አድሮ፦ ተግሣጽን አትቀበሉምን? /ኤር 35፥13/ እያለ ያናግር ነበር እናነባለን።

ይህ ተግሣጽ፥ በብሉይ ብቻ ሳይሆን በሐዲስ ኪዳንም ቢሆን የምናገኘው እውነታ ነው! ይህ የተግሣጽ እውነታ ደግሞ እራሱ ባለቤቱ፦ የፍቅር አምላክ፣ የተግሣጽ ጌታ፣ መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስም በመዓክለ ምድር ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በስጋ ተወለዶ፣ (ከበረት ውስጥ መወለድ ጀምሮ እስከ በዓለ ዕርገት፤ የተተረከውን ብናነብና ብናስተውል፣ በመንፈሳዊ ዕይታ ብናያቸው፣ ፍቅርን ብቻ ሳይሆን ተግሣጽ እናገኛለን! ) ሲያስተምርና ይህንን ዓለም በፍቅሩ አቅርቦ፣ በተግሣጹ ገሥጾ፤ ሕይወትን እንድናገኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያት እንዲህ ሲል ጥያቄ አቀረበላቸው፦ "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?" ብሎ ሲጠይቅ፥ ሐዋርያትም በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን፣ እንዲሁም በአይሁድ ረበናት ካህናት የሚባለውንና የሚናገሩት ቀድመው ስለሰሙ፦ "አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው፤ ይላሉ አሉት።"

Thursday, March 20, 2014

በመልአከ መንክራት ግርማ ወንዱሙ ላይ ማጉረምረም ለምን?


አንዳንድ ወንድሞችና እኅቶች በመልአከ መንክራት ግርማ ወንዱሙ ትምህርት ቢመሰጡም፤ የተስጧቸው፥ ያህል ግን አጥጋቢ መንፈሳዊ ስንቅ ያለመያዛቸው ጉዳይ በተጠይቅና በፍልስፍና ጥያቄዎች ሲዳክሩ ማየት የተለመደ ነው።

እንዚህ ሠዎች የዲያቢሎስ መንፈስ ስልትና ውጊያ አለማገናዘባቸው፣ በመንፈሳዊ ትምህርታቸው ውስጥ የሚያስተላልፉት መንፈሳዊ ትምህርቶች ወደጐን በመተው፤ ከአምላክ የተቸራቸውን የጸጋ ሃብተ-ፈውስን በመንተራስና በመለጠጥ፣ አጉልተው፥ ለማጣመምና ሃብተ-ፈውስን "በአጋንት አለቃ አጋንትን የሚያወጣ ሠው ናቸው" በማሰኘት፣ ከመንፈሳዊ ዕይታ ይልቅ በኢ-መንፈሳዊ ዕይታዎች በማቀናጀት፣ ለማጣጣልና ከእግዚአብሔር ጸጋ-በረከት ህዝቡ እንዲርቁ በአሳቻ ምክር በመምከርና በክፉ ዕይታ እንዲታዩ በማሳየት፤ ትልቁን፥ የማጥመቅ አገልግሎት ማለትም፦ ከቤተ-ክርስቲያን ምስጢራት አንዱ "ምስጢረ ጥምቀት" የወጣ ነው፤ ብለው፥ ሲያወሩና ሲፅፉ እያየን ነው።

ቢሆንም ምስጢረ ጥምቀት ከቤተ-ክርስቲያን ምስጢራት አንዱና ዋነኛው ሲሆን፤ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ሆነና ስለ ምስጢረ ጥምቀትን (-አማናዊ የሆኑ ሠዎች፦ ወደ ክርስትና ሊመጡ ቢወዱ ንስሐንና ክርስትና እንዲነሱ ሲፈቅዱ የሚያደርጉትን የቀኖና ስርዓት ከምስለ ወድምፅ VCD 1-27 እንዲሁም መፅሐፋቸው፣ በተጨማሪም በአቢሲኒያ የሚተላለፈው በመንፈሳዊ ትምህርታቸው የተካተተ ነው!) በተለይም እንዴት እንደሚፈጸም በ፪፯ኛው በምስለ ወድምፅ በየረር ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን በአውደ ምዕረት ላይ በተካሄደው ንስሐ ክርስትና እንዴት በቤተ-ክርስቲያን ምስጢራት እንደሚከናወን፤ የተገለጸና የታመነ በቂ ምስክር ነው!

እግዚአብሔር፥ ጸጋ በረከታቸውን ያብዛልን፤ እርሳቸውንም ከሠዎች ከንቱ ውዳሴና ከንቱ ማጉረምረም በተጋድሎና በጽናት ያቆይልን፤ አሜን!

Sunday, March 2, 2014

ግብረ-ሰዶማውያንና የባህድ ስውር መነፅር፤ ለሃገራችን አይበጃትም!



ሚኒስትር / ዘነቡ ሆኑ የኢአህዴግ ባለስልጣናት እንዲሁም የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቢሆኑም በግብረ-ሰዶማውያን ላይ በአፅኖት ማስገንዘብ አለባቸው። ዳር-ዳር ማለት አያዋጣም!

እውነት ነው ኢትዮጵያ የሴቶች፣ የወጣቶች፣ የሕጻናትና የእናቶችን ነገር በተመለከተ፤ ቡዙ የብዙ፣ ሕጎቿን በማጥበቅ እና እጅግ አድርጋ አርቅቃ መስራት ይጠበቅባታል እንጂ ለአስጸያፊ ድርጊት የአሜሪካንንና የአውሮፓ ሃገራትን የሞት ምኞት ማስተናገድም ይሁን በር መክፈት የለባትም!

እርግጥ ነው፤ በመንግስ መገናኛ-ብዙሃን፦ ስለ ግብረ-ሰዶማውያን አስከፊነት፣ የነውር ድርጊት መሆኑን፣ የሥነ-ልቦና ቀውስ እንደሚያስከትል፣ በዚህ አስጸያፊ ድርጊት የገቡና የኖሩ ሰዎች ለተለያየ በሽታዎች የመያዛቸው ዕድል በጣም ከፍ-ያለ ሰፊ መሆኑን፣ በጭንቀትና በውጥረት መሰቃየታቸው እንደሚጨምር፣ እራስ-በራስ የማጥፋት ደረጃ በነዚህ ሰዎች ላይ ቁጥሩ እንደሚያይል፣ አጠቃላይ ግብረ-ሰዶማውያን አስከፊነትና መራራነት፤ በዜና አውታራቸው አለመዘገባቸው፤ ወዴት እየሄድን ነውም? ያሰኛል!

ወዳጆች ሆይ፦ በውጭ ዓለማት ላላቹ፤ በተለይ ደግሞ በአሜሪካና በአውሮፓ ሃገራትን ያላቹ! ዘመኑ ከባርነት ዘመን ወደ ዲሞክራሲያዊ ባርነት ዘመን (ከሃገራችን የወጣንበት የተለያየ ምክንያት ቢኖረንም) ላይ መድረሳች ይታወቃል። ይህን ስል፥ ማንም ቢሆን ሃገሩ ላይ መኖን የሚጠላ ሠው ያለ̕ አይመስለኝም።