Thursday, April 25, 2013

“ምስጢራዊው ቡድን”

 በመምህር ምሕረትተአብ አሰፋ (የደብረ መዊዕ ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ስብከተ ወንጌል ሐላፊ)

“በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።” 1ኛ ጴጥ 3፥15
 

     በዚህ “ምስጢራዊው ቡድን” በተሰኘው ቪሲዲ ትምህርታችን የምንመለከተው በተዋህዶ ጓዳ በክርስትና ዓለም ምሽጋቸውን መሽገው በዲቁናና በቅስና እንዲሁም በምንኩስና ከተቻላቸውም በጵጵስና መሐረግ በየአብያተ ክርስቲያናቱና በየገዳማቱ ተደብቅው ከቆዩ በኃላ ውስጣችን አጥንተው ምስጢራችንን አየተው የስለላ ስራቸውን በማጠናከር ቀን ጠብቅው ጊዜ አመቻችተው እኛ ኮብልለናል እናንተም ኮብልሉ በማለት እንጀራችንን በልተው ተረከዛቸውን በኛ ላይ ስለሚያነሱብን ወገኖች ነው።

        ሃያ ሰባት ዓመት በክርስትናው ዓለም ቆይቻለሁ፥ ክርስትናንም ከእግር እስከ ራሱ መርምርያለሁ ነገር ግን የሚያሳምነኝ ነገር ለህሊናዬ አላገኘሁም በማለት፦ “ጉዞ ወደ ኢስላም” በሚል የኮበለለውን በእንጦንስና በመቃርስ ቆብ የቆመረውን የትላንቱን አባ ወ/ሥላሴ የዛሬው ኻሊድ ካሳሁንን ምስጢራዊ ተልዕኮ መርምረን ላነሳቸው ጥቄዎች መልስ የምንሰጥ ሲሆን በቀጣይነት ልክ እንደ ኻሊድ ካሳሁን “ብርሀናዊው ጎዳና” በማለት የክርስትናውን ዓለምና ክርስትናን በማጠልሸት ለኮበለለው ዳኢ ኻሊድ ክብሮም መልስ የምንሰጥ ይሆናል።

               ከሁሉ አስቀድመን ማስተዋል ያለብን ነገር ቢኖር ሠው የፈለገውንና የመረጠውን እንዲሁም ያመነበትን ማምለክ እንደሚችል ሕገ እግዚአብሔርም ሆነ ሕገ መንግስት በሚገባ ደንግገውታል። ነገር ግን ሠው ከራሱ አልፎ ሌላው ያዋጣኛል ብሎ ያመነበትን ማንቋሸሽና ማጠልሸት ተገቢ ነው ብለን አናምንም።

       መቼም ዛፍ እራሱን ለመከላከል ካልሆነ በቀር መኪና ገጭቶ አያውቅም እንደተባለ፥ ሳንደርስባቸው ለደረሱብን፣ ሳንነካቸው ለነኩን፤ ዶግማችንና ቀኖናችን እንዲሁም ሥርዓታችንን አልፎም ትውፊታችንን ለመናድ ለሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች እንደየ አመጣጣቸው ተገቢውን መልስ መስጠት ግድ ይለናል።

  • ሁኔታዎች አሳሳቢ እየሆኑ ነው የተነገት ትንቢቶች በአፋጣኝ እየተፈጸሙ ነው ወደድንም ጠላንም አሁን የመጨረሻው መጨረሻ ላይ ነን።

  • ስለዚህ በአፋጣኝ ይህንን ቪሲዲ ይመልከቱና ላላዩት በማሳየት ክርስቲናዊ ግዴታዎን ይወጡ።

 የኻሊድ ካሳሁንና የዳኢ ኻሊድ ክብሮም የተዛባ አስተምህሮታቸው፦

1. እንፍጠር፣ በዓርያችንና በአምሳላችን የሚለው ቃል ክብርን የሚመለክት ነው። እንግዲህ ይሄንን ነው የክርስቲያን ሙሁራን ሥላሴን ሊያስረዳ ይችላል ብለው ሚተነትኑት። ግን ሥላሴን አያስረዳም። በእውነት አያስረዳም።

2. ማንም ሰው ሲወለድ ሙስሊም ነው።

3. ስታጠምቁ በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቁ አለ። ልክ ነው በአዛኙና በእሩሩ ረቂቅ በሆነው አምላክ ስም አጥምቁ። አዎ ማንም ሰው ሲታጠብም ሆነ ሲበላ በፈጣሪው ስም ነው ማድረግ ያለበት። ይሄ ነው ትርጉሙ፥ ጥምቀትን በተምለከተ ነው። ሥላሴን በተምለከተ አይደለም።

4. ከዘ ፍጥረት እስከ ራዕይ ዩሐንስ አንዲትም አንቀፅ የለችም ሥላሴን የሚያመለክት። እና መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሥላሴ የሚል ቃል አታገኝም።

5. እኔ፦ እድሜ - ልኬን በክርስትና ውስጥ ለሃያ ሰባት ዓመት ኖርያለሁ። ክርስትና ትምህርት አጥንቻአለሁ። ምስጢረ ሥላሴ፣ ምስጢረ ሰጋዌ፣ አምስቱ አህማደ ምስጢር፤ ተምርያለሁ፣ አስተምርያለሁ። እኔ ግን አልገባኝም። እኔን ብቻ አይደለም ያስተማሩኝም አልገባቸውም። እኔም ስጠይቃቸው ከጠየ ... ኳ ... በ   ከጠየኳቸው ውጪ   እሚ ... የ   ከ ... መ   ከመለሱልኝ ውጪ የሚያስረዱኝ የለም፥ ሳይገባህ መኖር ይቻላል። (እዚህ ጋር ቃላቱና አንደበቱ ተኮለታትፏል። እውነት ያስተማሩት አስተማሪዎቹ መለስ ሳይምልሱለት ቀርተው ነውን??? ወይንስ ጠይቆ ላለመረዳት የተደፈነ ልቦና ይሆን??? አልያስ ከእኔ በላይ ለአሳር ብሎ ይሆን??? ይህ ከንግግሩ፣ ከቃላቱና ከአንደበቱ ያስታውቅበታል።)

6. የሥላሴ አስተምህሮት፦ የኢየሱስ ክርስቶስ አስተምህሮት አካል አልነበረም።

7. አይደለም እስከ ክርስቶስ የነበሩት ይቅርና ከክርስቶስም በኃላ፤ ክርስቶስም ሥላሴ አላስተማረም።

      ለእነዚህ እና ሌላ መሰል የተዛባ አስተምህሮታቸውንና እነርሱ ስተው ሌላውን ለማሳት የተደረገውን ሴራ የሚያጋልጥ፥ ጥልቅና ድንቅ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፍቃድ የተዘጋጀ ቪሲዲ ይመልከቱና ላላዩት በማሳየት ክርስቲናዊ ግዴታዎን ይወጡ።

No comments:

Post a Comment